Translate

Monday, January 28, 2013

ስልጣንና ንግድ በህውሃት መንደር


27/01/13

Author and writer Tesfaye Zenebe from Norway
ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
አመልና ልማድ የትም ቢሆን አይለቅምና  ከሃገርና ከህዝብ መዝረፍ የለመደው የወያኔ ህውሃት ቡድን ድንበር ተሻግሮ በኢትዮጲያ  ቴሌቪዥን አማካኝነት ያልከፈለበትን የ29ኛው የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ማስተላለፉ ከነሱ አልፎ ቤሄራዊ ክብራችንን የሚነካ የወረደ ተግባር መሆኑ አስረጂ አያስፈልገውም፡፡ ስለሆነም  በካፍ መግለጫ መሰረት የኢትዮጲያ ቴሌቪዥን በዚህ ሳይከፍል ሰርቆ ባስተላለፈው ስርጭት ላይ የሃገር ውስጥ እስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶችን እየጠራ ተጨማሪ ገቢ ማግኘቱ ሌላው አሳፋሪ ተግባሩ  ነው፡፡ የኢትዮጲያ እግር ኳስ ቡድን ከ31 ዐመታት በሗላ ለዚህ መድረሱ ህዝቡን ቢያሰደስተውም  ጫወታውን በቀጥታ ለማስተላለፍ ግን የወያኔ መንግስት  አቅም የለኝም ማለቱ ጫወታውን በጉጉት ለሚጠባበቀው ህዝብ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ 18 ሚሊዮን ብር እንኳን በዘረፋ ለደለበ የወያኔ ቡድን ቀርቶ ስርዓቱ ላፈራቸው ህገወጥ ባለሃብቶች በጣም ቀላል እንደ ሆነ ብዙዎች ይሰማማሉ፡፡ሆኖም ምኑም ባለየለት ምክንያት  ህገወጥ ስርጭት በማስተላለፍ ቤሄራዊ ክብርን  ማስነካት ይቅር የማይባል በደል መሆኑን ልብ ሊባል የገባዋል፡፡
በመሰረቱ  የወያኔ ህውሃት  ስርዓት፡ ስርዓት ከተባለ ከመጀመሪያው አንስቶ (ከምስረታው አንስቶ)ሀገር ማዋረድ፣ ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠት፣ በዙዎች የተሰዉለትንና  ለሶስት ሺ ዘመን ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገርን  ባህልና ቅርስን ማጥፋት (መመዝበር) ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ነገር ሁሉ በመዝረፍና ማግበስበስ ያኔ ጠዋት በእድሜያቸው  መጀመሪያ የተነሱለት የማይሰንፉበት  አላማቸው  ነው፡፡
ከደደቢት ጀምሮ የተነሰለትን ሃገር የማፍረስና የመናድ እቅዶቸውን ለመተግበር እንደ  መነሻ የወሰዱት እርምጃ  በወቅቱ የህዝብና  የሃገር ሃብት  የሆኑት ባንኮችን  መዝረፍ፣  በመቀጠልም  እስካሁን  በስሙ በሚነገድበት  በትግራይ ህዝብ  ርሃብና  ሰቆቃ ላይ በመንተራሰ ለርሃብተኛው የመጣውን እርዳታ  በመዝረፍ  ኪሳቸውን እንዳደለቡ  ይህንን የጥፋት ቡድን  ሲመሰረት አበረው የነበሩ አስረድተውናል፡፡ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት የሃገርና የህዝብን ሃብት እያግበሰበሰ የኖረው የህውሃት ቡድን  የሚፈጥራቸው  የመብት እረገጣዎችንም  ሆኑ የሚያጠፏቸው  የንፅሃን ዜጎች  ህይወት መንስኤው ሃገር በመሸጥ ያግበሰበሱትን ሃብት ለማስጠበቅ ካላቸው ፍላጎት አኳያም ነው፡፡
በመሰረቱ አንድ ሃገር የሚመራ ቡድን የተመሰረተበት አካባቢን በመለየት የንግድና የልማት ተጠቃሚ ማድረግ ከመሰረቱ በእብሪትና በማን አለብኝነት ላይ ለመመስረቱ ማሳያ ነው፡፡
በተለያየ ግዜ የሰርዓቱ አባላት የሚነግሩንና የሚደሰኩሩልን የኤኮኖሚ እድገት በዙሪያቸው ላሉ አፍቃሪ ህውሃት ብቻ እንጂ ለሌላው የህብረተሰብ ክፍል እንዳልሆነ  ህዝብ የሚመራው ከድህነት በታች የሆነ ኑሮ በዚህም ምክኒያት በሃገሩ የመኖር ዋስትና በማጣት ከሃገር በመኮብለል የጎረቤት ሃገራትን እስር ቤት ማጨናነቁና በበረሃ እንዲሁም በባህር መበላቱ  የየቀን ክስተት መሆኑ አለ የሚባለው የኤኮኖሚ እድገት ጥቂቶች ያውም የስርዓቱ ሎሌዎች ብቻ ያበለፀገ ለመሆኑ እማኝ መጥቀስ አያሻውም፡፡
በትግራይ ህዝብ ስም ተሰይሞ የወያኔ ህውሃት ባለስልጣናት ባለ ድርሻ የሆነው ኢፈርት ስላለው ካፒታልም ሆነ አመታዊ ገቢው ምን ያህል እንደሆነ ህዝቡ የማወቅ እድል ባይሰጠውም እነኚሁ የስርዓቱ ሰዎች ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ፍፁም በመናቅና ለክብሩ ቁብ ሳይኖራቸው በአገኙት አጋጣሚ ይህንን የሃገሪቷን አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴ በሞኖፖል የተቆጣጣረውንና የንግዱን የህብረተሰብ ክፍል ከገበያ ውጪ ያደረገ  ከሃገርና ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ የተመሰረተውን ኢፈርት አሁን ስላለበት ግዝፈትና ደረጃ በድፍረት ያወራሉ፡፡
ኤፈርት  ያሉት ቁልፍ የንግድ ተቋማት መሰቦ ሲሚንቶ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል፣ ባባ ዳይሜንሽናል ስቶን፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ኤክስፕረስ ትራንዚት፣ትራንስ ኢትዮጲያ፣አዲስ ፋርማሲዩቲክ፣ ጉና ትሬጊንግ፣ ሂወት አግሪካቸር፣ሼባ ታነሪ፣ ኤክስፔሪየንስ ኢትዮጲያ፣አልመዳ ጨርቃ ጨርቅና ኢዛና ወ.ዘ.ተ. . . . . . .
የነስብአት ነጋ ኢፈርት  ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ከወያኔ ህውሃት በሚያገኘው ፖለቲካዊና ወለድ የለሽ የብድር አገልግሎት በመታገዝ የመንግስት የግንባታ እቅዶችን ያለተቀናቃኝ በመውሰድ የሌሎችን የግል ባለሃብቶችን ከውድድሩ እያወጣቸው መሆኑ በግልፅ የሚታይ እውነት ነው፡፡ በሃገሪቱ ውስጥ ለሚገነቡ ትላልቅ ተቋማት በምርት አቅርቦትም ሆነ በግንባታ በቀጥታ ያለ ጫረታ በመግባት  ምዝበራውን በስፋት ተያይዞታል፡፡ ለምሳሌ መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ከሶስት የስኳር ፋብሪካዎች የ2.6 ቢሊዮን ብር ኮንትራት መውሰዱ፣ መሰቦ ሲሚንቶ የአባይ ግድብ ግንባታን እንዲሁም የግቤ ሶስትን  ግንባታ የሲሚንቶ አቅርቦታ ያለ ተቀናቃኝ  መውሰዳቸው  ባለድርሻ የሆኑት  የህውሃት ሰዎች ከመቼውም  በበለጠ  ምዝበራው ላይ እየተጉ  መሆኑን ያሳየናል፡፡
ብቻ ትልልቆቹ የህውሃት ሰዎች ከኢፈርት በተጨማሪም የግል ሃብት ሲያደራጁና ሲያሸሹ ሲከርሙ ትንንሽ  ሎሌዎቻቸው እንዳቅማቸው ያቺን  ሃገር ሲመዘብሩዋት አመታት ተቆጥረዋል፡፡
ባሳለፍነው አስቸጋሪ ዘመነ ህውሃት ይህ እኩይ ስርዓት ብዙ ገድሏል፣ ብዙ አስሯል የብዙዎችን ቤተሰብ አፍርሷል፣ ብዙዎችን ለአገርና  ለህዝብ ትልቅ ስራ ሊሰሩ የሚችሉ ውድ የሃገር ልጆችን በልቷዋል፣ አሳዷዋል፡፡ በሃገራችን በሰላም የመኖር ህገ-መንግስታዊ መብታችንን እንዲሁም ሰው በመሆናችን ብቻ ሊኖረን  የሚገባውን  ሰዋዊ መብታችንን ጥሰው፣ የኛ የሆነውን ሁሉ ዘርፍውና ሃገር ሸጠው ያካበቱትን  ንብረት ለማስጠበቅ በተቃራኒው ስለ ሃገርና ህዝብ ክብር፣ ነፃነት ያገባኛል ብልው የሚሟገቱ ለምሳሌ እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ መምህርት እሪዎት አለሙና የመሳሰሉት የህሊና እስረኞችን በፈጠራ ክስ  ማጎሪያ ከተዋቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በሁሉም መስክ እጃቸው እረዝሞ በእምነት ተቋማት፣ በሞያ ማህበራት፣ እንዲሁም በየትኛውም የህዝብ አደረጃጀት ውስጥ በመግባት ሁሉም ቦታ ሁሉም ጥግ ደርሶ የሰላም አማራጮችን በሙሉ በመዝጋት በሃይል የበላይነቱን ለማስጠበቅ ዘረኛው ብድን ቀን ከሌት እየሰራ ነው፡፡
በአንፃሩ በህዝብ ወገን በአንድ ጀንብር 17000 ህዝብ ጎዳና ሲበትን፣ በደቡብ የሃገራችን ክፍል ንፁሃን የሱሪ ጎሳዎች በግፍ ተገለው በጅምላ ሲቀበሩ፣ የሙሰሊሙ ህብረተሰብ ሰላማዊ ትግል ያለምንም መፍትሄ አንድ አመት ሲያስቆጥር፣ የዋልድባ መናንያን መነኮሳት ወደ እስር ሲጋዙና ሌሎችም በህዝብና በሃገር በደል ሲፈፀም  በጭፍን የሚመሩን የህውሃት ሰዎች በንዋይና በጉልበት በያዙት ስልጣን የታወረ ህሊናቸው ማስተዋል ነስቷቸው ለሰላማዊ የህዝብ ጥያቄ ሰላማዊ መፈትሄ መስጠት ተስኗቸው እለት ከእለት የህዝብን የመከራ ቀንበር እያከበደበት ይገኛል፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ  ሞት ለወያኔ!
Ftih_lewegene@yahoo.com

No comments:

Post a Comment