Translate

Thursday, January 10, 2013

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ150 ያላነሱ ሱሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ


ኢሳት ዜና:-በሱሪ አካባቢ ተገኝቶ ያየውን ሁኔታ በብዕሩ ያሰፈረ በአንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ  የውጭ አገር ዜጋ የሚከተለውን ሪፖርት ልኳል።

ዲሰምበር 20፣ 2012 የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በባሌሳ ሱሪ መንደር፣ ቢያሆላ   ወይም በአገሬው ቋንቋ ነጭ ድንጋይ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ መጡና ነዋሪዎችን ከበቡዋቸው። ወታደሮቹ ወንዶችን  መንግስት ይህ እልቂት  ፣ ሴቶችንና ህጻናትን እርስ በርስ ካሰሩ በሁዋላ ወደ ዲዲቢ ጫካ ወሰዱዋቸው። 7 ወጣቶች
ብቻ ሲያመልጡ  ሁሉንም በአንድ ጊዜ ረሸኑዋቸው። በመንደሩዋ 154 ሱሪዎች ይኖሩ ነበር።እንዳይነገርበት የሚችለውን ሁሉ እየጣረ ነው። እግዚአብሄር ይመስገን ዜናው ይፋ ወጣ። ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄ ያለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት ለምን ይሆን የኢትዮጵያን መንግስት የሚደግፉት? አሸባሪነትን መደገፍ ሳይሆን መዋጋት አልነበረባቸውም?የሟቾቹ አስከሬን በዲቢዲብ ጫካ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ እንዲቀበር ተደርጓል። አንዳንድ አስከሬኖች በጥንብ አንሳ አሞሮች እና በአውሬዎች ተበልተዋል። አብዛኞቹ ህጻናት በአቆቦ ወንዝ ላይ ተጥለዋል። ከጭፍጨፋው በሁዋላ ወታደሮች ይህን ድርጊት ሪፖርት ባደረገው ላይ ሁሉ ከዚህ የበለጠ አስከፊ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
በሱሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንደቀጠለ ነው። በየወሩም እየከፋ በመሄድ ላይ ነው። ማንም ግን ስለችግሩ የተናገረ አካል የለም። በምእራብ አገሮች በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ የምእራብ ሚዲያዎች ሰፊ የዜና ሽፋን እንደማይሰጡት ሁሉ ፣ በደቡብ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ መጠን ሲገደሉ ግን የዜና ሽፋን ሊያገኙ አልቻሉም።
ባለፉት ሳምንታት ብቻ 147፣ ከሶስት ወራት በፊት 30፣ ከአራት ወራት በፊት ደግሞ 70 ሰዎች ተገድለዋል።
የሱሪ ህዝብ በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን ይገኛል። ሱሪዎች ቻይ፣ ቲርማጋ እና ባሌሳ እየተባሉ በሶስት ይከፈላሉ። ሱሪዎች ከኦሞ ወንዝ በስተምስራቅ በኩለ ከሚኖሩት ሙርሲዎች
ይመሳሰላሉ። አንድ አይነት ባህልና አንድ ቋንቋ ይናገራሉ።  ዛሬ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች መሬቶቻቸውን ለመውሰድ እያፈናቀሉዋቸው ነው። ዲፊድ፣ ዩኤስ አይዲ፣ ቻኢና፣ ህንድ፣ የአውሮፓ ህብረትና ሳውዲ አረቢያ እነዚህን ባለሀብቶች እየደገፉ ጥፋቶች እንዲሰሩ እያደረጉ ነው።
አሁን የተፈጸመው ጭፍጨፋ ምክንያቱ ሰፈራ ነው። ሱሪዎች መሬታቸውን ለቀው መንግስት ባዘጋጀላቸው የሰፈራ ጣቢያ እንዲሄዱ ተነግሮአቸዋል ምክንያቱ ደግሞ ሬታቸው ለአንድ የወርቅ ማእድን ፈላጊ ኩባንያ በመሰጠቱ ነው። ሱሪዎች መሬታችንን ለቀን አንሄድም ይላሉ፤ የኩባንያው ሰራተኞች ደግሞ ስራችንን ማከናወን አልቻልንም በማለት ክስ ያሰማሉ።

    No comments:

    Post a Comment