Translate

Sunday, January 6, 2013

ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ “ኢትዮቴሌኮም”ዌብሳይቶችን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን የማገድ አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡


.በኤን አንድና በኤን ሁለት የማነጅመንት ደረጃ የስራ ድርሻ የተሰጣቸዉ ኢትዮኦጵያዉያን በቁጥር 54 ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ 46.3 በመቶ ወይም ሃያ አምስቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። 
እራሱን “ልማታዊ መንግስት” ብሎ የሚጠራዉ የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ከያዘባቸዉ የመጀመሪያዎቹ አመታት ጀምሮ አስከ ቅርብ ግዜ ድረስ እንደ ቤት ዉስጥ ዕቃዉ ከተቆጣጠራቸዉና የኢትዮጵያን ህዝብ በሚጠቅም መልኩ እንዳያድጉ ካደረጋቸዉ ቁልፍ መስሪያ ቤቶች ዉስጥ አንዱ ኢትዮቴሌኮም ነዉ።  ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ያላደረገዉ ነገር የለም።
የመረጃ ቴክኖሎጂ መሠረት የሆነዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ አፍሪካ፤ ላቲን አሜሪካና ኢሲያ ዉስጥ የሚገኙ በእደገት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮችን ለዘመናት ከተዘፈቁበት የኋለ ቀርነት ማጥ ዉስጥ ጎትቶ አዉጥቶ ወደ ፈጣን የእድገት ጎዳና ይወስዳቸዋል ተበሎ የታመነበትና በአንዳንድ አገሮች ዉስጥ ይህ ለእድገት አመቺነቱ በተግባር የተመሰከረለት ዘርፍ ነዉ።
ይህ ዘርፍ ገበሬዉ፤ ሰራተኛዉ፤ ተማሪዉ፤ ወታደሩና ለሌላም በማንኛዉም የስራ ዘርፍ ለተሰማራ የህብረተሰብ ክፍል የእዉቀት ምንጭ በመሆን የስራ ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የሚረደና በህብረተሰብ መካከል ፈጣን የሆነ የመረጃ ልዉዉጥ አንዲኖር የሚያደርግ ዘርፍ ነዉ።በእድገት  ወደ ኋላ ለቀረችዉ አገራችን ኢትዮጵያም ይሀ ዘርፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ዘርፍ ነዉ።  ነገር ግን በአፍሪካ ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ወደኋላ ከቀርችባቸዉና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ሆን ብሎ እድገታቸዉ እንዲገታ ካደረጋቸዉ ኋላ ቀር ዘርፎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ይሄዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ ነዉ።
ዘረኝነትን በሚጠቅም መልኩ አደራጅቶታል፤ የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆበታል፤ ቻይናዎችን አምጥቶ የስለላ ተቋም አድርጎታል፤ የሚገርመዉ ዛሬ ኢትዮቴሌኮም የተራቀቀዉ በስልክ፤ በኢንተርኔትና በሌሎችም የመገናና አገልግሎቶች ሳይሆን ዜጎችን በመሰለልና የመረጃ ጨለማ በመፍጠር ርካሽና ጎታች ስራዎች ነዉ። ይህንን ርካሽ ስራ ደግሞ በቅርቡ የአገዛዙ የኢንፎርሜሺን ደህንነት ኤጀንሲ ሹም ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን” የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠርና የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን የማገድ አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁም ይህ ነዉ በማለት በአዳባባይ አረጋግጧል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በላፉት ስድስት ወራት ይህንኑ ኢትዮቴሌኮም በሚል መጠሪያ የሚተወቀዉንና በስለላ ስራ ላይ የተሰማራዉን የሲቪል መስሪያ ቤት አደረጃጀት፤ አወቃቀርና የሰዉ ኃይል አመዳደብ በቅርብ ተከታትሎ ከዚህ ቀትሎ የሚታየዉን መረጃ አጠናቅሯል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚገባ እንደሚያዉቀዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን ቴሌኮሚኒኬሺን ተቋም ከኋላ ቅርነት ለማላቀቅ በሚል ሰበብ የኮርፖሬሺኑን የማኔጅመንት ዘርፍ ለፈረንሳይ ኩባኒያ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ። ወያኔ እንደሚለዉ የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ለፈረንሳዩ ኩባኒያ የተሰጠዉ የኮርፖሬ ኑን አቅም ለማሳደግ ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ወያኔ የሚናገረዉና የሚሰራዉ ስራ የተለያየ በመሆኑ ዛሬ ወያኔ ኢትዮቴሌኮም በየዘርፉ የረጂም ግዜ ልምድ ያላቸዉን ባለሙያዎች አባርሮ ታማኝ የህወሀት ታጋዮችን በመተካት ኮርፖሬሺኑን የለየለት የስለላ ተቋም አድርጎታል። ስለሆነም ዛሬ ብዙ የአፍርካ አገሮች ትልቅ ግስጋሴ ያደረጉበትና የዜጎቻቸዉን ህይወት የለወጡበት ዘርፍ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎችን እየሰለለ አገረን የመረጃ ጨለማ ዉስጥ የከተተ ተቋም ሆኗል።
ባላፉት ሁለት አመታት የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ኤን አንድና ኤን ሁለት በሚባሉ ሁለት ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች ተከፍሎ በሁለቱም ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ዉስጥ የሰዉ ኃይል ተመድቧል። ይህ በከፍተኛ ማነጅመንት ደረጃ የተመደበዉ የሰዉ ኃይል ኢትዮጵያዉያንንና የፈረንሳይ ዜጎችን የሚያጠቃልል ነዉ። በኤን አንድና በኤን ሁለት የማነጅመንት ደረጃ የስራ ድርሻ የተሰጣቸዉ ኢትዮኦጵያዉያን በቁጥር 54 ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ 46.3 በመቶ ወይም ሃያ አምስቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በዚህ ከፍተኛ የማነጅመንት እርከን ዉስጥ የኦሮሞ፤ የአማራና የተቀሩት ስድሰት ክልሎች ድርሻ በቅደም ተከተል 18. 5 በመቶ፤ 29.6 በመቶና 5.6 በመቶ ብቻ ነዉ። ከሁለቱ የማነጅመንት እርከኖች ዉስጥ ኤን አንድ የሚባለዉ ከፍተኛዉ ሲሆን በዚህ እርክን ዉስጥ ሰምንት የትግራይ ተወላጆች ሲኖሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች እያንዳንዳቸዉ ሁለት ቦታ የያዙ ሲሆን በዚህ ከፍተኛ የአመራር እርከን ዉስጥ ከተቀሩት ስድስት ክልሎች የተመደበ አንድም ሰዉ የለም።
ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት አራት ብቻ ነዉ (ሁለት ከኦሮሚያ ሁለት ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5 ነጥብ አራት በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን ስምንት ሰዎች ኤን አንድ በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ከተቀሩት ስድስት የአገሪቱ ክልሎች የመጡትን ሰዎቸ ስንመለከት የሚታየዉ ስዕል እጅግ በጣም የሚያሳዝንና ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት እያለ ከሚሰብከዉ ስብከት ጋረ የሚጋጭ ነዉ። በ2012 ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል ዉጭ በተቀሩት ስድስት ክልሎች ዉስጥ የሚኖረዉ ህዝብ 25,627,349 እንደሚሆን ይገመታል። ከዚህ ህዝብ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ እድል ያገኙት .000012 በመቶ ብቻ ወይም ከእያንዳንዱ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ አንዱ ብቻ ነዉ። እንግዲህ ይህንን ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነታቸዉን ተጎናጽፈዋል እያለ የሚናገረዉ።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ ቀደም ወያኔ “የኢትዮጵያ መከላከያ” ጦር እያለ የሚጠራዉን ሠራዊት ምን ያክል የኔ በሚላቸዉ የህወሀት ሰዎች ብቻ እንደሚቀጣጠር የሚያሳይ መግለጫ በመረጃ አስደግፎ ለህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። አሁንም ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ምን ያክል የራሱ የቤት ዉስጥ እቃዉ እንዳደረገዉ የሚያሳየዉን በጽሁፍና በአኀዝ የተፈገፈ መረጃ በዛሬዉ እለት ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸ ከአሁን በኋላም የወያኔን ዘረኝነትና ህግወጥነት የሚያጋልጡ ስራዎችን በተከታታይ እየሰራ ለህዝብ የሚያቀርብ መሆኑን ይገልጻል።

No comments:

Post a Comment