Translate

Thursday, August 16, 2012

ባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ተደጋግሞ በሚነገርባት አገራችን ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በምግብ እጦት እየተሰቃዩ መሆናቸውና አስቸኳይ ዕርዳታ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል የወያኔ ግብርና ሚንስቴር ዴታ አስታወቀ



የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ምትኩ ካሳ የረሃብ ችግሩን አስመልክቶ ነሃሴ 7/ 2004 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እነዚህን በምግብ እጦት የሚሰቃዩ ወገኖች ለመታደግ በገንዘብ ሲተመን 190 ሚሊዮን ዶላር የሚፈጅ 314 ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ ለጋሾች በአስቸኳይ እጃቸውን ይዘረጉ ዘንድ ልመናውን አቅርቧል።

ሚኒስትር ደኤታው በዚሁ ወቅት እንዳለው በምግብ እጦት የሚሰቃዩት ዜጎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጻር 16 በመቶ አሻቅቧል።
የተዛባ ዝናብ፣ የበልግ ምርት መቀነስ፣ ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች የመግዛት አቅም ማጣት በምትኩ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።ይሁንና ሌሎች የሚኒስቴሩ ባለሙያዎች ግን ምክንያቶቹ እነዚህ ብቻ አይደሉም፣ በተለይም በሱማሌ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በየጊዜው የሚታዩ አለመረጋጋቶች በዋነኛ ምክንያትነት ሊጠቀሱ ይገባል ይላሉ።
እነዚህ በምግብ እጦት የሚሰቃዩ ወገኖች  41 ከመቶው በሱማሌ፣ 27 ከመቶ በኦሮሚያ፣ 10 ከመቶ በትግራይ፣ 8.1 ከመቶ በደቡብና 7.7 ከመቶው በአማራ ክልሎች የሚገኙ ናቸው።
የግብርና ሚኒስትሩ በቅርቡ በምግብ ሰብል እራሳችንን እንችላለን ሲል መግለጫ በሰጠ በአጭር ጊዜ በሚኒስትር ደኤታው እንዲህ ዓይነት ተቃራኒ መግለጫ መሰጠቱ የወያኔ ባለስልጣናት ሀገር ያወቀውን እውነት ለመሸፋፈን ምንያህል እንደሚዋሹና እርስ በእርሱ የሚጋጭ መግለጫ ያለ እፍረት እንደሚያወጡ አመላካች ነው።

No comments:

Post a Comment