Translate

Wednesday, August 15, 2012

የተመስገን ችሎት ተራዘመ!


Abe Tokchaw
እንደምን አላችሁልኝ ዜና አስነብባ
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከበርካታ ወዳጆቹ እና የፍትህ ናፋቂዎች ጋር በመሆን ፍርድ ቤቱ እንገናኝ ባለው መሰረት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም “የዳኞቹ ቡድን”  ባለመሟላቱ ለቀጣዩ ሐሙስ ነሐሴ 17/ 2004 ዓ.ም ድጋሚ ተቀጥሯል። ዳኞቹ ምን ሆነው እንዳልተሟሉ ለማጣራት ያደረኩት ሙከራ የለም።

ወደ ፍርድ ቤት በርካታ ሰው ችሎቱን ለመታደም የተገኘ ሲሆን በጣም ስናጋንንም ራሱ ተመስገን ወደ ፍርድ ቤቱ ለመግባት ተቸግሮ ለሌላ ቀን መተላለፉን የሰማው ከሌላ በሰው በሰው እንደሆነ እንገልፃለን። ስንጠረጥርም ችሎቱ የተራዘመው “እዚህ ሁሉ ህዝብ ፊት ምን ተብሎ ያ… ክስ ይቀርባል!” በሚል እንደሆነ እናስባለን!
ዜናው በዚህ ተደመደመ። ሌሎች ዜናዎች ካሉ ለማድረስ እንደምተጋ እናገራለሁ!
ይመቻችሁ!

No comments:

Post a Comment