Translate

Saturday, August 4, 2012

ኢትዮጵያዉያን ተፈናቃዮች በደቡብ

ደቡብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በጎሳ መካከል የተነሳ ግጭት ከሃያ በላይ ሰዎችን ህይወት አሳጥቶ በርካቶችን ለጉዳት ዳርጎ፤ ሺዎችን ወደጎረቤት ኬንያ ካሰደደ ቀናት ተቆጥረዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል ከ10 እስከ 15 ሺህ የሚገምታቸዉ ኢትዮጵያዉያን ተሰዳጆችን የሚረዳበት ድጋፍ ባስቸኳይ እንዲቀርብለት አመልክቷል።
ደቡብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በጎሳ መካከል የተነሳ ግጭት ከሃያ በላይ ሰዎችን ህይወት አሳጥቶ በርካቶችን ለጉዳት ዳርጎ፤ ሺዎችን ወደጎረቤት ኬንያ ካሰደደ ቀናት ተቆጥረዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል ከ10 እስከ 15 ሺህ የሚገምታቸዉ ኢትዮጵያዉያን ተሰዳጆችን የሚረዳበት ድጋፍ ባስቸኳይ እንዲቀርብለት አመልክቷል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አንድ አጥኚ ቡድን ወደስፍራዉ መላኩን ገልጿል። የአካባቢዉ ኗሪዎች ሁኔታዉ አሁን የተረጋጋ መምሰሉን በመግለፅ፤ ለዳግም ግጭት ያደቡ መኖራቸዉን ለዶቼ ቬለ ጠቁመዋል።



በኦሮሚያ ክልል፤ በቦረናና ገሪ ጎሳዎች መካከል ደቡብ ኢትዮጵያ ሞያሌ ዉስጥ የተቀሰቀሰዉ ግጭት ከናይሮቢ እንደወጡ የዜና ዘገባዎች ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዉያንን ለስደት ዳርጓል። ከትናንት ጀምሮ በተደጋጋሚ ስለሁኔታዉ እንዲገልፅልን የጠየቅነዉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሁኔታዉን የሚቃኝ ቡድን ከመላኩ ዉጪ ለተፈናቃዮቹ እስካሁን ያደረገዉ እንደሌለ ነዉ አቶ ሀጎስ ገመቹ የግብረ ሠናይ ድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ እና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ ዛሬ ለዶቼ ቬለ የገለፁት። በጉዳዩ ላይ ከአካባቢዉ ኗሪዎችና ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ያሰባሰበችዉን መረጃ ሸዋዬ ለገሠ እንደሚከተለዉ አጠናቅራዋለች።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ
http://www.dw.de/dw/article/0,,16143866,00.html

No comments:

Post a Comment