Translate

Friday, July 28, 2017

የህወሓት መፈርከስ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያቀርባል !


#ሰበር_ዜና
#አርበኞች _ግንቦት_ሰባት_የሰሜን_ኢትዮጵያ_ዕዝ
በህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ የዓላማ ሳይሆን የጥቅም ግጭት ተፈጠረ። " ጅብ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ነው የሚጣላው " እንደ ሚባለው ሰሞኑን የህወኃት/ኢህአዴግ ሰዎች በማን አለበኝነት ለ26 ዓመት እነሱ እና መሰሎቻቸው የዚችን ምስኪን አገር ሀብትና ንብረቷን በመዝረፍ እነሱ እንደሚሉት በእድገት ጎዳና ያለች አገር ሳትሆን እጅግ ኃላ ቀር ከሚባሉ አገሮች የአገር ጭራ አድርገዋት ትገኛለች። 



በመሆኑም ይህ ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ በሙስና የተዘፈቀና አገሪቱን ለከፋ ድህነት ከመዳረጉም በላይ ለዕዳ ዳርገዋት ይገኛሉ። ይህን አገራዊ ችግር የተናገሩ ሙሁራን፣የፖለቲካ ሰዎች፣የራሳቸው አባል የሆኑ ሳይቀር ተገድለዋል ፣ታስረዋል፣ከአገር በግፍ ተሰደዋል። ከዚያም ጉዳዩ ይህ ስርዓት በስልጣን ላይ ካለ ሙስናን መከላከልም ሆነ ዘራፌዎችን በህግ ለመጠየቅ የማይቻል በመሆኑ በሁሉም መልኩ የተዘጉትን መንገዶች ማለትም የዴሞክራሲ( የፖለቲካ)፣የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ መብቶችን ማስፈን የሚቻለው በኃይል እንጅ በሰላማዊ ወይም በልመና እንዳልሆነ ያመኑ የትጥቅ ትግልን በአማራጭነት በመያዝ በአሁኑ ሰዓት ስርዓቱን ለከፋ ችግር እንዲወድቅና በርካታዎቹን ከጎናቸው በማሰለፍ ለህዝብ አሊንታና መኩሪያ ለጠላት ደግሞ ድንጋጤና ፍርሃትን ለቆበት ይገኛል።

 በሌላ በኩል የራሱ የስርዓቱ ሰዎችም ቢሆኑ ሙስናን፣ስልጣንን ያላግባብ መጠቀምን፣ በተለያዩ ፕርጀክቶች ስም የተመደበን ገንዘብ መዝረፍ ይቁም ማለትና መጠየቅ በራስ ላይ እንደመፍረድ የተቆጠረ ሆነ ፣ ከዚያም ዝርፊያውን በጋራ ተያያዙት ከዚህ ላይ ግን ግጭቶች ብቅ አሉ እሱም ቁልፍ እና በርካታ ገንዘብ የሚዘረፍባቸውን ቦታዎች እኔ ልያዝ እኔ ልያዝ በሚል፣ከዚያም ህወኃት ያለውን ጡንቻ በመጠቀም ቦታዎችን ጠቅልሎ ያዘ ከዚያም ከፍተኛ ገንዘብ የሚመደብላቸው ድርጅቶችን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ሜቴክን መሰረቱ በዚህ ድርጅት አማካኝነት አገሪቱ እንዴት በዘራፊዎች እየተቦጠቦጠች እንደሆነ ሁላችንም እያየን ነው። ከዚያም ህዝቦች ኧረ ባካቹህ ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ሆነ፣ህዝብ ድህነት አጠቃው፣ ጥቂቶች እጅግ በለፀጉ ብሎ ሲጠይቅ ለተወሰነ መልስ ወይም ማስታገሻ ይሆን ዘንድ ምስኪኑን የበታች ሰራተኛ ሰብስቦ በማሰር በራሱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን " ሙሰኞችን በቁጥጥር ስር አዋልናቸው" እያለ ይለፈልፋል ይህን የሰሙ አንድ አዛውንት አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን በሚመሩት የህዝብ መድረክ ላይ የሚከተለውን ቃል ተናገሩ
" አንድ ሰው መንገድ ወጥቶ እየሄደ ሳለ ይመሽበትና ከእንድ ቤት አሳድሩኝ ብሎ ይገባል ሰዎችም እሽ ብለው የመሸበትን እንግዳ ተቀብለው ወደ ቤት አስገቡት በቤቱ ባል ሚስትና አንድ ልጅ ብቻ ይኖራሉ፣ ከዚያም ራት እየተበላ በጫወታ ላይ ድንገት ሚስት ያመልጣቸዋል ከዚያም ደንገጥ አሉ እና አንተ ልጅ ብለው ከእንግዳ ፊት እንዴት እንዴህ ታደርጋለህ ብለው ልጅን በኩርኩም ይመቱቷል፣ ከዚያም ትንሽ ይቆይና ባል ድንገት ያመልጣቸዋል እሳቸውም ደንገጥ በማለት አሁንም ልጃቸውን አንተ ባለጊ በማለት በኩርኩም ይመቱታል ከዚያም ጫወታው ያልቅና እንግዳው ከመቀመጫቸው ሲነሱ እሳቸውም ያመልጣቸዋል ሰውየው ደንገጥ ብለው የት አለ ያነ የፈረደበት ልጅ በሉ አምጡትና እኔም በኩርኩም ልበለው አሉ" በማለት ተረቱባቸው የናንተም የሙስናው ትግል እንዲህ ነው አሏቸው። እንግዲህ በአገሪቱ ያለው የሙስና ሁኔታ ከህዝብ የተደበቀ እንዳልሆነና ሙሰኞች እነማን እንደሆኑ ጠንቅቆ ያውቃል ስለሆነም ይህን ህዝብ ማታለል የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል ህወሓት/ ኢህአዴግ በሚከተሉት ነገሮች አጣብቅኝ ውስጥ ገብቷል።


1ኛ፣ ጂቲፒ እያለ በየ አምስት ዓመት የሚያቅዳቸው እቅዶች ከወረቀት አልፈው ጠብ የሚል ነገር አላሳዩም ይባስብለው ህዝብን በማፈናቀል እና አገሪቱን ለዕዳ ከመዳረግ ያለፈ የፈየዱት አለመኖሩ
2ኛ፣ስርዓቱ ከዓመት ዓመት እየወረደና በተለይ በአሁኑ ሰዓት በነፃነት ታጋዬች በሁሉም ዘርፍ ( በትጥቅም ትግል፣በዲፕሎማሲ) መወጠሩ በስርዓቱ አገልጋዬች ላይ ለፍተኛ ስጋት በመደቀኑ እነዚህም ህዝቡ ቃል የገባንለት ነገር ባለማሳካታችን በጥያቄ እያስጨነቀን ነው የሚሉና እኛ ምንም ሀብት ሳንይዝ ሊሎች በዘረፉት የነሱ አገልጋይ ሁነን ነገ ልንጠየቅ ነው ስለዚህ ከአለንበት ከክልል ኃላፊነት ወደ ላይ አውጡን ወይም አባሳደር አድርጋቹሁ ሹሙን የሚል ጥያቄ በብዛት መምጣት ጀምራል።


 በተለይ ለዛሬ መነሻ የሆነን በአገሪቱ የስኳር አቅርቦትን ይፈታሉ የተባሉ ፉብሪካዎች በልዩ መልኩ አደረጃጀትና አመራር ተመድቦላቸው የነበሩ ፉብሪካዎች የውሃ ሽታ መሆናቸውና የተበላው ገንዘብ ደግሞ የትየለሌ መሆኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ከሆነ ውሎ አድራል ወያኔም ለጥያቄው ቅድም አንድ አባት እዳሉት ዋናዎቹ መሪዎች እነ አባይ ፀሀዪ ተቀምጠው ታችኞችን ማሰሩ መፍቴሄ አለመሆኑ እውነታው እየተገለፀ መጥቶ በአሁኑ ሳዓት የነአባይ ፀሀዪ ቡድን እና የሌሎቹ ቡድኖች ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል። በመሆኑም ይህ የበሰበሰ ስርዓት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል በተለይ ሙስና መገለጫ የሆነበት" በሙስና የተጨማለቀ ስርዓት በሁለት ጎን ይወጠራል ይህም ሙስናን ልዋጋው ቢል ስርዓቱ ይፈርሳል፣ሙስናን ዝም ብሎ ቢመለከትም ይፈርሳል" ስለዚህ ይህ ስርዓት ፈራሽ መሆኑን አውቀን ግብዓተ መሪቱን የማፉጠን ስራ ከሚሰሩት የነፃነት ታጋዬች ጎን እድንሰለፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

No comments:

Post a Comment