Translate

Saturday, July 22, 2017

የኢኮኖሚ ጦርነት (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ)

የህወሓት አገዛዝ ራሱን የኢትዮጵያ ሀብት ባለቤት አድርጓል። አገዛዙን ታማኝነትን በገንዘብና ሥልጣን ይገዛል። በአንፃሩ አገዛዙን የሚቃወሙ ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በኢኮኖሚ እንዲዳከሙና በድህነት እንዲማቅቁ ይደረጋል። በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ማን ሀብታም፣ ማን ደግሞ ድሀ መሆን እንዳለበት የሚወስነው ህወሓት ነው። ማን ምን ያህል ግብር መክፈል እንዳለበትም የሚወስነው ህወሓትና የህወሓት ተላላኪ ድርጅቶች ናቸው።Patriotic Ginbot7 Radio
በዚህም ምክንያት ጥቂት የህወሓት ባለሟሎች እና ከየክልሉ የመለመሏቸው አገልጋዮች ከዚህ በፊት በታሪካችን በማይታወቅ መጠን ሀብት አጋብሰዋል። እጅግ በጣም ጥቂቶች መቶ ሚሊዮኖችን ከመቁጠር አልፈው ቢሊዮኖች ላይ ደርሰዋል። በቁጥር እጅግ የበዛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ከቀድሞው በባሰ አስከፊ ድህነት እየማቀቀ ነው። ልመና፣ የጎዳዳ ተዳዳሪነት፣ ስደት፣ የአዕምሮ ጤና ጉድለት፣ ሥራ አጥነት፣ ረሀብና እርዛት . …. የአብዛኛው ኢትዮጵያው የዕለት ተዕለት ሕይወት መገለጫዎች ሁነዋል።
እዚህ ሀቅ ላይ ቆመን ስናየው ነው በአገዛዙ ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት ማወጅ ፍትሀዊ መሆኑን የምንረዳው። በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡ በርካታ የኢኮኖሚ ጦርነት ስልቶች አሉ፤ ዋና ዋናዎቹን ከዚህ በታች እናቀርባለን።

1. ግብር አለመክፈል – በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ ግብር የዘረፋ መሳሪያ ነው። የኤፈርት ድርጅቶች የሥርዓቱ ቅምጥሎች ናቸው ቁጥራቸው ከ100 በላይ ነው፤ ልዩ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል። ሌላው በግብር ስም ይዘረፋል። የግብር መጠን በአስከፋዩ በዘፈቀደ የሚወሰን ሳይሆን ከፋዩም አስልቶ ሊደርስበት የሚችል መሆን ይኖርበታል። አሁን አብዛኛው ግብር የሚወሰነው በሹም ግምት ነው። ነጋዴዎችና ባለሙያዎች ሂሳብ ሠርተው ቢያመጡ ተቀባይነት አያገኙም። ለኢትዮጵያ ግብር ሂሳብ ከሚያውቁ ባያውቁ ይመረጣል። እንዲህ የተበላሸ አሠራር፣ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-አገር አገዛዝ ባለበት ግብርን ማዘግየት፣ ማዛባት ብቻ ሳይሆን ጭራሹንም አልከፍልም ማለት ፍትሃዊ ነው። በአሁኑሰዓት ግብር አለመክፈል የኢኮኖሚ ጦርነቱ አንዱ ስልት ነው።
2. ገንዘብ – ለኢኮኖሚ ጦርነት ቀዳሚ ትኩረት የሚሻው ለግብይት የሚውለው ወረቀት ወይም ገንዘብ ነው። የገንዘብ ዝውውርን የሚያዛቡ እርምጃዎች የመንግሥትን ሥልጣን የያዘ ጠላትን ኢኮኖሚ የማናጋት አቅማቸው ከፍተኛ ነው። (በነገራችን ላይ፣ ህወሓት በረሀ እያለ ከአልባኒያ የተቀበለው ትልቁ ስጦታው የገንዘብ ማተሚያ ማሽን እንደነበር ይነገራል)
የገንዘብ ዝውውር ላይ ያተኮሩ በቀላሉ ሊታሰብባቸው የሚገቡ የኢኮኖሚ ጦርነት ስልቶች አሉ።
• ለሥርዓቱ የተለየ ቅርበት ካላቸው ባንኮች (ለምሳሌ ውጋገን፣ አንበሳና አባይ ባንኮች) ገንዘባችን ማውጣት ያለብዙ ችግር ሊተገበር የሚችል ነገር ነው።
• በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ዘመዶቻቸው የሚልኩት ገንዘብ የሥርዓቱ አገልጋዮችን በማይጠቅም መንገድ ማድረግ (ጥናትና ዝግጅት የሚጠይቅ ቢሆንም) ይቻላል።
• የሥርዓቱ አገልጋዮች የሚያሸሹትን ገንዘብ እየተከታተሉ ማጋለጥ ሌላው መበረታታት ያለበት ዘርፍ ነው። በኔ በ10 ዓመታት ውስጥ 17 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ መውጣቱ ዓለም ዓቀፍ ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲ መግለጹ እዚህ ላይ ማስታወሱ ይጠቅማል፤ ይህ እነሱ የደረሱበት ነው እንጂ ሀቁ የዚህ ብዙ ጊዜ እጥፍ ነው። 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያወጣል በተባለው “ላም አለኝ በሰማይ” ግድብ ሳቢያ ስንት ሕዝብ ጾሙን እንዳደረ፤ ስንቱ በፕሮፖጋንዳ ጆሮው እንደደነቆረ እያሰብን የሥርዓቱ አገልጋዮች የሚያሸሹትን ገንዘብ ስናሰላ ምሬቱ አንጀታችን ውስጥ ዘልቆ ይሰማናል። በዚህ ዓይን አውጣ ዘረፋ ላይ ጦርነት መክፈት ፍትሀዊ ነው።
3. የሸማቾች አድማ – በዳሽንና ባላገሩ ቢራዎች ላይ የተጣሉ የግዢ እቀባዎች መጠናከርና ወደሌሎችም ዘርፎች መሄድ አለባቸው። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ለተባበረ እርምጃ (Collective Action) የተመቹ በመሆናቸው የተከበሩ ሰዎችና ድርጅቶች የግዢ ማዕቀብ አድማ ቢጠሩ በቀላሉ ተቀባይነት ያገኛሉ። ለምሳሌ
• ሰላም አውቶቡሶች ላይ አለመሳፈር፤
• የአገዛዙ ቀንደኛ አባላት የሆኑ ነጋዴዎች ንብረት በሆኑ ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች አለመጠቀም፤
• በአገዛዙ ሰዎች ንብረትነት በተያዙ የግል ኮሌጆች አለመማር፣
• በአገዛዙ ሰዎች ሆስፒታሎችና የግል ክሊኒኮቻቸው አለመታከም፤
• ውጋጋን፣ አንበሳና አባይ ባንኮችንና ኢንሹራንሶቻቸውን አለመጠቀም።
4. “ኢንቨስተሮችን” ማዋከብ – የሀገራችን አርሶ አደሮች ቁራጭ መሬት አጥተው ቤተሰቦቻቸውን መቀለብ አቅቷቸው እያለ፤ “ኢንቨስተር፣ ልማታዊ ባለሀብት” እየተባለ የሚቆላመጡ ቱጃሮች በ 100 ሺህ ሄክታር የሚገመት ለም መሬት ነፃ በሚባል ዋጋ ይሰጣቸዋል። ወገኖቻችን ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ተሻግረው በማረሳቸው ባዕድ ተደርገው ሲባረሩ ባህር አቋርጠው ለመጡ ቱጃሮች መሬት ብቻ ሳይሆን ብድር እየተሰጣቸው ባለሥልጣናቱ ያሸረግዱላቸዋል። ከሥርዓቱ ጋር ተሻርከው ሀብት በመዝረፍ ላይ የተሰማሩትን ለሀገር በቀልም ሆነ የውጭ ኢንገስተሮችን ማስጠንቀቅ፣ ከሕዝብ የዘረፉትን ንብረት መዝረፍ፤ ካልተቻለም ማቃጠል ፍትሀዊ ነው።
5. ዓለም ዓቀፍ እርዳታዎችና ብድሮች እንዳይሰጡ በለጋሽ አገሮች ላይ ጫና ማድረግ – እንደ ህወሓት አገዛዝ የውጭ እርዳታ ያገኘ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። አሜሪካና እንግሊዝ በሚሰጡት የመሣሪያና የስልጠና እርዳታ ኢትዮጵያዊ ድሀ ይደበደብበታል፤ ይገደልበታል። በእንግሊዝ ርዳታ የሰለጠኑ የህወሓት ሰላዮች የኢትዮጵያን ሕዝን ቁም ስቅሉን ያሳዩታል። በዚህ ሁኔታ ዓለም ዓቀፍ ርዳታን በድፍረት መቃወም ፍትሀዊ ነው።

No comments:

Post a Comment