Translate

Saturday, July 22, 2017

ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ህዝባችን እረፍት አይኖረውም! (አርበኞች ግንቦት7)

መልካሙ ታደግ, ከሮም
Ethiopian Sport and Culture-Festival in Europe
በሮም የተዘጋጀው 15ኛ የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል በወያኔ ኤምባሲና በትግራይ ልማት አቀናባሪነት እንደተዘጋጀ ፣ የፌዴሬሽኑም ኃላፊነት ሙሉ ለመሉ በወያኔ አገልጋዬች እንደተጠለፈ መረጋገጡ በተለያየ መንገድ ሲገለፅ ቆይታል።
አብዛኛው ሃገር ወዳድ የሃገሩና የህዝቡ ጨቋኝና ጨፍጫፊ የአገዛዝ ስርዓት ለመደገፍ በሮም ዝግጅቱ ላይ ላለመገኘት ወስኗል ።

ይህ በዚህ እንዳለ ጁላይ 21 / 2017 በትግራይ ኦን ላይን ላይ የተለጠፈው የ2012 የሮም ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል አዘጋጆች ( የ2017 ንም የሚያዘጋጁት እነ ሃብታሙ ዋቁማ ) መልህክት የ 2017 የሮም ዝግጅትም በወያኔ የመዘጋጀቱን እውነታ ያጋለጠ ክስተት ሆኖ ብቅ ብሏል።
መቼም ትግራይ ኦን ላይን የማንን ለምን ዓላማ የሚሰራ መሆኑን ማብራራት አንባቢን ከማሰልቻት ባሻገር ለቀባሪው ማርዳትም ይሆናል ።
ይሁን እንጂ 2012 የሮም ዝግጅት ላይም የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚዎች በዝግጅቱ ላይ የሰሩትን አሳፋሪ ተግባርና ከጌቶቻቸው የተሰጣቸውን ተልኮዕ ከፈፀሙ በኃላ የወያኔ ልሳን በሆነም ትግራይ ኦን ላይን ላይ ያስወጡትን መግለጫ ዛሬ 5 ዓመቱን ጠብቀው በድጋሚ ፅሁፉን የለጠፉበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንመልከት ።
በ2012 የሮም ዝግጅት ላይ የወያኔ እግር እሳት የሆነውን ኢሳትን የፌስቲባሉ አዘጋጆቹ ( የወያኔ አባልና አገልጋዬች እነ ሃብታሙ ዋቁማ ) በዝግጅቱ ላይ እንዳይሳተፍ በመግፋት በተጨማሪም የነፃ ያህል ለህዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች በማዋከብ አፀያፍ ተግባር መፈፀማቸው የብዘሃን መነጋገርያ የቁጭት አጀንዳ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል ( ጋዜጠኛ ገሊላን ሜዳ ለሜዳ በማሯሯጥ ለማጥቃት ያደረጉት ሙከራ ልብ ይሏል )
በወቅት ይህን ስርዓት አልባ ተግባራቸውን
” የግንቦት 7 ልሳን የሆነውን ኢሳትን ከሜዳ አባረርነው ” በማለት ሲፎክሩ የተስተዋለ ሲሆን ድርጊቱንም በወያኔ መገናኛ ብዙሃን እያቀረቡ ተሳልቀውበታል ።
የትግራይ ኦን ላይን ሪፖርታቸው እንዲመለከቱት ሊንኩ ከዚህ በታች ተያይዟል ።
http://www.tigraionline.com/articles/article120740.html
የ2017ቱ 15ኛው ዝግጅት በወያኔ መጠለፉ በተረጋገጠ ማግስት አዘጋጆቹ በራዲዬናቸው በሰጡት መግለጫ ካለ አንድ ሚዲያ በቀር ( የኢትዩጵያ ወጣቶች የተባለ ) ሌላ ሚዲያ ቦታ የላቸውም በማለት በድፍረት የገለፁ ሲሆን በዚህ አባባላቸው በ2017 የሮም ዝግጅት ኢሳትን ጨምሮ በወያኔ የማይወደዱና የሚፈሩ ሚዲያዎችን መግፋታቸውን አረጋግጠዋል ።
የእነዚህ ቅጥረኞች ተግባር በራዲዬ መግለጫ ብቻ አልተገታም የወያኔ ታዛዥነታቸውንም በይበልጥ ለማረጋገጥ ፣ ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል ያላቸውን ንቀትና ጥላቻ በሚያሳብቅ መልኩ በትግራይ ኦን ላይን ላይ ” Esat Rejected by the Ethiopians in Europe sport & Culture festivel ” የሚለውን የቀድሞ መግለጫቸውን በድጋሚ እንዲለጠፍ አድርገዋል ።
የተከበራችሁ ወገኖች አነዚህ የህወሓት መራሹ አገዛዝ ስርዓት አሽከሮች በህዝብ ስም የተቋቋመውን ማህበር ለፀረ ህዝብ ቡድን አሳልፈው መስጠታቸው በተጨባጭ መረጃዎች እየተገለፀ ባላበት ሰዓት እንደዚህ ለከት የለሽ ስራዎችን በማከታተል የሚሰሩት በማንአለብኝነት ተተብየው እንደሆነ ተረድተን ማህበራችን ለማስመለስ ከምንሰራው ስራ ጎን ለጎን የሮም ዝግጅትን በሙሉ ኪሳራ እንዲጠናቀቅና ወያኔ እንዲሸማቀቅ ለማድረግ በእልህ መነሳሳት ይኖርብናል።
ትግራይ ኦን ላይን የወያኔ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ነው ፣ 15ኛ የሮም ፌስቲቫል አዘጋጆችም የወያኔ ቅጥረኞች ናቸው የሁለቱም ዓላማ ከውጭ ከምንገኝ ኢትዩጵያዊያን ሃገር ውስጥ ያለውን ህዝብ ለማፈን የሚያስችል ግብዕት ( ገንዘብ ፣ የሰው ኃይል ፣ ቁሳቁስ ) መሰብሰብ ነው ።
እምቢ ለወገኔ ገዳይ መጠናከሪያ ድጋፍ አላደርግም ፣ እምቢ በስደት ላይም ሆኜ ለስደት ለሚያበቃ አገዛዝ ስርዓት አልገብርም ማለት ደግሞ የኛ የንፁሃን ኢትዬጵያዊያን ድርሻ ሲሆን በሌላ በኩል ሙሉ ስብዕናን ማረጋገጥና ለህሊና ተገዥ መሆን ነው።
ስለሆነም ሁላችንም የ2017 ሮም ዝግጅትን በማቀብ ገዳያችንን መበቀል የዜግነት ድርሻን መወጣት በአንፃሩም በእስር በግፍና በስቃይ ላይ ያሉ ወገኖች አጋርነትን መግለጫ የዜግነት ግዴታ መሆኑን መቀበል የግድ ይላል ።
እኔ ሮም አልሄድም ለወያኔ አልገብርም ! ! !

No comments:

Post a Comment