Translate

Saturday, July 29, 2017

አዲሱ የአሜሪካ ምክርቤት ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦች ላይ ጭንቀት ፈጥሯል

ትላንት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ የፀደቀው ረቂቅ ሕግ በህወሓት ባልሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ሥጋት፥ ፍርሃትና ጭንቀት መፍጠሩ ተሰማ።

ረቂቅ ሕጉን ገና ከአወጣጡ ጀምሮ ሲከታተሉና ግብዓት ሲሰጡ የቆዩ ወገኖች እንደሚሉት ይህ ያሁኑ ረቂቅ ሕግ የህወሓት ሰዎች አንገት ላይ ገመዱን ያስገባ ነው። ኢትዮጵያውያንን በመግደል፥ በማሰቃየትና በማንኛውም መልኩ የሰብዓዊ መብቶቻቸውን በመርገጥ ስማቸው የሚገኝ የህወሓት ሹሞችና ተባባሪዎቻቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት ከገንዘብ ሚ/ር መ/ቤት ጋር በመተባበር በዓለምአቀፍ ሕግጋት በተደነገገው መሠረት ዕቀባ እንዲያደርግባቸው ረቂቅ ሕጉ ያዛል። ይህ ማለት በሌላ አነጋገር ህወሓት/ኢህአዴግ ለዚህ የአሜሪካ የለውጥ ዕቅድ የማይገዛ ከሆነ የህወሓት ሹሞችና ቤተሰቦቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ማዕቀብ ይጣልባቸዋል፥ ሃብታቸው እንዳይነቃነቅ ይደረጋል። የአሜሪካንን ፈለግ የሚከተለውና ከህወሓት ጋር የላላ ወዳጅነት ያለው የአውሮጳ ኅብረትም ተመሳሳይ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ያሁኑ ረቂቅ ሕግ በአሜሪካ ምክርቤት በሚገኙት ሁለቱም ፓርቲዎች ሙሉ ድጋፍ ያገኘ በመሆኑ ሊታጠፍ እንደማይችልና የወትዋቾች (ሎቢይስቶች) ድለላ የማይበግረው እንደሆነ ተነግሯል።

የህወሃት/ኢህአዴግ ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ከሒዝቦላና ሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ጋር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አገኘ (July 27, 2017 08:43 pm)

የህወሃት/ኢህአዴግን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድርን የሚወቅስ የህግ ረቂቅ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መምሪያ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ በሙሉ ስምምነት አልፏል። ከውሳኔው በላይ የአሜሪካ ወዳጅ በመሆን ሕዝብን ለመከራና ስቃይ ሲዳርግ የኖረው የኢህአዴግ አገዛዝ በአሻባሪነቱ ከሚወገዘው ሒዝቦላ እና ከሰሜን ኮሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ጋር በእኩል ቀርቦ መታየቱ “የአሜሪካና ኢህአዴግ ወዳጅነት ወዴት?” አስብሏል፡፡

መለስ በG-20 ስብሰባ
በዕለቱ ዘጠን አጀንዳዎች ለውሳኔ የቀረቡ ሲሆን የኢትዮጵያን ጉዳይ ጨምሮ የአውሮጳ ህብረት ሒዝቦላን አሸባሪ ድርጅት በማለት እንዲጠራው፤ የሰሜን ኮሪያን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ ከዚህ በፊት የወጣው እንደገና እንዲተገበር፤ ኬኒያ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዳታካሂድ፣ በቬኒዙዌላ ያለውን የሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውስ የሚኮንን ረቂቅ ሕግ አቅርቦ ከማስወሰንና ከሌሎች አጀንዳዎች ጋር የቀረበ ነበር፡፡ (የስብሰባውን ሙሉ ውይይትና ውሳኔ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ)
ለምዕራባዊ ጌቶቹ በተለማማጭነትና በታዛዥነት የሚታወቀው መለስ አለቆቹ ያሉትን በመፈጸም አስፈላጊ ሲሆንም ከተጠየቀው በላይ በመሄድ ለመወደድ ያደርግ የነበረውን የአሁኖቹ የህወሓት አመራሮች ሊከውኑት ያልተቻለ ተግባር ሆኖ በተደጋጋሚ የታየ ሆኗል፡፡ በምዕራባዊ አገራት ሎሌነቱን በገሃድ ያስመሰከረው መለስ አገር ውስጥ “አሜሪካ አትረዳንም፤ የሰጡን ኮንዶም ነው፤ ሶማሊያ በኮንዶም አንዋጋም” እያለ በጠብመንጃ የሚገዛው ሕዝብ ላይ ሲደነፋ ቢኖርም ሃቁ ግን ኢህአዴግ አልሻባብን እዋጋለሁ እያለ ሲምታታ የኖረበት ዘመን ማለቁ ነው፡፡
ለዓመታት የህወሓት ቀንደኛ ተቃዋሚ በመሆን የሰላ ትችቶችን በአደባባይ በማድረግ የሚታወቁት የኒው ጀርዚው እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ዛሬም ኢህአዴግን አብጠልጥለውታል፡፡ በኢትዮጵያ “እየደረሱ ያሉት የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም” በማለት ኢህአዴግም ሆነ ሰሚዎቹ ሊክዱት በማይችሉበት ሁኔታ ማስረጃዎችን እየጠቀሱ ተናግረዋል፡፡
ከኦባማ አስተዳደር የሥልጣን ማብቃት ጋር ተያይዞ በወያኔነት ሲያገለግሉ የቆዩና በአሜሪካ ከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ላይ የነበሩ “ነጭ ወያኔዎች”መልቀቅ ህወሓትን እጅግ በርካታ ገንዘብ የሚያፈስበት የሎቢ (ውትወታ) “ፕሮጀክት” ውስጥ አስገብቶታል፡፡ ይህንኑ ውትወታ አልፎ “H. Res. 128Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia.” በሚል ርዕስ በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ረቂቅ ሕግ ለህወሓት ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኖ እንሚቀጥልበት ይነገራል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ አሜሪካንን በተደጋጋሚ የጉዞ ማዕቀቧንእንድታነሳ ጠይቆ ፈቃደኛ ሳትሆን መቅረቷ የተቃዋሚው ጎራ አለመተባበርና አለመዘጋጀት ነው እንጂ አሜሪካንን ከኢህአዴግ ጋር ለማቆራረጥ ጊዜው አሁን ነው የሚሉ ወገኖችን አመለካከት ያጎላ ሆኗል፡፡
በኦባማ አስተዳደር ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው የነበሩት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የዴሞክራሲ፣ የሠብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሊኖውስኪ በወቅቱ የተናገሩትን አስመልክቶ ጎልጉል ይህንን ዘግቦ ነበር፡፡

ፎቶ: የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊ የUSAID በኢትዮጵያ ሃላፊ ጌይል ስሚዝ (በመኪናው ላይ የሚታየው ምህጻረ ቃል “ማረት” – ማኅበረ ረድኤት ትግራይ) – Photo: David Kahrmann USAID Ethiopia)
ወይንም ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ በሚወሰድ እርምጃም ሊሆን አይገባም፤ ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሥልጣን ማስረከብ ደረጃ ሊደረስ ይችላል፡፡” ሲቀጥሉም “እንደ ወዳጅ መክረናል … ምክንያቱም … ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ቢፈጠር ሙሉ ምስራቅ አፍሪቃ ምን ሊከተል እንደሚችል ስለምናውቅ … ነው” ካሉ በኋላ አገሪቱን እሳት ላይ ተቀምጦ እንደሚንተከተክ ማሰሮ የመሰሉትና ማስሮው እንዳይገነፍል ብቸኛው አማራጭ ክዳኑን መክፈት እንደሆነ ያመለክቱት ቶም ማሊኖውስኪ፣ “ተስፋ አለን ይሰሙናል፣ መልካም ነገር እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡ ይህንን ማስጠንቀቂ በማሳያነት የሚጠቅሱ ክፍሎች ተቃዋሚው ጎራና ኢህአዴግ ተያይዘው ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲገቡ አሜሪካ አሁን ላይ የደረሰችበት እምነት ነው። ለዚህም ይመስላል ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠችው ይላሉ። ሌሎች ግን አሜሪካ ምንም የምታመጣው ነገር የለም፤ ብታመጣ ኖሮ እስከዛሬ አትቆይም ነበር፤ ይህ ተራ የፖለቲካ ጫወታ ነው ሲሉ የአሜሪካንን አካሄድ ያጣጥላሉ፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ “በአሻባሪነት” ስም በሶማሊ የሚያደርገው ማስፈራሪያ ጊዜው ያለፈበት ይመስላል፡፡ የህወሃትና የአልሸባብ ግንኙነት እንዳለ ሆኖ አሸባሪነትን ለመዋጋት በሚል አርባ ምንጭ የሰው-አልባ አሮፕላን ማረፊያ (ድሮን ቤዝ) ማቋቋም ደርሳ የነበረችው አሜሪካ ፕሮጀክቷን ያጠናቀቀች ይመስላል፡፡ “ሶማሊያ ውስጥ … በኮንዶም አንዋጋም!” እያለ የሚያምታታ መለስ የሌለው ህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮውን ብቻ ሳይሆን ከበረሃ ጀምሮ ሲያግዙት የነበሩትን “ነጭ ወያኔዎችም” እያጣ ነው፡፡
ዛሬ በረቂቅ ህግነት በሙሉ ድምጽ ያለፈው አዋጅ ወደ እንደራሴዎች ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ ማጽደቁ ለእንደራሴዎቹ ምክርቤት የድጋፍ ድምጽ መስጠት በር ከፋች ነው ብለዋል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያቀናበረው የምስል ዘገባ ከዚህ በታች ይገኛል፡
http://www.goolgule.com/hr-128-a-threat-to-tplf-and-their-cronies/

No comments:

Post a Comment