Translate

Wednesday, July 19, 2017

ሆለታ ዝግ ሆና ዋለች – ወሊሶ ለ3ኛ ቀን ሥራ ማቆም አድማው ቀጥሏል * ተሳፋሪዎች ከአዲስ አበባ ወደ ወለጋና ሰሜን ሸዋ ለመሄድ ተቸግረዋል



(ዘ-ሐበሻ) አላግባብ ግብር ተጭኖብናል በሚል በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ “ግብር አንከፍልም” የሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው:: ዛሬ በሆለታ ከተማንግድ እና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ቆመው የዋሉ ሲሆን የመንግስት ኃይሎች በግድ ለማስከፈት ቢጥሩም እንዳልተሳካላቸው ለማወቅ ተችሏል::

በወሊሶ ከተማም ለሶስተኛ ቀን የቀጠለው የነጋዴዎች የሥራ ማቆም አድማ ዛሬም በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል:: እንደ ዜና ምንጮች ገለጻ በወሊሶ የመንግስት ተላላኪዎች ሕዝቡን ሰብስበው “ግብር በዛብን የምትሉ ለየብቻ እየመጣችሁ አነጋግሩን” በማለት ነጋዴዎችን ለማረጋጋት ቢሞክሩም ለየብቻ አነጋግሩን ያሉት መርጠው ሕዝብን ለማሰር መሆኑን የተገነዘቡ ነጋዴዎች አይሆንም ብለዋል::
በሌላ በኩል ከአዲስ አበባ ወደ ወለጋ እና ወደ ሰሜን ሸዋ ለመሄድ የመጓጓዣ ችግር እንዳለ ተገለጸ:: የክፍለሃገር ሹፌሮች ሥራ በማቆማቸው የተነሳ ወደ ሰሜን ሸዋ እና ወለጋ ለመሄድ ትኬት ቆርጠው የተቀመጡ ወገኖች ወደሚፈልጉበት ቦታ ለመሄድ እንዳልቻሉና 3ኛ ቀናቸውን እንዳስቆጠሩ ከመዲናዋ የተገኙ መረጃዎች ይናገራሉ:: የመንግስት ባለስልጣናት እና ሚድያዎቻቸው ምንም ዓይነት የትራንስፖርት እጥረት እንደሌለ እየሰበኩበት ባለበት በዚህ ወቅት ሕዝቡ እየተጉላላ ይገኛል::
መንግስት ከአቅም በላይ የጨመረውን ግብር ካላነሳ ሕዝባዊው አመጽ እየተቀጣጠለ እንደሚሄድ ከየሥፍራው ለዘ-ሐበሻ ከሚደርሱ መረጃዎች ለመረዳት ችለናል::

No comments:

Post a Comment