Translate

Monday, July 17, 2017

የዘፋኞች “እንጀራ” ከነእስክንድር ነጋ “እንጀራ” በላይ ነው

በጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ (ከፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)
Ethiopian artists and the repressive regime (TPLF)
  • ቦይኮቱ አስቴርና ጎሳዬን ሲነካ ደርሶ ድንገት የዘፋኝ መብት ተቆርቋሪ ለሆናችሁ
  • ዘፋኞች የገዢው ስርዓት ድግሶችን ቢያደምቁ በንዴት “እቀባ አታድርጉባቸው:: እንጀራቸው ሆኖ እንጂ ሕዝቡን ይወዱታል:: የት ሄደው ይዝፈኑ?” ለምትሉ
  • ተራ ሕዝብንና ታዋቂ ዘፋኝን ለምታነጻጽሩ
  • በሕዝብ ላይ በሚያሳድሩት የስነልቡና ተጽእኖ ለጨቋኙ ስርዓት የፕሮፖጋንዳ ሽያጭ የሚሰጡት የበላይነት ላልገባችሁ
  • ከኮንሰርት በሚገኙ ገቢዎች ህወሓት እንዴት የገንዘብ ጡንቻውን እንደሚያፈረጥም ያልተረዳችሁ ወይም ግድ ያልሰጣችሁ
  • አርቲስቶች ፈጽሞ አትዝፈኑ እንደተባሉና የአድማ ጥሪው የዘፋኝ ዳቦን ለማጥፋት የሚደረግ ለማስመሰል የምትሞክሩ
  • ዘፋኞቹ ከህወሓት ኢህአዴግ ድግስ ውጪ በሌላ መንገድ ፈጽሞ ገቢ ማግኘት የማይችሉ ዓይነት አድርጋችሁ ለመሳል ለምትታትሩ
  • “የቦይኮት ስትራቴጂ ድክመት አለው፥ እንዴት፥ በምን መልኩ እንዲሻሻል መረዳት እችላለሁ” ከማለት ይልቅ የግል ሕይወታቸው ሳያሳሳቸው ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚጥሩ ወጣቶች ላይ ድንጋይ መወርወርን ለተካናችሁበት የተቃዋሚ ተቃዋሚዎች
  • ዘፋኞች የፈለግሁበት አዘፍናለሁ ማለት መብታቸው እንደሆነ ሁሉ አክቲቪስቱ boycott፥ ዳያስፖራው ግንዛቤን እምቢኝ ማለት መብታቸው እንደሆነ ለጠፋችሁ”Boycott” ሰላማዊ የእቀባ ጥሪ ወይም ልመና እንደሆነ መርዳት ተስኗችሁ ቦይኮትን ከወያኔ ጥይት በላይ ለምታወግዙ… ምጡቅ አተረጓጎም ተጠቅመን ቦይኮትን እንደሚከተለው እናወግዛለን፣
1. ፌደራል ፖሊሶች ወይም አጋዚዎች ቢያስሩ ቢደበድቡ አልፎ አልፎ ቢገድሉ አትፍረዱባቸው:: እንጀራቸው ሆኖ እንጂ ጨካኝ ሆነው ተፈጥረው አይደለም:: ልጆቻቸውን ሌሎች ቤተሰቦቻቸውን በምን ያኑሩ?
በዚያ ላይ ሁሉንም የሚያደርጉት ታዘው እንጂ ፈልገው አይደለም::
እነሱም እንደኛ የሕዝቡ አካል ስለሆኑ እባካችሁ አትጥሏቸው::
ብዙዎቹ ካሰሩ ከገደሉ በኋላ በጸጸት ፊታቸውን ማንም እንዳያያቸው በካኪ ዩኒፎርማቸው ሸፍነው ስቅስቅ ብለው ያለቅሳሉ።
2. ታዋቂ ሰዎችና ባለሃብቶች ….ኃይሌ፥ ቀነኒሳ… ከኢህአዴግ ጋር ቢሰሩ ቢተባበሩ አትርገሟቸው::
ይህን ባያደርጉ ሀበታቸውን ንግዳቸውን ሊያጡ ይችላሉ:: ቤተሰብ አላቸው… እንጀራቸውን ማጣት የለባቸውም::
እውነቱ እኮ ያለው ልባቸው ውስጥ ነው ሕዝቡን ይወዱታል
3. ብዙኅኑ ትግሬ ህወሓት በምንም መልኩ በመንግስትነት እንዲቀጥል ቢፈልጉ አታውግዟቸው:: ወደው እኮ አይደለም:: ይህን ባያደርጉ በዘዴ የማህበረሰብ መገለል ይደረግባቸዋል::
4. ህገወጥ ቤቶችን የሚያፈርሱ አፍራሽ ግብረኃይሎች የሕዝቡን ቤት በላዩ ላይ የሚንዱት መንግስት አዟቸው እንጂ ወደው-ፈቅደው አይደለም:: የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው ነው::ካፈረሱ በኋላ ተጸጽተው ቤተስኪያን ሄደው ንስሐ ይገባሉ::
5. አሁን ማን ይሙት ይሄ ሁሉ የቀበሌና ወረዳ ሹመኛ በመንግሥት ባይታዘዝ በገዛ ፈቃዱ የገዛ ወገኑ ላይ ይጨክናል? የእንጀራ ጉዳይ ባይሆን ሲያልፍም አይነካካው!
በመጨረሻም:-
ሕዝቡ ለወያኔ ቢገዛ ወዶ አይደለም ምን ያድርግ? ደኸነት ክፉ ደዌ የማያሳየው አበሳ የለም::
ፀጥ-ለጥ ብሎ ቢገዛ የደኸ ነፍሱን ለማዳን ከዚያም የዕለት እንጀራውን ለማግኘት ብሎ ነው::
እና ከላይ በተዘረዘሩት አተረጓጎሞች መሰረት የለውጥ እንቅስቃሴን ለፓለተከኛ ትተነዋል:: ግዴታው የነሱ ነው::
እነ እስክንድር፥ ተመስገን፥ ውብሸት፥ ዳርሴማ ሶሪ፥ ኤሊያስ ገብሩ…
እነ ኮሎኔል ደመቀ፥ በቀለ ገርባ፥ ዶክተር መረራ፥ እማዋይሽ፥ ንግስት ይርጋ… ቤተሰብና እንጀራ የላቸውም::

No comments:

Post a Comment