Translate

Wednesday, August 8, 2012

ብታምኑም ባታምኑም፤ ፌስ ቡክን በመጠቀማቸው ሰራተኞች ሃርድ እየተሰጣቸው ከስራም እየተባረሩ ነው!


አቤ ቶኪቻው
ከዚህ በፊት በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥኔ ውስጥ አንድ ወዳጄ አላባ አካባቢ ወደ ሶስት የሚጠጉ የመንግስት ሰራተኞች በፌስ ቡክ ላይ ፖለቲካ ነክ ፅሁፍ ለጥፋችኋል ተብለው ከስራ መባረራቸውን ነገሮኝ ነበር። እኔ ግን ይሄንን ነገር ከራሳቸው ከተባራሪዎቹ ሰዎች ካልሰማው በስተቀር የመንግስቴን ስም “በከንቱ” አላጎድፍም ብዬ ስልካቸውን እንዲልክልኝ ጠየኩት። (እንዴት ያለሁ ልማታዊ ወገኛ እንደሆንኩ ብቻ ግራ ቀኝ ልብ አድርጉልኝ!) ልጁ ግን ስልካቸውን ፈልጌ ልክልሃለሁ ብሎኝ ሳይልክልኝ ቀረ። እኔም ያንን ወሬ አላወራም ብዬ ፀጥ አልኩ።ብታምኑም ባታምኑም፤ ፌስ ቡክን በመጠቀማቸው ሰራተኞች ሃርድ እየተሰጣቸው ከስራም እየተባረሩ ነው!
ነገር ግን በሌላም ግዜ በተደጋጋሚ የተለያዩ ወደጆቼ “በፌስ ቡክ ግድግዳችሁ ላይ ፖለቲካ ፖልትካችኋል” እየተባሉ ከአለቆቻቸው ዘንድ ግሳፄ እየተሰጣቸው መሆኑን ስሰማ ይሄ ነገር ሁሉም ዘንድ ነው ማለት ነው… ብዬ በማንሰላሰል ላይ ሳለለሁ፤
አንዱ ወዳጄ ደግሞ ከምስራቅ የኢትዮጵያችን ክፍል ከአንዱ ወረዳ ሌላ መልዕክት ሰደደልኝ።

ይህ ወዳጃችን በወረዳው ውስጥ በአንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት “ICT” ኤክስፐርት የስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። በመስሪያ ቤቱ የሚገኙ በርካታ ወዳጆችን ወደ ፌስ ቡክ ሰፈር እንዲቀላቀሉ አድርጓል። ራሱም አዘውትሮ ፌስ ቡኩን ይጠቀማል።
ይህ ተግባሩ ግን በመስሪያ ቤት አለቆቹ ዘንድ አልተወደደለትም። ምን አለመወደድ ብቻ ከስራውም እንዲፈናቀል ምክንያት ሆነው እንጂ…! እኔማ ምናልባት በፌስ ቡክ ላይ ብዙ ጊዜህን እያጠፋህ የመንግስትን የስራ ሰዓት በድለህ ይሆን…!? ብዬ ጠይቄው ነበር… እርሱቴ… ከትርፍ ሰዓቱ ውጪ የግል ጉዳዩን ንክች አያደርግም። ይልቅስ “በዋናነት ከስራ ለመባረሬ ምክንያት ለአብዛኛው የመስሪያ ቤት ሰዎች ፌስ ቡክን በማስተዋወቄ ነው!” ብሎኛል።
ይህንን ወሬ የነገረኝ ወዳጄ ብታምንም ባታምንም ብሎ ነው። እኔም “ብታምኑም ባታምኑም…” ብዬ አካፈልኳችሁ!
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም “ከፌስ ቡክ ነፃ የሆነ ማኅበረሰብ እንፍጠር” አይነት ስብከት መስማት ከጀመርን ቆይተናል።

No comments:

Post a Comment