Translate

Tuesday, July 31, 2012

የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄያችንና ያንበሳ ድርሻ የሆነው ቀረጥ።

በአሁኑ ሰአት ስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛና አንበገነናዊ ስረአት ለማስወግድ እየተደረገ ባለው ትግል ጠንካራ የለውጥ ሀይል ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ክፍሎችን ሁለንተናዊ አቅም ደረጃ እንስጥ ቢባል ከተቃዋሚ ድርጅቶች ቀጥሎ የመምሀራን ሁለንተናዊ ጥንካሬ በአምስተኛ ደረጃ የሚመጣ ይመስለኛል። መምህሩ የሰራተኛው መደብ አካል ነው። በአንድ ደምረን ከወሰድነው ደረጃችን ወደ አራትተኛ ከፊ ሊልም ይችላል።

በእሰካሁኑ ታሪካችን እንዳየነው ለነጻነት፤ ለእኩልነት፤ ለፈትህ በተደርጉ ትግሎች ሁሉ የመምህራን የትግል አስተዋጾ ከፍተኛ ስፍራ ያለው ነው። የትግል ታሪካችን ለውጥ አብሳሪና አብሪም ነው።
ትግላችን ዛሬም እንደቀጠለ ነው። በቅርብ በዋናነት የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄን ይዘን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አድርገን ነበር። ተቃውሞው በጥቂት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስራ እስከማቆም የደረሰ ጉልበት ነበረው። በርግጥ የዚህ ዙር የስካሁኑ ትግል ከቀድሞ የመምህራን የትግል ታሪክ ጋር ስናስተያየው ብዙዎችን ያሳተፈና ተጽኖ ማድረግ የቻለ ነበር ለማለት አያስደፍርም። ጅማሮ ነው።
እንደተለመደው በአነሳነው የመብት ጥያቄ ምክንያት የወያኔ ድላ አርፎብናል። ተቃውሟችሗል ተብለው ከስራ የተባረሩ ባልደረባዎቻችን አሉ። ይዘነው የተነሳነው ጥያቄ ገና መልስ አላገኘም። ስለዚህም ተቃውሞችን ቀጣይ መሆን አለበት። ትግሉን አጠንክሮ በቀጣይ ለማካሄድ ያለውን ጠቅላላ ያገራችንን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና የጊዜውን የፖለቲካ ሁኔታ አስተውሎ ማንም ጥሩ አሳቢ በቀጣይ ጠንካራ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ማድረጊያው ጊዜ አሁን መሆኑንና በርግጠኛነት መናገር ይቻለዋል። እኔም አሁን ነው ትግላችንን ማፋፋም ያለበን የሚል እምነቱ አለኝ።
ያም ሆኖ ሁላችንም እንደምናውቀው የብዙሀኑን ጥያቄ ይዞ ያልተነሳና እንቅስቃሴውን ከሌሎች የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ጋር ማቀናጀት ያልቻለ ማንኛወም አይነት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጥያቄዎቹን ለማስመለስና ለውጥን ለማምጣት ያለው እድል አናሳ ነው። በዛ ላይ ስልጣን ላይ ያለው ብድን ጠንካራ የተባበረ ጉልበት ካላረፈበት በቀላሉ ለህዝብ ፍለጎት የሚገዛ አልነበረም። እንኳን ለከባባድ የመብት ጉዳዮች ጥቃቅን የሆኑ የዜጎች ጥያቄዎችንም የመመለስ ፍላጎት በፍጹም አልነበረውም። እኛም ለሀያ አንድ አመት አቅብጠንዋል።
የደሞዝ ጭማሬው በቂ አይደለም የሚለው ጥያቄ መምህራን እናንሳው እንጂ የሰራተኛው ክፍል ሁሉ ጥያቄ ነው። የዋጋ ግሽበት አሁን በአለበት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ አይደለም ከድሮውም በቂ ደሞዝ ለማይከፈለው ለበዛው የሰራተኛ መደብ ኑሮ ከጅ ወደአፍ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ ደሞዝ ተካፋይ ለሆነው አይደለም በተለምዶ ሀብታም የምንላቸውና በብዙ ሺዎች የሚከፈላቸውም ዜጎች መኖር አልቻልንም እያሉ እያማረሩ ያሉበት ጊዜ ላይ ነን።
የዋጋ ግሽበቱ በቶሎ በከፍተኛ መጠን የማይቀንስ ካልሆነ። በቅርብ ይቀንሳል ብሎ ማሰብ በጭራሽ አይችልም። ስለዚህ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄው በሁሉም ሰራተኛ ዘንድ ጥያቄ መሆኑ አይቀርም። አግባብ ያለው የመታገያ ጥያቄም ሆኖ ይቀጥላል። ጥያቄው ተመላሽ እንዲሆን ግን በአጠቃላይ የሰራተኛ ክፍል ጥያቄ ሆኖ መስተጋባት በቶሎ አለበት።
እኛ ጥያቄውን ማንሳት ሲደክመን፤ የመብራት ሀይል ሰራተኞች፤ እነሱ ሲደክሙ የአየር መንገድ ሰራተኞች ወይ የሻኪሶ የወርቅ መአድን ሰራተኞች የሚያነሱት ከሆነ እስካሁኑ መለስ ዜናዊ ወደፊት በሱ ቦታ ሊሰየሙ የሚያኮበኩቡት ፓርላማውን እየሰበሰቡ ዘራፍ እንዴት ተደፈርኩ። ምን ሲደረግ ነው የተጠየቅነው እያሉ ቢፎክር መገረም የለብንም።
ሁላችንም እንደምንገነዘበው ጠንካራ በሆነው አፈና ምክንያት ተቃውሞውን ያነሳሱት መምህራን አቃቂ ሰራተኞችን ጨምረው ለትግል ለማንቀሳቀስ አይደለም የበዛውን መምህራን በጋራ ለማሰለፍ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው እይተናል። በርግጥም የተባበረ ጠንካራ ተቃውሞ ለማድረግ ብዙ ችግሮች ነበሩብን። ትግሉ ላይ የፈለገውን አይነት ችግሮች ይኑሩ የምናነሳቸው የመብት ጥያቄዎች መመለስ ግን አለባቸው። መልስ ማግኘት የሚቻለው ደግሞ ይህ የበሰበሰ ዘረኛ አንባ ገነን መንግስት በመገርሰስና ለህዝብ ፍላጎትና መብት መከበር ፍላጎት ባለው፤ ለማዳመጥ ጆሮና ትእግስቱ ባለው ህዝባዊ መንግስት መቀየር ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ በድጋሚ ከዚህ ጊዜ የተሻለ መልካም አጋጣሚ ሊፈጠር አይችልም።
እንደምናውቀው በአገሪቷ ውስጥ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ወይ የጋራ የመብት ጥያቄዎች መኖራቸው ብቻ በጋራ መብትን ጠይቆ ለማስመለስ እስካሁን በሞከርነው መንገድ አላስቻሉንም ። ስለዚህም ጠቅላላ ያተጋገላችን መንገድ መቀየር ይፈለግብናል። ላንባገነናችንና ላፈናው የሚመጥን አዲስ አይነት የትግል አይነት፤ አደረጃጀት፤ አፈጻፀምና አስተሳሰብ ማሰላሰል በቶሎ አለብን። ከአርስቱ በዙ እንዳያወጣኝ እዚህ ቁም ነገር ላይ ወደፊት ልመለስበት።
እዚህ ትግል ላይ ያለብን ትልቁ ችግር አፈናው ነው። ችግራችንና ጥያቄዎቻችን ላያ በጋራ መምከርና በጋራ መፈትሄው ላይ ለመቆም በጭራሽ አላስቻለንም። ስለዚህም እዚህ ላይ ለዛሬ አንድ መፍትሄ ሊሆን የሚችል ሀይለ ሀሳብ ብቻ አነሳለው።
መፍትሄው መናበብ፤ መናበብ፤ መናበብ ነው። ቁጭ ብለን ሳንመክር መስማማት። ሳንነጋገር በጋራ ማቀድን። ሳንወያይ በአንድ መቆምን ሳንጠራ መተጋገዝን ልንካንበት ይገባል
እስከዛሬም በማወቅ አላደረግነው ይሆናል እንጂ ታሪካችንን ወደሗላ ስናየው ይህ ችሎታ እንደ ኢትዮጵያው የተካንበት ነው። ከቅርብ ጊዜው ታሪካችን ጀምረን ዋና ዋና የሆኑትን የህዝባዊ ትግል ታሪኮቻችንን ብናይ ምርጫ 97፤ የሱማሌ ጦርነት፤ 1966 የለውጥ እንቅስቃሴ፤ ያደዋ ጦርነት እንዴት አሸነፍናቸው እንዴት ያን ያህል ቁጥር ያለው ዜጋ ማሳተፍ ተቻለ የሚለው ጥያቄ? ። መልስ የሌለው አይነት ሆኖ ነው በኛም በውጪም ጸሀፊዎች ክፍት የሚተወው።
በድጋሚ የዚህ ጽሁፍ አላማ እንዴት ነው በዚህ አፈና ውስጥ ትግሉን ማስተባበር ወይ በጋራ መስነሳት የሚቻለው ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት አይደለም። አነሳሴ ከኛ የደሞዚ ጭማሪ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ሰራተኛው ክፍል እንዲሁም ዜጋው ሁሉ ሊጋራው ስለሚችል አግባብነት ስላለው ጥያቄ ለማንሳት ነው። ዞሮ ዘሮ የጋራ የሆነው ጥያቄ ይቀድማል። ያስፈልገናልም።
ሌላኛው መምህራኑን ጨምሮ የመላው ሰርቶ አደርና ዜጋ ጥያቄ ሆኖ መውጣቱ የማይቀረው ተያያዥም የሆነው ጉዳይ የወያኔው መንግስት እስከዛሬ በታክስ ስም የሚዘርፈን ገንዘብ ነው። ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ ዜጋው ለፍቶ ካስገባው ላይ የሚወሰድበት ነው። በቀረጥ ስም የሚመዘብሩት ገንዘብ ከደሞዝ ጭማሪው ጥያቄ ጋር በቀጥታ የሚያዛመደው ጉዳይ ሁለቱም የሰራተኛውን በጠቅላላው የዜጋውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አስፈላጊም ወሳኝም ስለሆኑ ነው።
የወያኔው ዘረኛ መንግስት በአማካኝ ዜጋው ሰርቶ ካገኘው 30% ቱን ከገቢያችን ይወስድብናል። 15% ብሩ እጃችን ሳይገባ ቀድሞ በተለያየ ቀረጥ ስም ከደሞዛችን ላይ ካዝናቸው የሚያስገቡት ነው። (አሳይተው የሚነሱን) ተርፎ በጃችን ከገባው ደሞዛችን ለኑሮ የሚያስፈልገንን ሸቀጥና አገልግሎት በገዛን ቁጥር ቫት ብለው በሰየሙት ሌላ አይነት ቀረጥ ከዜጎች ሁሉ ተጨማሪ 15% ይዘርፉናል። በድምሩ 30% መሆኑ ነው። ይህ እንግዲህ ከየትኛውም የመንግስት ቢሮ አገልግሎት ስንጠይቅ የሚያስከፍሉንን ከፍትኛ መጠን ያለው በጭራሽ ላገልግሎቱ የማይመጥን የገንዘብ መጠን ሳንደምር ነው። እንዲሁ በየጊዜው በተለያየ መዝረፊያ ሰበብ እየታሰበ ያንድ ወር ደሞዛችሁን ስጡ እየተባለ የምንቀማውን ሳይጨምር ነው።
ላንድ ሰርቶ አዳሪ ወይ ኢትዮጵያያዊ ዜጋ ከገቢው 30% የሚሆነውን ለመንግስት መስጠት በጣም በጣም የሚከብድ ነው። በጣምም ብዙ የሆነ የገንዘብ መጠን ነው። ባዛ ላይ ከገቢያችን 30% የሚጠጋው የሚወሰድብን ገንዘብ የመግዛት አቅም ዜሮ በገባበትና የኑሩ ውድነት ሰማይ በነካበት አገር ውስጥ እየኖርን ነው።
በያንዳንዳንዱ ቤት ችግሩ የከፋው፤ ደሞዝ አልብቃቃና ከወር ወር አላደርስ ያለበት ምክንያት ሌላ ምንም አይደልም እስካሁን የወያኔው መንግስት ሰርተን ካገኘነው የሚወስድብን የገንዘዘብ መጠን ከመጠን በላይ በመብዛቱ ነው።
በአሁኗ ሰአት የራቧችሁ ዜጎች ሁሉ፤ ለልጅሽ ወተት መከራየት አቅቶሽ ጥራጥሬ ደባለቀሽ አስፈጭተሽ የምታጠጪ እናት፤በቀን ሶስቴ መመገብ አቅቷችሁ በቁምሳ ህግ ሁለቴ ወይ አንዴ የምትበሉ ዜጎች፤ በርበሬ መግዛት ተስኗችሁ አልጫ ሽሮ ከወር ወር የምትመገቡ ቤተሰቦች፤ልጆቻችሁን ማስተማርና ማልበስ ያቃታችሁ ወላጆች፤ በመኖሪያ ቤት እጦት የምትሰቃዩ ዜጎች በአጠቃላይ ሰርታችሁ ኑሮ አልሞላ ያላችሁ ዜጎች ለሌላ ለምንም አይደለም አዜብ ፤ በረክት፤ መለስ አርከበ አባድላ የሚባሉ ሰላቢዎች ኪሳችንና ቤታችን ስለገቡ ነው። ለፍተን ካገኘነው 30% ነው የሚቀሙን።
መድገም ያስፈልጋል 30% በጣም በጣም ብዙ ነው። ይህን ያህል ገንዘብ ልዩነት ሳያበጅ በጅምላ ከደሀ ዜጎቹ የሚወስድ መንግስት በአለም ላይ የለም። ካለም መንግስት መልሶ ለህዝብ የጋራ ጥቅምና ሰርተው ኑሮን ማሸነፍ ላቃታቸው መደጎሚያ የሚያውለው በጣም በጣም ብዙ ጥቅማጥቅሞችና ነጻ አገልግሎቶች መኖር አለባቸው።
ከሁሉ በፊት በአገራችን ውስጥ እየሰራን የሚርበን ባልነበርን። ምግብ እስከጭራሹ ችግር መሆን መቆም ነበረበት። ዜጎች ሁሉ ጥራት ያለው ነጻ ትምህርትና ህክምና ማግኘት ነበረባቸው። እነዚህን ዋናዎቹ ናቸው። እነዚህን እንኳ መንግስት ተብዬው ዘረኛ አንባገነን ያለችግር መሸፈን ነበረበት። በተገላቢጦሽ ወያኔዎች የነገሱባት አገር ዝነኛ የሆነችው በነዚሁ ችግሮች ነው።ታዲያ ገንዘባችንን የት እየከተቱት ነው?።
የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ዜሮ ገብተዋል። ውሃ በፈረቃ ፤መብራት በፈረቃ፤ ትምህርት ቤት በፈረቃ፤ በአጠቃላይ ኑሮ በፈረቃ፤ የሆነባት አገር ነች ያለችን። ጉዞ በኮረኮንች፤ ህክምና በወረፋ፤ ጥያቄውን እደግመዋለው ታዲያ ያ ሁሉ የሚወስዱብን ገንዘብ የት ሄደ?። ከ80 ቢሊዮን ህዝብ 30% በጣም ብዙ ነው። በቀላሉ መልስ የማይገኝለት ጥያቄ ነው።
ወያኔዎች በታክስ ስም የሚዘርፉን የገንዘብ ጉዳይ ከዚህም አልፎ ወደ ሁለት አለማቀፋዊ ባህሪ ወዳላቸው በሌላው አገር ወደ ተለመዱ ሁለት ታላላቅ ጥያቄዎችና መታገያ መፈክሮችን እንድናነሳ የሚያደርገን መሰሎ ይታየኛል።
  1. መንግስታዊ ቀረጥ ተአማኒ ከሆነ የህዝብ ውክልና ጋር።
  2. ቀረጥ ከተገቢ አገልግሎታ ጋር።
በድጋሚ መንግስታዊ ቀረጥ ተአማኒ ከሆነ የህዝብ ውክልና ጋር። መንግስታዊ ቀረጥ ከተገቢ አገልግሎት ጋር። ከገቢያችን 30% እጅግ በጣም ብዙ ነው። የደሞዝ ጭማሪ ከቀረጥ ቅነሳ ጋር። የደሞዝ ጭማሪ የዋጋ ግሽበቱን መቆጣጠር ከመቻል ጋር።
ደንፎ ነኝ ከአዋሳ። Monday, July 23, 2012
denfo.dd46@gmail.com

No comments:

Post a Comment