Translate

Monday, July 30, 2012

አቶ ለገሰ እውን እረፍት ላይ ናቸው?

ከብርሃኑ ተስፋዬ Chillalo@gmail.com
እረፍት ላይ ናቸው በያቅጣጫው ይነገራል ሁለቱም ቡችሎቻቸው ካገር ዉስጠም ሆነ ከውጭ ሃገር ሲያብራሩልን የሀኪም እነደሆን ረገጥ እያደረጉት ነው ሆኖም ወደ ስራ መመለሻቸውን ጊዜ ደግሞ በውል አያዉቁትም ያሉበትንም ቦታም ለደህንነታቸው ሲባል መግለጽ አስፈላጊ አይደለም ብለው ይዘጉታል
ይህ አገላለጽ ሁለት ነገሮችን እንዳሰላስል ያደርገኛል በመሆኑም አንድም አቶ ለገሰ ራሳቸውን የተሸሸጉ የጦር ወንጀለኛ አሊያም ያሉበት አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ቢሄዱበት በባሀልEthiopia's longtime ruler Meles Zenawi is ill አስነዋሪ ቦታ እንዳሉ አንደምታ አለው ታዲያ ይህንን ሳስብ ምናልባት ሃኪም ቤት የገቡ ሳይሆን ጠንቁዋይ ቤት አቤት አቤት እያሉ የከዳሚነት ስራ ተሰጥቶዋቸው ይሆን ብየ አስባለሁ

መቸም ያደቆን ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም ይባላልና ከውጭ ሃገር እንደተመለሱ ሁለት ጋዜጦች ዘግበው ወሬ ሆኖ ቀርቶዋል ምናልባት ባለቤታቸውን ጭምር ደጅ ያስጠኑት ጠንቓይ ከቃሊቲ ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው ይሆን ወይስ ሌላኛው እረፍት አሳቸውም ላይ ደረሶ ይሆን ለማናቸውም እርፉ ከተባሉ መቆየቱን ለማሳየት ትንሽ የምለውን አንብቡ
ባሁኑ ወቅት ያለበትን እስር ቤት በውል ባላውቀም አንድ ወቅት መንግስት ጋዜጠኞችን ጋብዞ በአማራ ክልል ያለውን የልማት ሁኔታ ሲጎበኙ ውብሸት ታዬ ያነጋገራቸው ገበሬ ያሉትን በ1997 ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ ደክሞታልና እረፍት ስለሚያሰፈልገው አውቀን እንዲያርፍ በካርዳችን ብንነግረው አማራ ባፉ ከናንተ ጋር ነን እያለ በካርዱ አደባየን አለን ማለታቸውን ዘግቦልን ነበር ታዲያ ይህ አባባል ጥርስ ውስጥ አስገብቶት በበቀል የተካነው ያቶ ለገሰ መንግስት ለእስር ዳርጎት ፍዳውን እያየ ይገኛል ርእዮትም አነሳችው የተባለው መፈክር በቃ ማለት ድካም አለና እረፍት ይደረግ መልእከት ውጪ ሌላ ነገር ያዘለው የለም እስክንድርም ደጋግሞ የጻፈው አቶ ለገሰ ራስዎ ደክመው በጻፉትና ባጻፉት ህግ መሰረት ሲጸድቅም እስክሰታ መሳይ ተሊት የወረዱበትን ህግጋት ደረማመሰው ራሰዎ ህግ ሆነዋልና ወደ ህሊናዎ ይመለሱ (ህሊና ካለዎ) የባሰ ሁኔታ ተከስቶ ከቤናሊ እስከ ጋዳፊ እይነት ሁኔታ ከሚከሰት እረፍት ያስፈልጎታል መልእከት ነው
ለመድከማቸውም ማረጋገጫ 11.7 ቢሊዮን ዶላር ካገር መሸሹ 10 ሽህ ቶን ቡና አየር ላይ በኖ መቅረቱ ባሊስትራ ብረት ወርቅ ተብሎ ብሄራዊ ባንክ መገኘቱ ከሚጠቀሱት የጎሉት ሲሆኑ ራሳቸው የመንግሰት ሌቦች መኖራቸውን ማመንናቸው አፍንጫቸው ስር ያሉት ድልብ ቡችሎቻቸው በሃያ አመት ውስጥ በሚሊዮን የሚያወጡ ህንጻዎች መገንባታቸው አንዳንዶችንም እባካችሁ ለፓርቲህ ስጥ ብለው ለመደበቅ መሞከራቸው የቅርብ ጊዜ እውነታዎች ናቸው
ከእነዚህ ያገጠጡ እውነታዎች ባሻገር እረፍት እንዲያደርጉ የሚያሰገድዳቸው አንኩዋር ሁኔታዎች ግን በተለያዩ ጊዚያት በሲዳማ አኝዋክ አማራ ኦሮሞ ሶማሌና አዲሰ አበባ የፈጸሙዋቸው ጅምላ ጭፍጨፋዎችና የሀገሪቱን እስር ቤቶች በባነኑ ቁጥር ቅልብ ውሾችዎትን በመላክ የህዝብ ጉረኖ ማድረጋቸው ነው
እነዚህ ሁኔታዎች የምቀኛና ሙዋርተኛ አመለካከቶች እንጂ እኔን አይመለከቱም ብለው ሲመጻደቁ አበበ የሚባል ትንታግ ለሰላሳ ሴኮንድ እርቃናቸውን አሰቀርቶ ላለም ካጋለጠ ወር ባለሞላው ጊዜ ደብዛቸው ጠፍቶ ሰንበተው አሁን እረፍት ላይ እንደሆኑ አንዴ ካዲሳባ አንዴ ከዋሽንግተን መግለጫዎች እየተሰራጩ ነው
የህይወት ሩህያ ወሳኙ የማያመኑበት አምላክ ፈቃድ ስለሆነ ከሱም ጋር ሙግት አሰፈላጊም ስላለሆነ ያሉበትን ለሱ ትቼ መልካም እረፍት እያልኩ እንደባለቤታቸው እኛ ሰፈር መጥተው እንዳይፈወሱ እኛ ሁሉን አድናለሁ የሚሉትን እያንጉዋለለን ቃሊቲ ልከዋቸል ምናልባት እሳቸው ጋር ተደብቀው እየታከሙ ይሆን ወይስ ኦፕራሲዮን ማድረጋቸውም ሹክታ ስላለ ለመሆኑ አጃቢዎቻቸው ሁሉ ደህና ናቸው ወይስ ባምላክ የተገደበውን ለማራዘም ከመሃላቸው ጭዳ የሆነ እንዳለ ለማረጋገጥ ፈልጌ ነው ምክንያቱም አንባ ገነኖች የማይበጥሱት ቅጠል
የማይሞክሩት የለምና ነው
የአንባገነኖች እድሜ የሳሙና አርፋ ነው

No comments:

Post a Comment