Translate

Saturday, July 21, 2012

Awolia uprise updates (መሪዎቹ በሽብርተኝነት ተከሰሱ)leaders being tourcherd

Postby Beles » Fri Jul 20, 2012 6:54 am
ባሳለፍነዉ እሁድ ክዋስ ሜዳ በሚገኘዉ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ ታላቁ የዳዕዎ መርከዝ የዳዕዎ ሰዎች መደበኛ የሶስት ወር ሹራ ለማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበዉ የነበረ ሲሆን በስብሰባዉ ለተገኙ ሙስሊሞች የተዘጋጀዉን ምግብ የፌደራል ፖሊስ ለሰደቃ የተዘጋጀ ነዉ በማለት ምግቡን ማስደፉቱ ተገለፀ!!

በዛሬው እለት በታላቁ አንዋር መስጂድ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሕዝበ ሙስሊም እጅግ ሰላማዊ የሆነውን ተቃውሞ በአስጨናቂ ዝምታ ገለፀ መንግስት ኢስላም ላይ የከፈተውን ዘመቻ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አሰምቶአል ከመፈክሮቹ ውስጥ ኮሚቴዎቻችንን መንካት ሕዝበ ሙስሊሙን መንካት ነው !! መብትን መጠየቅ ካሳሰረ ለመብታችን ለመሰዋት ዝግጁ ነን !! በሚዲያ ስም ማጥፋቱ ይቁም !! ሕገ መንግስቱ ይከበር !! መንግስት ከኀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ !! የሚሉና ሌላ ብዙ መፈክሮች ታይተዋል:: በዛሬው የጁመዐ ሠላት ላይ የሕዝቡ ብዛት ከወትሮው የተለየ ነበር ሕዝቡ በሲኒማ ራስ እስከ ተክለ ኀይማኖት በጣና ገበያ እስከ መርካቶ ባስ ስቴሽን በበፒያሳ እስከ ሀብተ ጊዮሪጊስ በአውቶቢስ ተራ ጎጃም በረንዳን አልፎ ነበር:: ኢቲቪና መንግስት እንደሚሉት ይሔ ሁሉ ሕዝብ አሸባሪ ከሆነ ሀገሪቱ ውስጥ መንግስት የለም ማለት ነው::...
Last edited by Beles on Sat Jul 21, 2012 6:33 am, edited 4 times in total.
http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=40462

No comments:

Post a Comment