Translate

Tuesday, August 18, 2015

አንድ የወያኔ አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ተያዘ

ወደ 150 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በሻንጣ ጠርቆ ለንደን የገባ የሀገራችን ዘራፊ የወያኔ ባልደረባ በእንግሊዝ ፖሊሶች ክትትል እጅ ከፈጅ ተያዘ።ከፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች እንደገለጹት ፣ አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል።
ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ፣ ግለሰቡ ” ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጻል። ይሁን እንጅ ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ? ” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሜ ይቀርባል።
ኢሳት ዜና

No comments:

Post a Comment