Translate

Sunday, August 9, 2015

የሰሞኑ ሙዚቃ ጆሮም ኣያነቃ – እኔ ያልለወስኩት ቡኮ እንጀራ ሳይሆን ቂጣ ሆኖ ይቀራል?

ብርሃኑ ተስፋዬ
ኣሁንስ በየቀኑ የምሰማው ሙዚቃ ቃናው ይለያይ እንጅ እስክስታው ተመሳሳይ መሆኑ ኣግራሞቴን ይስበዋል። ኣንዳንዴ ራሱ ይረጋል የሚል ህሳቤ ብልጭ ቢልብኝም ኣንዳንዴ ሳስበው ደግሞ ሙዚቀኞቹ ሃይ ሊባሉና የሚሰሩትን የማያውቁ መሆናቸው መናገር ግድ ይሆናል። ይህ የሚሆንበትም ምክንያት ኣስበውትም ሆነ ሳያስቡት እየመቱት ያለው ቅላጼ፣ የከበሮው ድምጽ፣ የእስክስታ መቺዎቹ ኣዘላለል ህብረ ብሄራዊ ሳይሆን ለድርጎ ኣዳሪዎች ወያኔ ሰራሾች ኣቀንቃኝ የተደረሰ ድርሰት ላይ መሰረት ማድረጋቸው ነው።Patriotic Ginbot 7 freedom fighters continue attacking TPLF
ለመነሻ የሚሆን ስንቅ
ለረጂም ጊዚያት በዲኣስፖራው የሚነገር ኣንድ ኣባባል ነበር። ወይ ተባበሩ ኣልያም ተሰባበሩ ። ይህ ማለት ግን ውሃና ዘይት ለመቀላቀል የታሰበ ኣልነበረም። ይህ ባለመሆኑም በተለይ ሃይላቸውን ኣስተባብረው በነፍጥ የሚታገሉት ስብስቦች ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የበኩላቸውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህም ይበል የሚባል እንጅ ኣዶ ከብሬ የሚያስነሳ መሆን ኣልነበረበትም።

ከዚህ ባሻገር በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሃገር ውስጥ ያሉ ድርጅቶችም የበኩላቸውን ኣስተዋጽዎ እንዲያደርጉ ኣስፈላጊ እገዛ ያደርጉ የነበሩም እገዛቸውን ኣንድ ደረጃ ከፍ ያደርጋሉ የሚል ግንዛቤ ባብዛኛው ኢትዮጵያዊ ነበር እንጅ ከዚህ ስብስብ ጋር የነበሩ ኣንዳንድ ኣባላት ቀኝ ሁዋላ ዙር ብለው የውግዘት ኣፎታቸውንና ኣፋቸውን ከሰገባው ማውጣትን ምን የሚሉት ይሆን?
እነዚህና እነዚህን የመሰሉ ሃሳቦችን ሳውጠነጥን ምንም መነገር ያለበት በመሆኑ ሃሳቤን እንደሚከተለው ኣቀርባለሁ።
በኣሁኑ ወቅት ትግሉ ከወረቅትና ከኣዳራሽ ስብሰባ በተጨማሪ በመስክ ተጠናክሮ የተጀመረበት ወቅት ነው ቢባል ማጋነን ኣይሆንም። ይህ ሲባል ግን የመስክ የትጥቅ ትግል ኣልነበረም ለማለት ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ኣልነበረም ለማለት ነው።
ይህም የሚያሳየው ባለፉት ኣመታት ተከስተው የነበሩ ሁኔታዎችን ገምግሞ የተስተካከለ ኣካሄድን መቀየስ ኣስፈላጊ እንደነበረ ነው የሚያመላክተው። ባንድ ወቅት ይህንን ሃሳብ የሚያጠነክር ሃሳብ ኣቶ ኣንዳርጋቸው ባንድ ስብሰባ ላይ ተጠይቆ ባለፉት ኣመታት የተለያዩ ነፍጥ ያነሱ ድርጅቶች ኣሁን በምትሄዱበት መንገድ ሞክረው ኣልተሳካላቸውም ነበር ኣሁን የናንተን መንገድ ኣዲስ የሚያደርገው ምኑ ነው ተብሎ ሲጠየቅ ያለው እንዲህ ነበር፣ እኔ ባለፉት ኣምስት ኣመታት በቦታው ተመላልሼ ባደርግሁት ጥናት መሰረት ባገኘነው የመሸጋገሪያ ቦታ ተጠቅመን ትግሉን ኣመርቂ ውጤት ላይ ለማድረስ ካልቻልን የራሳችን ድክመት እንጅ ይህ ድክመት የኤርትራ መንግስት ሊሆን ኣይችልም።
ባለፉት ሁለት ኣስርት ኣመታት በኤርትራ በኩል ነፍጥ ኣንስተው ሲታገሉ የነበሩትን ለመንቀፍ ኣቃቂር ለማውጣት ኣቅሙም ህሊናም ሞራሉም የለኝም። ሆኖም በተለያዩ ጊዚያት ያቀረቡዋቸውን የቡድንም ሆነ የግል ዘገባዎች ስመረምራቸው ሁኔታው ኣልጋ ባልጋ እንዳልነበር የሚጠቁሙ ናቸው። በመሆኑም የነበሩትን ችግሮች ኣንስቶ በወቅቱ መፍትሄ መፈለግ ኣዋቂነት የነበረ ቢሆንም በዚያን ጊዜ የተከሰቱትን እንደ ኣላል ለጥፎ ዛሬ ድረስ ማመንዠክ ኣስፈላጊ ግን ኣይመስለኝም። ልምዶችና ያለፉ ድክመቶች መማማሪያ እንጅ ማስፈራሪያ ሆነው ማገልገል የለባቸውም።
ይህንን ስል ደግሞ ያላቸውን ፍራቻ ለምን ተነፈሱ ሳይሆን ፍራቻቸውን እንዴት መቀረፍ ይኖርበታል ይህንን ኣይነት ስልት ብትጠቀሙ ስራችሁን ቀና ያደርገዋል የሚሉ ሃሳቦች ኣቅርበው ቢሆን ኖሮ ትግሉን በማጎልበት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ከመሆን ባሻገር ኣዋቂነት ነበር።
የመዳረሻ ሃሳብ መዳረሻ
እንግዲህ ያለፉትን ችግሮች ኣምጥቶ ለማስረዳት የተሞከረበት ዘዴ ምን ይመስል ነበር የሚለው መዳሰሱ ወሳኝና መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ኣስፈላጊ ይመስለኛል። ስለዚህ ትንሽ ካነሳሱ ኣንስቼ የራሴን ግንዛቤ ላስረዳ።
ኣሁን የደረስንበት በተቃዋሚዎች ጎራ ያለው መራኮት ላይ በተዋናይነት ወደ ፊት የመጡትን ስብስቦች ማጤኑ ወሳኝ ነው። መነሻው ከላይ እንደገለጽሁት ለመንደርደሪያ በትግሪኛ ኣንድ ኣባባል ልዋስ ። ባል ፈልገሽ ጺም ጠልተሽ እንዲሉ ኣሁን ነፍጥ ኣንስተው የሚዋጉትን ለመቃወም ቀደም ቀደም ብለው የተነሱት ነጻነት ፈላጊዎች ነን ባይ የወያኔ እድሜ ኣራዛሚ እንክብል ሆነው መገኘታቸው ኣሳዛኝ ክስተተ ነው።
እንደኔ ኣመለካከት ኣሁን የተያዘው ኢላማን ከኩዋሱ ላይ ዘወር ለማድረግ የሚንደረደሩት ወያኔዎች ሳይሆኑ በእድሜ ጠገብን የሚሉ በወጣትነታቸውን ህዝባዊ መንግስት መፈጥር ኣለበት ብለው ትንታግ የነበሩና በ1983 ሃይል ስላልነበራቸው ካሁኑ ጉጅሌ ጋር ስልጣን የመካፈል እጣ ያልደረሳቸው ናቸው።
የህብረተሰብ እድገት እንደሚያስተምረን ሁሉ ኣንድ ስብስብ ከትንሽ ወደ ትልቅ የመሰባሰብ ኣቅም ሲያዳብር እድገት ይሆናል። የዚህ ስብስብ አቅም ሲያጣ ኣንድም መክሰም ኣለያም መዋጥ ወይ መዋሃድ ኣማራጭ ነው። ይህ ካልሆነ ግን እንደ ኣሜባ ኣንድም መከፋፈል ወይም ሲሚንቶ እንደጎደለው ግድግዳ መሰናጣጠቅ ባህል ያረገዋል። ኣሁንም የምናየው ይሕ ክስተት ነው። ይህን እውነታ ለመሸፈን ግን ባሁኑ ጊዜ እየተደረገ ያለው በኤርትራ በኩል ያለው ትግል ኣያዋጣም እነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በሚመሩት ትግል ግቡን ኣይመታም የሚል ስንካላ ምክንያት ማቅረብ እንጅ የተለየ ኣማራጭ ይዞ ኣለመገኝት ሌላው ኣስቂኙ ቲያትር ነው።
ሌላው ኣስቂኝ ሁኔታ እስከ 2015 (እኤአ) መባቻ ድረስ የኣርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 የፍትህና ደሞክራሲያዊ ንቅናቄ በጣምራ መስራት ከመጀመራቸው በፊት በኤርትራ በኩል የሚደረገው ትግል ምንም እንከን ኣልነበረበትም ወይም ኣሁን የምንመለከተው ዉካታ ኣልነበረም። ሆኖም ግን እኔ ያልለወስኩት ቡኮ እንጀራ ሳይሆን ቂጣ ሆኖ ይቀራል ኣይነት ጉዋዛም ትግል በተለያዩት የኣርበኞች ግንባር ኣባላት መነሳቱ ኣንድም ንፉግነት ኣልያም ለህዝብ ሳይሆን ኣንድ ታሚል ጉዋደኛየ እንደነገረኝ “እኔ ለትግሉ የማዋጣው ቤተ ሰቤን እስካስወጣ እንጅ ትግሉ አራት እግሩን ቢበላ ኣይቆጨኝም”ኣይነት ነው። ይህንንም ለማስረገጥ ኣንድ እንደራሴ ነኝ የሚል ታዳሚ ለእኔ ያልሆነች ኢትዮጵያ ኣራት እግሩዋን ትብላ ያለውን ኣስቂኝ ኣባባል ኣስታወሰኝ።
ይህንንም ለማስረገጥ ኣንድ እንደራሴ ነኝ የሚል ታዳሚ ለእኔ ያልሆነች ኢትዮጵያ ኣራት እግሩዋን ትብላ ያለውን ኣስቂኝ ኣባባል ኣስታወሰኝ።
ኣሁን ኣግራሞቴን የባሰ የሳበው ደግሞ ከ2011 በፊት ኣስመራ ተመላለስኩ ባይ ጋዜጠኛ ደግሞ ያልበላውን ማከክ ያልሆነ ውሸት መሞነጫጨር ጀምሮዋል። ድንቄም ጋዜጠኛ በሄደበት ወቅት ጽፎት ቢሆን ኣደንቀው ነበር። ሆኖም ጅብ ከሄድ ምን ጮኸ ኣይሆንበትም ኣሳፋሪ ጋዜጠኛ።
ኣሁን ስብስቡ የሚያወራዉ ጠፍቶት ወያኔ ያጎረሳቸውን የዘር ፖሊቲካ ማላመጥ መጀመራቸው ምን የላከው ምን ኣይፈራም ኣይደል።
የሰሞኑ ኣላዛኞች መጀመሪያ በኤርትራ በኩል ለምን ይኬዳል ነበር ጩኸታቸው ሲነጋ ደግሞ ዞረው በኣርበኞች ግንባር ኣባላት የሉትም ሆነ ኣሁን ደግሞ በኤርትራ ያሉ የነጻነት ታጋዮች ኣንድ እርምጃ ተጉዘው በጋራ መሰራት ሲጀምሩ በተናጥል ድምህት ላይ ዞረዋል። ይህ ዘረኝነት የተጣባው ስብስብ ባለፉት 25 ኣመታት ምንም መፍጥር ኣለመቻሉን መገነዘብ ኣለመቻሉ ሳያንሰው ኣሮጌ ወይን ባዲስ ጠርሙስ ሆኖ ብቅ ማለቱ ሊያፍሩበት ይገባ ነበር። ኣስቲ ለነዚህ ያስተሳሰብ ጎደሎዎች ትንሽ ልግጥምላቸው፣
አሱዋም ዜሮ ዜሮ እሱም ዜሮ ዜሮ
ምነው ተቆለለ ስማቸው ዘንድሮ
የስዋን ባካል ቅሪት የሱን በተራራ
ምን ኣቃጠላቸው እንዲህ የሚያስጎራ
በዜሮ ላይ ዜሮ ምን ቢከምሩት
ትግሉን ኣይመልሱት
ኣንዴ ጉዞ ይዝዋል የትግሉ ትንታግ
ጩኸቱን ትታችሁ ተው ፈልጉ ጥግ
ሳትረጋገጡ በጀግኖቹ ጫማ
ታጋዮቹ መሃል የለም የሚያቅማማ
ነጻነት ሳይገኝ ለውዲቱ እማማ
ማሳረጊያ
የማያድግ ጥጃ በጅብ ሳይሆን በተቅማጥ ይሞታል ኣይነት ሆኖ ትግሉ በጋመና በጋለ ቁጥር መንሸራተት እንዳለ ያስተማራች ሁን እናንተው ነበራችሁ ታዲያ ኣሁን ኣንድም ማደግ ኣልያም ማስተባበር ኣለመቻላችሁ ሲገረመኝ ትግሉን መርገጥ ለምን እንዳስፈለጋችሁ ሊገባኝ ካለመቻሉን ባሻገር ባይሆን መረዳት ኣሊያም ዝም ማለት ዝም ባለ ኣፍ ምን ኣይገባበትም ይሆናልና ጠንቀቅ ነው የሚሻለዉ ኮሚንስቶች ።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆችዋ ደም ለዘላለም በክብር ትኖራለች
chillalo@gmail.com

No comments:

Post a Comment