Translate

Tuesday, August 18, 2015

እነ ፕሮ/ር ብርሃኑ ከኤርትራ በረሃ መልዕክት አስተላለፉ –


_በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና በምክትላቸው በአርበኛ መዓዛው ጌጡ የተመራው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር በኤርትራ በረሃ በተለያዩ የጦር ካምፖች የሚገኙትን የነጻነት ታጋዮችን ጎበኘ። አቶ ነዓምን ዘለቀና አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ተገኝተዋል። ታጋዮቹ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከአመራሮቹም ጋር ተወያይተዋል።

_ባለፈው ዓርብ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ 17 ኢትዮጵያውያን ተገደሉ። ስርዓቱ በቃን ብለው አደባባይ ለተቃውሞ በወጡት ላይ ፌደራል ፖሊስ ተኩስ ከፍቶ 12ቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ 5ቱ ሆስፒታል ሲደርሱ ህይወታቸው አልፏል።
_አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው ተጎበኙ። ቃሊቲ በቅርቡ የተወሰዱትን ልጃቸውን የጎበኙት አቶ ጽጌ ሀብተማርያም ስለምን እንደተነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም።
_አንድ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አባል 5 ሚሊዮን ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣ ይዞ እንግሊዝ ሲገባ ተያዘ። በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ በመሆኑ ስሙ ያልተገለጸው ይሄው የህወሀት አባል ጋትዊክ በተሰኘው ለንደን በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ በፖሊስ ተይዟል።
_ድርጊቱን ፈጽመናል። ግን ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ ሶስቱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ። ብርሃኑ ተክለያሬድ፡ ኢየሩሳሌም ተስፋውና ፍቅረማርያም አስማማው ያመንበትን የወሰነውን አድረገናል። ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ትክክለኛውን መስመር ለመያዝ ስንጓዝ ተይዘናል። በተረፈ ጥፋተኛ አይደለንም ብለዋል።

No comments:

Post a Comment