Translate

Wednesday, August 5, 2015

ሁለቱ ትግሎች፤ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ የዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም የማስቀየስ ስልት

እርቀ ሰላም (ከደቡብ አፍሪቃ )
ብርሁኑ ነጋ ዱር ገባ!
አንዳርጋቸው ጽጌ መፅሀፈ ሰ ጨረሰ!
ኦባማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መመረጣችንን አውቅና ሰጠ!
እነዚህ እንግዲህ የሰሞኑ ፖለቲካዎች ናቸው።
ያለወትሮዋቸው በአሜሪካ ድምፅ ላይ ለቃለመጠይቀ የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኅኖም ያልበላቸውን ሲያኩ ተደምጠዋል። አድማጭ ልብ ሊሊው የሚገባ ጉዳይ አለ። ዶፍተሩ ስለ ብርሀኑ ነጋም ሆነ ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተናገሩት ሳይጠየቁ ነበር ይኼ እንግዲህ “ማርያምን … ምን የበላ ..” እንዲሚባለው ነው።Tedros Adhanom interview
ሲጀመር ዶፍተሩ ቪኦኤ ላይ የቀረቡት ስለ ኦባማ መምጣትና መሄድ ላይ አስተያየት ይሰጡ ዘንድ ነበር። ማርሻቸውን ቀየሩት!
የተጠየቁት “ከአንበሳና ነብር ማን ያሸንፋል?” ተብለው ሲሆን፣ የእርሳቸው መልስ ግን
“ዝሆንን ማን አህሎት!” እንደሚባለው ፈሩን የለቀቀ ምላሽ ሰጥተዋል። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ወያኔ ሸገር ሰተት ብሎ ሲገባ ግፋ ቢል የአምስት አመት ልጅ ነበርኩ፤ ሀያአራት አመት ግን የወያኔ ባህሪ ለመረዳት እጅግ በጣም ብዙ ነውና ይህንን መሳት አይኖርብንም የሚል ሀሳብ አለኝ።

አገራችንን አንቆ እየሳማት ያለው ገዢያችን ስልታዊም ዘላቂያዊም እቅዶችን በመጠንሰስ ከችግር እንዴት መወጣት እንዳለበት ሲተልም፥ ሲያስፈፅም ይኸው ዛሬ ላይ ደርሰናል። የገዢዎቻችንን ስስ ብልት ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ጎናቸውንም ልናውቅ ግድ ይላል።
የወያኔ አመራር አንድ እንዳልሆነ እርስ በርስ እንደሚናናቁ ብዙ የተባለለት ነው። ሆኖም ግን ችግር ሲመጣ አንድ መሆንንም ያውቁበታል፤ ከዚህ ባለፈም አቅጣጫ በማስቀየር በኩል የተጨበጨበለት እንደሆነ ባለፉት ጊዜያት ያየነው ነው። ይህንን ስልትም ከበረሀው ጀምሮ ያዳበሩት ስለሆነ ኢትዮጵያን ለመግዛት (የዋህ የሆነውን ህዝብ) በእጅጉ ጠቅሟቸውል።
ይህች የማሳለጫ ስልታቸውም በተደጋጋሚ ሲጠቀሙባት ተስተውሏል።
የምርጫ ዘጠና ሰባት ትኩሳት አልበረድ ብሎ ራስ ምታት በሆነባቸው ጊዜ ሚሊኒየም የሚሉትን ጅራፍ ማጮህ ጀመሩ ሁሉም ተቀብሎ ማስተጋባት ሆነ፤ ዲያስጶራው፥ ሚዲያው፥ ተቃዋሚዎ፥ የቤተ እምነት ሰዎች፥ ተማሪ ቤቶች፥ መስሪያቤቶች፥ ስፖርታዊ ክንውኖች ሁላ ስለ ሚሊኒየም ሆነ ወሬያቸው። ወያኔም እፎይ አለ ለሶስት አመታት ከማእበሉ ወደ ደሴቱ ሲያላጋው የነበረው ችግር ተቀረፈለት። የህዝቡ አቅጣጫም ተቀየረ! ያ ስንት ዋጋ የተከፈለበት ትግል ወሀ ተቸለሰበት፤ ዳግመኛም እንዳይመጣ ተድርጎ ተሰናከለ (በነገራችን ላይ አንዳንድ የዋሆች የማይመጣውን ሲጠብቁ ይስተዋላሉ። አፋቸውንም ሞልተው ያኔ ወደነበራቸው ተክለ ቁመና ተመልሰናል ሲሉ ይደመጣል።)
ሁለተኛ ማስቀየሻ – የአባይ ግድብ!
የ2002 አ.ም. ምርጫ ተደርጎ ካበቃ በሁዋላ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (ጂቲፒ) የሚባለውን ልማታዊ ቅዥት ይፋ አደረጉ። ይህንን ማድረጋቸው ኢህአዴግ የፓርላማውን ወንበር በሙሉ በማሸነፉ ተደስቶ ህዝብን ሊያገለግል ፥ ልማትን ሊያፋጥን ቆርጦ የተነሳ ተደርጎ እንዲሳል ሆኗል። ከምርጫው ትኩሳት ብዙም ሳይቆይ የአረብ ፀደይ አብዮት ተጀመረ።
ለቀጣዩ አምስት አመት እንሰራዋለን ብለው ካቀዱት ውስጥ ያልተካተተውን የአባይ ግድብ ግንባታ ዋነኛ የልማት አጀንዳ በማድረግ አጎኑት። ሁሉም ነገር አባይ ሆነ። ስለ አባይ የሚያወሱ ዘፈኖች አቧራቸው እየተጠረገ ተደመጡ፤ ስለ አባይ የተገጠሙ ፥ የተጻፉ ጽሁፎች ተጎልጉለው ወጡ። (ስለ አባይ በብዛት የተገጠሙ ግጥሞች “አባይ ስም ነው እንጂ ምን ጠቅሟል ለአገሩ” ፥ “አንተን ብሎ አባይ”፥ “አባይ ቀላባይ”፥ “እውነትም አባይ” የሚሉ አሉታዊ መሆኗችን ያጤኗል። ነገር ግን እድሜ ለወያኔ ሳንሱር እነዚህን አዎንታዊ ማድረግ አይሳናቸውም።)
እዚህ ስለ አባይ ሲዘፈን የአባይ ስጦታ ወደሆነችው ግብጽ አብዮት ይካሄድ ነበር። የሆነው ሆኖ ግን ያቺን የጭንቅ ቀን እንደምንም ብሎ ወያኔ ተላለፋት።
ዘንድሮ 2007 አ .ም. ነው!
ወያኔም ምርጫውን ያለማንም ተቀናቃኝ አሸንፌያለሁ ሲል ተንግሯል። እውቅና የሰጡት ባይጠፉም ከት ብለው የሳቁበትም አሉ። (ነገሩን በደንብ ካጤነው ፈረንጇ የሳቀችው በወያኔ ድራማ ቢሆንም እንደ ሀገር ግን ያላዋቂ ሳሚ በሚገዛት ጦቢያ ላይ መንከትከቷ ያሳፍራል።)
ወያኔ አሸነፈ … ድሉንም አወጀ … ኦባማንም ተቀበለ። በቬኦኤም ተጠየቀ። ምላሽም ሰጠ። የሚፈልገውን መልእክትም ለስለስ ባለ ቆዳው አስተላለፈ።
የወያኔ ሚንስተር ለቬኦኤ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አንጉአ ማግኘት ከትግሉ ተግዳሮቶች አንዱን ጠጠር እንደማስወገድ ይቆጠራል።
አንጉአ አንድ – ስለ አርበኞች ግንቦት ሰባት
ዶፍተሩ ወያኔ ባሁኑ ወቅት እያቃዠው ስለሚገኘው ጉዳይ ሳይጠየቁ መመለስ ጀምረው ስለ ዶከተር ብርሀኑና አንዳርጋቸው ተናግረዋል። የያዙትን ትግልም “አበጀህ! >ብለውታል። በፊት በፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን ሲመልሱ የደሀውን ህዝብ ለማስጨረስ”፥ “ቢያንስ ቢያንስ መሬት ላይ ተገኝቶ ቢያደርገው አላማውን ባልደግፈውም አከብረዋለሁ” “<የላፕ ቶፕ ጦርነት” “ሁልት ሺህ ማይል ተርቆ ስለ ኢትዮጵያ የመናገር ሞራል የላቸውም።” ወዘተ… ነበር መልሳቸው።
ለነገሩ አሁን በቅርቡ አዲስ አለም ባሌማ የተባለው የህወኀት ቀንደኛ አመራር “አሸናፊ የሚሆነው ጠንካራው አይደለም ብልሁም አይደለም፤ የሚያሸንፈው ራሱን ከጊዜው ጋር ፈጥኖ የሚቀያይረው ነው።” ብለውን የለ።
እናም ዶፍተሩ ስለ አንዳርጋቸው እንደ እንቁላል በክብካቤ መያዝ፥ የቻይና ላፕቶፕ ሰጠነው፥ መፅሀፈ አፈና ፅፎ ጨረሰ (ሜጋ ያሳትመዋል?)፥ ናዝሬት ሄዶ ጉብኝት አደረገ።
(እርሳቸው ሆነው ነው እንጂ ስብሃት ነጋ ኖሮ <እገረ መንገዱንም አዳማ (ናዝሬት) በሚገኘው ጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ተገኝቶ የታዘበውን መፅሀፉ ላይ አካቷል ይሉን ነበር።) ሲሉን አመሹ። እንዲህ የተደናባበረ መልስ መስጠታቸው ኦባማ አንድ ናገር ሳይላቸው ቀርቶ ይሆንን? ብለን እንድንጠራጠርም አድርጎናለ።
ዶፍተር ቴዎድሮስ! ሳይበሉ ያከኩበት ምክንያት አርበኞች ግንቦት ሰባት የቀን ራስ ምታት የሌሌት ቅዠት ስለሆነባቸው እንደሆነ ቆሪጥን መቀለብ አያሻም።
አንጉአ ሁለት – ስለ ሰላማዊ ፓርቲዎች
ሰማያዊ ፓርቲ ፥ አንድነት እንዲሁም መኢአድ (በህይወት የሌሉ ቢሆንም) አሁንም ድረስ ህዝባዊ አመፅ በማስነሳት ፥ ማህበራዊ መሰረታቸውን በመጠቀም የስልጣን ዘመናችንን ያሳጥራሉ የሚል ስጋት አላቸውና፤ በቃለ መጠይቃቸው በገደምዳሜ ከኛ ጋር አይሰሩም በሚል ስጋትቸውን ወይንም ማስፈራራታቸውን ተናግረዋል።
ወያኔ በቀጣይ አምስት አመት እሰራዋለሁ ላለው (ጂቲፒ ድራማ ክፍል ሁለት) እቅድም ተቃዋሚዎችን አሳትፋለሁ ማለቱ ምን ታይቶት ይሆን ? ብለን እንደንጠይቅም አድርጎናል። መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ዶፍተር ቴዎድሮስ በቃለ መጠይቃቸው የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከኢህ አዴግ ጋር ጥምረት ቢፈጥሩ የተሻለ እንደሆን መናገራቸውም ሌላ አንድምታ ሳይኖረው እንዳልቀረ መገመት አያዳግትም። ስልጣን ለማን እንደሚያስረክቡም ግራ ገብቷቸው ሊሆን ይችላል ። (መንግስቱ ኃይለ ማርያም “…በወቅቱ ስልጣን እናስረክብ ብንል ኖሮ ለማን ነበር የምናስረክበው? ለወያኔ? ለሻቢያ? ስለሆነም የአፍሪቃ መሪዎች ስልጣናቸውን የሙጥኝ እንዳሉ ይኖራሉ።ማለታቸውንም ልብ ይሏል አስረጅ – የመንግስቱ ኃይለ ማርያም ትዝታዎች ክፍል ሁለት – 2004 አ.ም.)
አንጉአ ሶስት – ስለ ደጋፊ (ደጀን) ሀይሉ
ዶፍተሩ! በቃለ መጠይቃቸው በራሳቸው ተነሳሽነት ካነሷቸው ነጥቦች ስለ ዲሲ ኢትዮጵያውያን የተናገሩት አንዱ። የወያኔ ካምፕ ለነጻነት በሚደረገው ትግል ዋና ደጋፊ ብሎ የፈረጃቸው በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንደሆነ ለማንም ነጋሪ አያሻውም። ይህንን ራስ ምታታቸውንም ዶፍተሩ ዲሲ ላይ ያለውን አጋዥ ሃይል ለማኮሰስ ያልተሳካ ሙከራ አድረገዋል።
አንጉአ አራት – አቅጣጫ ማስቀየሪያ
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳው መግባት ያስደነገጠው ወያኔ ነገሩን አሳንሶ ለማሳየት ያደረገው ጥረት አልሳካ ሲለው አቅጣጫ ወደማስለወጥ ያመራ ይመስላል። (እንደነርሱ ፍላጎት ቢሆንማ ከቁጥጥራቸው ውጪ ያልሆነ የምርጫ ድራማ በየአምስት አመቱ እየሰሩ ለመቀጠል ነበር።)
ይህንንም የማስቀየሻ ሽጉጥ ይዘው ወደ አሜሪካን ድምፅ መስመር የመጡት ዶፍተር ቴዎድሮስ ቃታኣውን በመሳብ የመጀመሪያውን ጥይት ተኩሰዋለ። በርግጥ በዚህ የተሳሳቱ (እልህ የገባቸው ሀገር ወዳዶች) በወጥመዱ ሰተት ብለው ሊገቡ ችለዋል። በዚህም ምክንያት ዶፍተሩ ቃለ መጠይቁን በሰጡ ማግስት የጀመረው ምላሽና አስተያየት የሳይበር ማህበረሰባችን መወያያ ሆኗል።
ነገር ግን ይህንን ፋይዳ ቢስ የሆነ እሰጥ አገባ ትተን ትኩረታችን የተጀመረውን ትግል እንዴት እናግዝ ? እንዴትስ ዘላቂና አስተማማኝ እንድርገው ወደሚለው መሆን ይኖርበታል። አስተያየት መስጠት ቀላል ነው፤ ተግባር ግን ቆራጥነትን ፥ ፅናትንና ዋጋን ይጠይቃል። ፈረንጆቹ “who dares win – ደፋር ያሸንፋል” ብለው ይጀምሩና “to dare is to do – ድፈረት ማለት መተግበር ነው።” ሲሉ ያፀኑታል።
አደብና ልባናን ለትእቢተኛው ስልጣንን ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሰጥ አምላክን እንለምነው!

No comments:

Post a Comment