Translate

Wednesday, August 12, 2015

የኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የመንግስት ባለስልጣናትን በጥያቄ አጨናነቁ

ስብሰባው ከአርባ ሰባት ሃገራት የተሰባሰቡ የኦሮሞ የዲያስፖራ አባላትን የአርባ ሰባቱ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተካሂዷል ።
መንግስት የኦሮሞ ዲያስፖራ ሳምንት ብሎ የሰየመውን ሳምንት በማስመልከት: ከመላው አለም ያሰባሰባቸውን የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላት: በሚሊኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚስትሩ በተገኙበት ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ካደረገላቸውና : ለሶስት ቀናት ያክል ሃገሪቷን ካስጎበኛቸው በኃላ : በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በመሰብሰብ : የተለመደ ፕሮፓጋንዳውን ለመንዛት ቢሞክርም: ከኦሮሚያ የዲያስፖራ አባላት ፍፁም ያልጠበቀው :የጥያቄ ውርጅብኝ ዘንቦበታል ።

ስብስባውን የመሩት አቶ አባዱላ ገመዳ አቶ ሙክታር ኸድር እና ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሲሆኑ : ከኦሮሞ ዲያስፖራ አባላት የተነሱት ጥያቄዎች በአራት ነገሮች ላይ ያጠነጠኑ እንደነበሩና እነሱ :–
1)የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን የፍርድ ሂደት በተመለከተ
2) የጋዜጠኞችን መታሰር ጉዳይ በተመለከተ
3) የኦሮሞ ተማሪዎችና ወጣቶች መታሰርን በተመለከተና
4) የመሬት ማስተር ፕላኑንና በተመለከተና በማስተር ፕላን ሰበብ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ እንደነበር ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል።
በተለይም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጉዳይ ከዲያስፖራው አባላት ሲነሳ : የተሳታፊዎቹ ስሜት ፍፁም ልዩ እንደነበርና: እያንዳንዱ እነሱን በሚመለከት የሚነሳ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር : ከኃላው ከፍተኛ ጭብጨባ ይከተለው እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ። በእለቱ ኮሚቴዎችን በተመለከተ ጥያቄ ካነሱት መካከል ከሳውዝ አፍሪካ የመጣው ወንድም እኔ እዚህ የመጣሁት መሬት ፈልጌ አይደለም : አባቴ ብዙ መሬት አለው ። ተጨማሪ መሬት ካስፈለገኝም ገንዘቤን አውጥቼ ከናንተው እገዛለው ። የመጣሁት አንድ ጥያቄ ለመጠየቅ ነው። ያሰራቿቸውን ኮሞቴዎቻችን ትፈታላችሁ አትፈቱም ? አቶ ሙክታር ከድር ና ፣አቶ አባዱላ ገመዳ ሁለታችሁን ነው የምጠይቀው ። ይህንን ጥያቄ መልሱልኝ ። መሬት ብሰጡኝ እንኳን አልቀበልም ። ለምን ፈረዳችሁባቸው ? ጥያቄውን የጠየቅነው እኛ ነን ። ህዝብ እየሰማ ትፈታላችሁ አትፈቱም ? ነው የምንላችሁ: እምቢ አንፈታም ካላችሁ : መሳሪያ ገዝተን በናንተ ላይ ነው የምንነሳው : ይህ የምትቀመጡበት ወንበር ነገ አይኖርም ። የህዝቡ ነው ልትነሱ ትችላላችሁ በማለት ቆምጠጥ ያለ ንግግር ማድረጉን: አንድ የባሌ ተወላጅ የሆነ ወጣት ደግሞ ሀይለስላሴ ይህችን ሀገር ፈጣሪ ለኔ አደራ ሰጥቶኛል : እያለ ስብስባ ላይ ሲያወራ : በስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሀጂ አደም ሳዶ የተባሉ ሙስሊም : ፈጣሪ ይህችን ሃገር ለአንተ አደራ ሲሰጥህ : ባሌን ረስቷታል ወይ አሉት : እኔ ደግሞ እናንተን እላችኋለው ። እናንተ የህዝቡን መብት እናስጠብቃለን ስትሉ የሙስሊሙን መብት ከመሃል ረሳችሁት ወይ ? እነዚህ ሙስሊም ወንድሞቼ የጠየቁት ጥያቄ መልስ የማያገኝ ከሆነ : ልማት የሚባል ነገር የለም። ነገሩም ዛሬ ቁጭ ብለን እየተሳሳቅን እንደምናወራው አይነት ወሬ አይሆንም ።
ከአሜሪካ ሜኒሶታ የመጡ ሽማግሌም : እኛ ትንሿ ኦሮሚያ ብለን የጠራናት ከተማ ሜኒሶታ ላይ ገንብተናል። ወደዳችሁም ጠላችሁም ስለችግራችን እዛ እንወያያለን ። እኛ ወደ ሌላ መጥፎ ነገር ሳንገባ ጥያቄውን መልሱ ኮሚቴዎችን ፍቱ ። ኮሚቴዎቹ ላይ የፈረደባቸው የመንገድ ዱርዬ ከሆነ እንደ መንግስት የማስተካከል ግዴታ አለባችሁ : አስተካክሉ : ለዚህም ነው ሀገር አቋርጠን የመጣነው : የምታስካክሉ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ሳይመሸ አስተካክሉ : እኔ እንደሆነ ነፍሴ በራሷ ሠዐት አጀሏ እየደረሰ ነው። ምንም የምፈራው ነገር የለም። እዚህ ምላሳችሁን ለማጣፈጥ የምትሞክሩ ስትወጡ ምላሳችሁ ሌላ ነው እኔ ግን እዚህ ም እዚያም አንድ ነኝ : በማለት ድንቅ ንግግር አድርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሚያ ወጣቶች ላይ መንግስት በተለያየ ወቅት :በተለያየ ምክንያት :የወሰዳቸውን እርምጃዎች በተመለከተ፣ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እያደረሰ ያለውን እስራትና ማሳደድ በተመለከተ ፣ የመሬትንና ማሰተር ፕላኑን በተመለከተ : ጥያቄዎች ለባለስልጣኑ የቀረቡላቸው ሲሆን : ከባለስልጣኑ የተሰጠው መልስ: እንደተለመደው አለባብሶ የማለፍ ዘዴ መሆኑንና : የመሬትን የኮንዲኒየም ቤትን በተመለከተ ግን : እንደማንኛውም ዜጋ አስፈላጊውን ምዝገባና ፎርማሊቲ ካሟሉ ብቻ : ሊያገኙ እንደሚችሉ እንደተገለፀላቸው ምንጮቻችን አያይዘው ዘግበዋል ።
በእለቱ የኦሮሞ ዲያሰፖራ አባላት እንደ ሙስሊምነታቸውና :እንደ ኦሮሞነታቸው: በቂና የሚያኮራ ስራ እንደሰሩ ምንጮቻችን አያይዘው ገልፀዋል።
ስብሰባው ለሁለተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን: በእለቱ በመጀመሪያው ቀን ስብስባ ላይ ድንቅ: ንግግር ያደረጉት የሜኒሶታው ሽማግሌ አባት : ንግግር ለማድረግ (ጥያቄ ለመጠየቅ) እጃቸውን በተደጋጋሚ ቢያወጡም በመጀመሪያው ቀን ስብሰባ ላይ :ያደረጉትን ምርጥ ንግግር : ያልወደዱላቸው ባለስልጣናት: እድል ስለከለከሏቸው ተበሳጭተው : ብድግ ብለው በመነሳት : ከሰብሳቢዎች አንዱ የሆነውን አብዱልዐዚዝ የተባለውን ባለስልጣን “Shame on you ” Shame on you ” በማለት የሰራውን ተገቢ ያልሆነ ስራ ፊት ለፊት ተቃውመውታል ።
መንግስት መላውን ኢትዮዺያዊ የዲያስፖራ አባላት ለዲያስፖራ ሳምንት በማለት ስብሰባ እንደጠራ የሚታወቅ ሲሆን በሰብሰባው የሚሳተፋ ተሳታፊዎች : ከኦሮሞ የዲያስፖራ አባላት ትምህርት በመውሰድ ድምፃቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያሰሙ ምንጮቻችን አጥብቀው አደራ ብለዋል ።

No comments:

Post a Comment