Translate

Thursday, August 20, 2015

አብረሃ ደስታ እና ሀብታሙ አያሌውን ጨምሮ ፍርድ ቤቱ አራት ፖለቲከኞች ነፃ እንዲለቀቁ ወሰነ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡
Abraha Desta and Habtamu Ayalew to be freeበአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡ በዚህ አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ፣10ኛ ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በኢግዚቢት የተያዘባቸው ተለቆላቸው እንዲፈቱ ሲወንስ እንዲከላከሉ ያላቸው የመከላከያ ምስክር እንያስመዘግቡ በይኗል፡፡
——————————-
ይህን ዜና ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድረገጾች አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፣
አቤል ሽፈራው
እኛ እኮ ልዩ ነን አንድ አመት ያለምንም ማስረጃ በምርመራ ስም አበሳቸዉን ሲያዩ የከረሙ ሰዎች ሲፈቱ እንጨፍራልን!
እኔስ ማነኝ ከዓመት እንግልት በህዋላ ያለምንም ማስረጃ ስለሃገራችሁ ስለጨዋችሁ መከራችሁ ስታዩ የነበራቹ ጀግኖች ዛሬ በመለቀቃችሁ ደስታዬ ትልቅ ነው።
ነገር ግን 90 ሚሊዮን ህዝብ እስኪፈታ እረፍት የለንም !!!
ሃሃሃ ከግንቦት ሰባት እና ከትህዴን ጋር በማበር ሃገር ልያተራምሱ ይነበሩ ጀግኖች ቶክስ ሲጀመር እነሱ ተለቀቁ። ገራሚ ሃገር !!!
————-
ነብዩ ኃይሉ
የህወሃት ሞድ፣ ህገወጥ እስር መፈፀም —› ታሳሪዎች ላይ ሰቆቃ መፈፀም —› መስተመጨረሻ በነፃ አሰናባቶ ለምዕራባዊያኑ “ፖለቲካል ሪፎረም ውስጥ ነን” የሚል መልዕክት ማስተላለፍ።
————-
Enndelbu
TPLF just figured out jailing innocent people brings Patriotic Ginbot 7… You better release all political prisoners, journalists, bloggers etc… And stop any form of abuse. If not you will not sleep peacefully. Sooner or later our patriots will come to your door doorstep! Remember Prof. Berhanu Nega is not in Washington D.C. he is closer than ever to you!
————-
Mesay Mekonnen
ትልቅ ዜና ነው:: በጠዋት የሰማሁት መልካም ወሬ:: እግራቸው የዚያን ክፉ ግቢ በር እስኪወጣ መጠበቅ ይኖርብናል:: እነህብትሽ ተፈተዋል:: የታሰሩለት ዓላማ ግን እንደታሰረ ነው:: ኢትዮጵያ ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ካልወጣች የግለሰቦች ብቻውን ትርጉም የለውም:: ህወሀት ሲደብረው የሚያስርበት: ሲደነግጥ የሚገድልበት: በኋላም ደስ ሲለው የሚፈታበት ዘመን ማብቃት አለበት:: ወጣቶችን በጉብዝና ጊዜአቸው በእስርና ሰቆቃ ዘመናቸውየሚቀረጠፍበት ጊዜ ካላበቃ በቀር የትኛውም የግለሰብ ከእስር ነጻ መውጣት ጊዜያዊ እፎይታ እንጂ ሀገራዊ ፋይዳ የለውም::

No comments:

Post a Comment