Translate

Tuesday, January 6, 2015

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አንድነትን እና መኢአድ በምርጫው መሳተፍ እንደማይችሉ ገለጹ

የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ፣ አንድነት እና መኢአድ በምርጫ እንዳይሳተፉ መታገዳቸውን ለፋና ራዲዮ ገለጹ። የአንድነት አመራሮች ወደ ምርጫ ቦርድ ሄደው የምርጫ ቦርድን ዉሳኔ በጠየቁ ጊዜ ቦርዱ ነገ ማክሰኞ እንደሚሰበሰብና ቦርዱ እንደሚወስን ቢነገራቸውም፣ ቦርዱ ሳይሰበሰብ ምክትል ሃላፊው፣ ቀደመው በራዲዮ፣ የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲ እንደይሳተፉ መግለጻቸው፣ ከወዲሁ በሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የተወሰነና ተግባራዊ የሚሆነው ይሄ ዉሳኔ ይሆናል በሚል እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ።

አንድነት ፓርቲ ከሶማሌ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች፣ ቢያንስ ከ480 ወረዳዎች በላይ ተወዳዳሪዎች ለማሰለፍ የተዘጋጀ በጥንካሬ ከአገዛዙ ጋር መፎካከር የሚችል ብቸኛ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል። አንድነት በዚህ ሳምንት ዉስጥ ብቻ በደሴና በመቀሌ ህዝባዊ ስብሰባዎች በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት እየሰራ የነበረ ድርጅት ሲሆን፣ አገዛዙ ሜዲያውን ቢዘጋም የማተሚያ ማሽን ገዝቶ፣ ሁለት ጋዜጦችን እያተመ ለህዝብ የሚያደርስ ድርጅት ነው።
ከአንድነት ቀጥሎ ጠንካራ የሚባለውንና በብዙ ቦታዎች መዋቅር ያለው ሌላው ሁለተኛ ድርጅት መኢአድ እንደሆነ ይታወቃል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ከፍተኛ የአንድነት አመራር፣ የቦርዱን ኦፌሳላዊ ዉሳኔ ነገ ከተሰማ በኋላ ምክክር ተደርጎ ምን መደረግ እንዳለበት ለሕዝብ እንደሚያሳወቁ ገልጸዋል። ምናልባትም የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊው ሆን ብለው ለማደናገር ብለው የተናገሩት ሊሆን እንደሚችል የገለጹት እኝሁ አመራር፣ ምርጫውን አትሳተፉም ቢሉም አንድነት ሰላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

No comments:

Post a Comment