Translate

Friday, January 9, 2015

ወያኔ/ኢሕአዴግ የሚያቆነጃጀው ምርጫ 2007 ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብቷል::

አንድነትና መኢአድ የውስጥ ችግራቸውን ካልፈቱ በምርጫ ላይሳተፉ ይችላሉ::የሚል መግለጫ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በራዲዮ ፋና መስጠታቸውን ተከትሎ;የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ስብሰባን ረግጦ መውጣቱን አስታኮ በመጭው ምርጫ ላይ ውጥረት ማጥላቱን መረጃዎች ሲጠቁሙ በሌላ በኩል መድረክ እና ኢዴፓ የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉን በማለት ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር መደራደር(መወያየት)እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ይገኛል::belay
ምርጫ ቦርድ እያለ ራሱን የሚጠራው ኢሕአዴጋዊ ተቋም አንድነት እና መኢአድ በህገ- ደንባቸው መሰረት ውስጣዊ ችግራቸውን እንዲፈቱ በቦርዱ ቢነገራቸውም ችግራቸውን ሊፈቱ አልቻሉም እያለ ሲከስ መስመራቸውን ስተዋል ብሎ እንዳመጣለት በመወንጀል በምርጫ ሊሳተፉ እንደማይችሉ ቢናገሪም የፓርቲዎቹ አመራሮች ግን ምርጫ ቦርድን በመቃወም አስፈላጊ የሚባሉ ፖለቲካው እርምጃዎችን እና ውሳኔዎችን እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል::
ይህ በፓርቲዎቹ እና በምርጫ ቦርድ መካከል የተነሳው እሰጥ አገባ እና ፓርቲዎችን ከፋፍሎ መወንጀል በዋናነት ህዝቡን እያነጋገረ መሆኑ ታውቋል:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ በጠራው ገንዘብ የማከፋፈል ስብሰባ ላይ በሃሳብ እና በገንዘብ ክፍፍሉ ባለመስማማቱ ስብሰባዉን ረግጦ የወጣ ሲሆን ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ ይቅርታ ይጠይቀኝ ሲል ኢሕአዴጋዊ መመጻደቅ እያደረገ ይገኛል::የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በምርጫ ቦርድ የይቅርታ ፉጨት እንደማይገርማቸው እና የተቋሙን ልፍስፍስነት እንደሚያመለክት እየተናግሩ ነው::
መድረክ እና ኢዷፓ የግዢው ፓርቲ ታማኝ ተቃዋሚ የሚባሉ ሲሆን በለዘበ ሁኔታ የግንቦቱ ምርጫ ሂደት ላይ ቅሬታዎች አሉን በማለት ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር መደራደር(መወያየት)እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ይገኛል:: ኢሕ አዴግ ምርጫውን ተገን አድርጎ የፖለቲካ ሙስና እየፈጸመ ነው የሚለው መድረክ በምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች አመራረጥና በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች ከመንግስት በሚሰጠው የድጐማ ገንዘብ ክፍፍል ላይ ቅሬታ እንዳለው ጠቁሟል፡፡መድረክ ይህን ይበል እንጂ ምርጫ ቦርድ ውሳኔው የኔ መብቱም የኔ ነው በማለት አምባርቆበታል::ኢዴፓ በበኩሉ ምርጫው ላይ ቅሬታዎች አሉ ቢሊም ገፍቶ እንዳልታየበት እና በገዢው ፓርቲ አስፈላጊውን ትብብር በየክፍለ ሃገሩ እና መሃል አገር ላይ እየተደረገለት ስለሆነ ብዙም ጫና የሚፈጥር ችግር እንዳሌለ ሲናገር አንዳንድ ችግሮችን ለመፍታት ገዢውን ፓርቲ ለውይይት ሲጠይቅ ምርጫ 2007 በተመለከት መድረክ እና ኢዴፓ ምርጫ ቦርድ ጥርስ የሌለው ውሻ መሆኑን በተዘዋዋሪ እየነገሩት መሆኑን ያመለክታል:: ምርጫውን በተመለከተ ገዢውን ፓርቲ መለማመጥ ይቀላል የሚሉት መድረክ እና ኢዴፓ ከገዢው ፓርቲ ከተወያየን የምርጫ ቦርድ ጉዳይ የሞተ ነው ሲሉ ይናገራሉ::‪
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) -

No comments:

Post a Comment