Translate

Monday, January 5, 2015

ዛሬ የወያኔው ፖሊስ ስለለቀቀው የአንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ ቪድዮ ዙሪያ የተሰጡ አስተያየቶች

የሕወሓት አስተዳደር ፖሊስ ዛሬ ስለአንዳርጋቸው አዲስ ቪድዮ ለቋል:: በየሶሻል ሚዲያዎችም መነጋገሪያ ሆኗል:: በዚህ ዙሪያ ከሶሻል ሚዲያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ስለቪድዮው ሰብስበናል ያንብቧቸው:-
andargacew Tsige
የጆሜክስ ካሳዬ አስተያየት:-
ሌባና ፖሊስ የሚባለው የገዢው አገልጋይ የሆነው የፌዴራል ፖሊስ ፕሮግራም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ቪዲዮ በማሳየት አሜሪካን የሚያስንቅ የምርመራ ሥልት አለን እንደ ሌባ ሻይ ሳንገርፋቸው ይናዘዛሉ በማለት የድፍረቱን (የድድብናውን) ልክ ሊያሳየን ሞክሯል፣ ይህ መራር ቀልድ በአስቀያሚ የማዕከላዊ ምርመራ ሂደት ውስጥ ያለፉትንና ቶርቸርን ያስተናገዱት ጓደኞቼን ሳስብ ድፍረቱ አሳምሞኛል ፤ጓደኞቼም በማዕከላዊ ቆይታቸው የታዘቡት ጥፍራቸው የተነቀለባቸውን ተማሪዎች ሳስብ እነዚህን መርማሪዎች እና ጋዜጠኞች በፍትህ አደባባይ አገኛቸው ዘንድ ዘወትር እናፍቃለሁ፤
ፕሮግራሙ አሜሪካን ሊያብጠለጥል የፈለገበት እና የጠቀሰወው ሰሞነኛው የቶርች ሪፖርት ኢትዮጵያም ተሳታፊ መሆኗን እንዳጋለጠ ዘንግተውት ይሆን ብዬ አልጠይቅም አንዴ ምንም አያመጡም አያውቁም ተብለን ተንቀናልና (ሕዝብን ከመናቅ ካለሆነ ከምን ይመነጫል?)፡፡

በዚህ እጅ እግር የሌለው ከመቆራረጡ የተነሳ አሁንም የመግረፍ እንጂ የካሜራ እውቀት የሌላቸው ብቻ የቀረጹት እንደሆነ በሚያሳብቀው ቀረጻ አልሞተም ለማለት ካልሆነ በቀር እርግጠኛ ነኝ እነሱም አልገባቸውም፡፡
አንድ ሰው ለአንድ ቃለ መጠይቅ 10 ደቂቃ ለሚፈጅ ልብስ ለምን ይቀያይራል?
የሚናገረውን እውነት ነው ብለን እንድናምን በተያየ ቀናት የተቀረጸ ነው ብለን ብንቀበል እንኳ ራሳቸውን የሚያሳጣ እንጂ ምንም የተላለፈ መልዕክት የለም፡፡
ምርመራችሁን ጨርሳችሁ ፈርዳችሁበት እያለ ስለሚበላው ሳይሆን ስለምታደርጉበት እናውቅ ዘንድ እስከዛሬ በፍርድ ቤት ራሱን እንዲከላከል እድል በተሰጠው ነበር፤ እኛም ባመናችሁ ነበር፡፡
ከጠበቆች ከእምነት አባቶች እና ቤተሰብ (ወይም ከኤምባሲው ተወካይ) እንዲያገኘው እድል በተሰጠው ነበር፡፡
ዜጎች በሕግ እስካልተወሰነባቸው ድረስ እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብት (ሕገ-መንግስቱን መጥቀሴ በራሳቸው ሜዳ ለማሳጣት እንጂ ያከብሩታል በሚል የዋህነት አይደለም) በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 20.3 ዛሬም በፖሊስ ተጥሶ የሙስሊም አመራሮች እና ጋዜጠኞች ሽብርተኛ ተብለው ምስላቸው በአጃቢነት ቀርቧል፤ ግልጽ ባልሆነው ይቅርታ የተለቀቀው አርቲስት ደበበ እሸቱ (ሳይፈረድበት) የአሸባሪነት ማጀቢያ በመሆን ስሙ በድጋሚ እንዲጠፋ ሆኗል፡፡
የሚንቀውን ሕዝብ የሚያስተዳድረው ሕወኃት (ኢሕአዴግ) ልሳን የሆነው ኢብኮ (ኢቲቪ) እና የሌባና ፖሊስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ሕዝብ ደንቆሮ ነው ብሎ ያስባሉ፡፡
እኛስ የእነሱን ግምት በዝምታችን እያረጋገጥን እስከመቼ እንቆይ ይሆን?
————————————————————
የጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን አስተያየት:-
አንዳርጋቸው ጓደኞቹን ሰላም አላቸው 
ፍርድ ቤት የመቅረብ፣ ጠበቃ የማቆም፣ በቤተሰቦቹ ፣በወዳጆቹ የመጎብኘትና ሐኪም የማናገር መብቶቹን የተነፈገ ሰው በአፋኞቹ በተዘጋጀለት ቀረጻ (መቀረጹንም ካወቀ) የተናገረው ነገር በምን አግባብ በምርመራ ጥበብ የተገኘ ሊባል ይችላል?
እውነቱን ለመናገር አንዳርጋቸው ጽጌ በዛሬው ቪዲዩ በስም እየጠራ የጠቀሳቸውን ሰዎች እኔ የምቆጥረው የከበረ ሰላምታ እንደላከላቸውና ትግሉን የምር እንዲገፉበት እንዳበረታታቸው ነው፡፡
ፖሊስ በእሰረኞች አያያዝና በምርመራ ወቅት ይጠቀማቸዋል ስለሚባሉ ኢ ሰብዓዊነት የጎደላቸው ቴክኒኮች ውሸትነት ህዝቡን ማሳመን ከፈለገ
—ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራን ለህዝብ ክፍት ያድርግ እያንዳንዱ የምርመራ ክፍል ምን አይነት የምርመራ መሳሪያዎች እንዳሉት ጭምር ህዝብ ይመልከታቸው
–በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ የሚገኙና ከዚህ በፊት በወንጀል ምርመራው ያለፉ ዜጎች ገለልተኛ በሆነ አካል ምን እንደተፈጸመባቸውና እነማን እንደፈጸሙባቸው እንዲናገሩ ያድርግ
መቼም የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የሆኑት እነአቡበከር በፍርድ ቤት የተናገሯቸው ለጆሮ የሚሰቀጥጡ የጭካኔ የምርመራ አይነቶች የፖሊስ ፕሮግራሙ አቅራቢ እንደተናገረው የተፈጸሙባቸው በአይ ኤስ አይ ኤስ ወይም በአሜሪካን ወታደሮች አይደለም ፡፡እነአቡበከር ይህን ግፍ በሰውነታቸው ያሳለፉት በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ነው፡፡
—————————————–
የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አስተያየት:-
ህወሀቶች አቶ አንዳርጋቸውን ዛሬ አሳዩን። አሜሪካን ሚስጢር የምታስወጣው በማሰቃየት ነው እኛ ግን በፍቅርና በእንክብካቤ ነው የሚለውን እንድናምንላቸው የሄዱበት ዙሪያ ጥምጥም በራሱ ያደክማል። ለማንኛው አንዲን በማየቴ በግሌ ደስ ብሎኛል፡፡ በተቃዋሚዎች ዙሪያ ህወሀቶች እንዲናገርላቸው ያደረጉት የሚመስለው ግን ያው ቀድመን የገመትነው ነው። ገና ከዚህ የባሰውንም ሊያሳዩን ይችላሉ።
—————————————–
የጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ አስተያየት:-
ምዕራባውያን ሀገሮች- በሰላማዊና በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ጋር እንዲያደራድሩት ጥያቄ እንዳቀረበ በኢሳት በመነገሩ የተበሳጬው የኢህአዴግ መንግስት፤ በዛሬውፖሊስ ፕሮግራም መቶ ቦታ የተቆራረጠ የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግርና ምስል በማቅረብ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል። ወይ ጭንቀት!!!
አንዳርጋቸው፤ሁሌም ጀግና ነህ!!!
——————————
ሳም ቮድ ሶን አንዳርጋቸው የተባሉ ግለሰብ የሰጡት አስተያየት:-
ወያኔ አሁንም እንደለመደው ቆርጦ እና ቀጥሎ በ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ይሄንን ቪድዮ ለቋል እውነታው ግን እስካሁን ድረስ የ ኢንግሊዟ አምባሳደር ባለፈው ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት የት ቦታ እንደወሰዷቸው አና አካባቢውን የት ቦታ እንኳ እንደታሰረ እንደማያውቁ ባለፈው ገልፀዋል እናም ወያኔ ለፕሮፖጋንዳው እንዲመቸው አድርጎ ቆርጦ እና ቀጥሎ ይሄንን ቪድዮ ለቀቀ እውነት አንዳርጋቸው ምን ተጠይቆ ነው የተናገረው ለምን የጠያቂው ድምፅ እና ጥያቄው ምን እንደሆነ አያሰሙንም ደሞ ይህ ቪደዮ አሁን የተቀረፅ ለመሆኑ ምንም አይንአይንተ ማስረጃ የለም::
———————————–
የሁኔ አቢሲኒያ አስተያየት:-
በዛሬው እለት በፖሊስ ፕሮግራም የተለቀቀው የጋሽ አንዳርጋቸው ጽጌ ቪዲዮ ጋሽ አንዳርጋቸው ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት ያስታውቃል።
ከሞቀ ኑሮው መካከል ስለህዝቡ ሲል እንዲህ ይሰቃይ? እስከመቼ ጀግኖቻችንን ለጅብ ሰጥተን ልንተኛ ይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ምርመራ የምናደርገው ሰብአዊ በሆነ መልኩ ነው እያለን ነው – የወያኔ ፖሊስ::



No comments:

Post a Comment