Translate

Friday, January 9, 2015

የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?)

ዳዊት ከበደ ወየሳበሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ "ገ'ጨው" በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል:: ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱ አሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል:: የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት - አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው - በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው::

ሰሞኑን ግጭቱ ከመባባሱ በፊት የአማራው ህዝብ ተዋጊዎች - ህወሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር:: ሆኖም የህወሃት ወታደሮች አካባቢውን ለቅቀው ባለመሄዳቸው በተለይ በማይ'እምቧ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ - ህወሃት አባላት ሞተዋል:: በወያኔዎቹ ላይ የደረሰው አደጋ ያስደነገጣቸው እና ወደ አርማጭሆ ያመሩት ሌሎች የህወሃት አባላት - ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ጦርነት ሲያደርጉ ነበር የከረሙት:: በዚህ ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም የተኩስ ልውውጡ ከፍተኛ ነበር:: አሁን የመከላከያ ሰራዊት በሁለቱ ወገኖች መካከል ከሰፈረ በኋላ ግን ጦርነቱ ለጊዜው ጋብ ብሏል:: ሆኖም ሁለቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች - ማለትም የህወሃት እና ብአዴን አመራሮች ውስጥ ውስጡን እየተናቆሩ ናቸው::



 ህወሃት በድንበር ጉዳይ ካደረጋቸው የአገር ውስጥ ጦርነቶች ይሄኛው ጠንከር ያለ ነው:: ከዚህ ቀደም የህወሃት ወይም የትግራይ ታጣቂዎች የአማራውን መሬት ሲወስዱ - ህዝቡ "በህግ አምላክ" ብሎ እየጮኸ ከመሞት ውጪ ብዙ ምርጫ አልነበረውም:: አሁን ግን እየጮኸ ሳይሆን ጥይት እያጮኸ መሞትን የመረጠበትን አጋጣሚ ለማየት እየበቃን ነው:: አሁን የደረንበትን የቅርቡን ታሪክ እንዳየነው ከሆነ - ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የአማራውን ህዝብ ከሁመራ እና ጠለምት: ከበየዳ, ከወልቃይት, ከድብ ባህር, ከአብደራፌ, ከብራ ዋድያ, ከሻግኔ እና ላሄን እያፈናቀሉ መሬቱን ለቀድሞ የወያኔ ወታደሮች ሲሰጡ ቆይተዋል:: በአካባቢው የአማራው መሬት ብቻ አይደለም ተወሰደው:: ወንዶቹን እያፈናቀሉ: ያንገራገረውን እየገደሉ ሚስቶቻቸውን እና ሴት ልጆቻቸውን በሙሉ ነው ነጥቀው የወሰዱት:: [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment