Translate

Thursday, January 1, 2015

አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ?

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የተመሠረተበትን አርባኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበትና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ የሀገሪቱ የገንዘብ ወጭ ተደርጎBereket-Simonአስረሽ ምችው የሚደለቅበት ሰአት ላይ ያለን ሲሆን የዘድሮው በዓል አከባበር ደግሞ የተለየ ሆኗል አስቀድመው ነው የጀመሩት ያም ሆነ ይህ በዓሉ ለምን ይከበራል? የሚያከብረውስ ማን ነው? ብለን ስንጠይቅ ድርጅቱ በጫካ አሥራ ሰባት ዓመት በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በኋላ በከተሞች ለሃያ ሦሥት ዓመታት ያህል የምሥረታ በዓሉን በከፍተ የገንዘብ ወጭ እያከበረ ዘልቋል።በዓሉ የሚከበርበት ምክንያት፦ ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሳበት ዓላማ ግቡን እየመታ በመምጣቱ፤ ከዚህ ግቡ የማይባሉ ሰዎችን ለሀገር ሥልጣን በማብቃቱ፤ጥቂቶቹን ሚሊየነር በማድረጉ፤የድርጅቱን ዓላማ የሚቃወሙትን እያወደመና እየበላ በመምጣቱ፤ ከሀገር እንዲሰደዱ በማድረጉ እንዲሁም አሰቃቂና ጭካኔ በተሞላበት ድብደባና እንግልት በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ፤ጋዜጠኞች፤ ጦማርያን፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ ተማሪዎች፤አስተማሪዎች፤ ነጋዴዎች፤አርሶ አደሮች ወህኒ ቤት ወርደው እንደ ብረት እየተቀጠቀጡ የሚገኙበት፤የሀገር ሀብት ተንጠፍጥፎ ካዝናው ባዶ እስኪሆን ድረስ ተጠርጎ ወደ ውጭ አገር ተልኮ በጥቂት ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው የግል ባንክ አካውንት በመቀመጡ፤ ከአጎራባች አገሮች ጋር የሚዋሰነው የኢትዮጵያ ለም መሬት በገፀ-በረከትነት የኢትዮጵያ ጠላት ለሆኑ አገሮች በመሰጠቱ፤በኢንቭስት-መንት ስም ነዋሪው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እየተፈናቀለ መሬት ለውጭ ባለሀብት ያለምንም ክፍያ በመሰጠቱ፤ የንግዱም ሆነ የግብርናው ዘርፍ ሕዝብ የማይሳተፍበትና በባለሥልጣናት እጅ የገባበት፤አገሪቱ ወደብ አልባ የሆነችበት፤ አንድነት የጠፋበትና ለዘመናት አብረው በሰላምና በፍቅር በአንድነት የኖሩ ነገደ ኢትዮጵያውያን በጥርጣሬና በጥላቻ የሚተያዩበት ሁኔታ በመፈጠሩ፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ የተረገጠበት ላይ በመድረሱ ህወሃትና ጋሻ ጃጌዎችን የሚያስደስት ተግባር ከዚህ በላይ ስለማይኖር በዓሉ ይከበራል።

ይህን የህወሃት በዓል የሚያከብረው ማን ነው? የህወሃት አባላት፤ አመራርና ጋሻ-ጃግሬዎች ምስኪኑን ሕዝብ በቀጭን ትዕዛዝ በኃይል ተገዶ እንዲወጣ በማድረግ ሲሆን እምብኝ አልወጣም በዓሉ የኔ በዓል አይደለም ያለውን ደግሞ በታጠቀ ኃይል በመሣሪያ ጀርባውን፤ ግንባሩን በጠመንጃ አፈሙዝ እየተገጨ እንዲወጣ በማስገደድ ነው በዓሉን የሚያከብሩት። ከህወሃት አምባገነናዊ ባህርይ መልካም ነገር የማይታሰብ ቢሆንም ህወሃት ለተነሳበት እኩይ ዓላማ ፀንቶ የቆመ በመሆኑ በዓሉን አታክብር ማለት የዋህ የሚያስብል ይሆናል።ነገር ግን ይህን ጠባብና ዘረኛ ሥርዓት ማስወገድ አለብኝ የሚሉ ኃይሎች በዓላማቸው ፀንተው አንድነት ፈጥረው ትግል አለማካሄዳቸው ህወሃትን ለዚህ ያበቃው መሆኑን ግልጽ አድርጌ ማለፍ እወዳለሁ።ሕዝቡ በቃኝ ካለ ሰንብቷል፤ አመጽ ያረገዘ ሕዝብ ከየአቅጣጫው እየሰነዘረ ያለው ርምጃ የተቃዋሚ ኃይሎችን የሕዝቡ ትግልና አመጽ ጭራ አድርጓቸው እየታየ ነው።ስለዚህ የተቃዋሚ ኃይሎች (ድርጅቶች)ሕዝብ እየሄደበት ባለው ፍጥነት በመሄድ የማደራጀት ተግባር መቅደም አለበት ብየ አምናለሁ ወይም ይጠበቅባቸዋል።ይህ የሚያግባባን ከሆነ መነሻ ወደ አደረኩት ርእሴ ተመልሸ ከበረከት ህብረ-ብሄራዊ ድርጅት መቆም አልቻለም።ውሎ አድሮ ደግሞ ኢህአዲግ በሚል የጋራ ግንባር ሥር ገብቶ ወደቀ መጥፎ ቀን የኢህዲን ታጋይ ባመናቸው መሮዎቹ ሊወጣ ከማይችልበት እሥር ቤት ገብቶ የህወሃት ጥቅም አስጠባቂ ሆነ።እነዚህ ከላይ ስማቸውን የጠቀስኳቸው ግለሰቦች የታገሉት የአማራው ነገድ ሕዝብ በሚኖርበት አካባቢ ሲሆን አማራ ስለአልሆኑ ኃላፊነት በጎደለው መንፈስ የአማራውን ነገድ ሕዝብና አብሯቸው ይታገል የነበረውን ትውልደ አማራ እየበሉና እያስበሉ የመጡ የእናት ጡት ነካሾች ናቸው። ይህ አይነት የግድያ ተግባር በደርግ ጊዜ የተጀመረ ብቻ ሳይሆን ደርግ ከወደቀ በኋላም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የመጀመርያው ዘመቻ አማራውን ማስወገድ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ በኦሮሞው ላይ ይሆናል። የዚህን ጅማሮ እየተመለከትነው ነው።
4ኛ/ ህወሃት አንድ የሚመፃደቅበት አንድ ትራጀዲ አለ እሱም የብሄር ብሄረስቦችን መብት አረጋግጫለሁ የብሄር ብሄረሰቦች ምክር ቤት አቋቁሜ ያለሁ የሚለው ፈሊጥ ነው።እያንዳንዱ ብሄር ብሄረሰብና ጐሣ ወይም ነገድ ሕዝብ በሰላም ውሎ እንዳያድር የዲሞክራሲና የፍትህ፤የእድገት፤ የእምነት ጥያቄዎችን እንዳያነሳ እርስ በርስ እያናከሳቸው ይገኛል።በአጭሩ ለማሳየትም ሁለት ምሳሌዎችን ልጥቀስ በኢትዮጵያ ሶማሌና አፋር ክልል ግጭት ተፈጠረ የግጭቱ ፈጣሪ ራሱ ህወሃት ሲሆን የተሰጠው መፍትሄ ደግሞ በጣሙን የሚገርምና በሁለቱ ሕዝቦች መሀከል ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና ተባብሶ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። ሶሞኑን በአማራና በትግራይ አጎራባች ክልሎች የተፈጥረው ግጭት ሆነ ተብሎ በህወሃት የተፈበረከ ሲሆን ከሁለቱም ወገኖች ደም እንዲፈስ ንብረት እንዲወድም እስከወዲያኛው የማያገናኝ ተግባር እየተፈፀመ ይገኛል። ድርጊቱን የሚያስፈጽሙት እንደ እባብ ገላ ማንነታቸውን አውልቀው የጣሉ የለየላቸው ሆዳም የህወሃት ጀሌዎች አማራዎችና የወረራው ፊታውራሪ ህወሃት መሆናቸው ቢታወቅም ሰፊው የትግራይና የአማራ ነገድ ሕዝብ እንደ ድሮው እንደ ጥንቱ በአገራችን ባህል መሠረት የተጫረውን እሳት ሊያበርዱት ይገባል።በተለይ የትግራይ ሕዝብ ህወሃት ለአርባ ዓመታት ያህል መጠቀሚያ አድርጐ የተጠቀመበት ሲሆ ዛሬም ባድማው ባዶ እንዲሆን ከኤርትራ ሕዝብና ከአማራ ሕዝብ ጋር በማጋጨት ሰላምህን እያደፈረሱ ስለሆነ በቃችሁ በላቸው።
በመጨረሻም አቶ በረከት እሱን መች ጠየቅንህ በሚል የጀመርኩት ብእዴንም ወያኔዎች (ወየንቲ) ነን ብሎ የተናገረውን ሰምቼ ነው። ህወሃትን ከሚገባው በላይ ሲያወድስ ብእዴን እንዴት ይንከባከቡት እንደነበር ሲደርት ብእዴን የመጣ አሁን በዚያ ወቅት የነበረው ኢህዲን ይህንም መለየት ከማይችልበት የደረሰ ይመስለኛል ታናንት **ህወሃት የታገለው የአክሱማዊ ዳይናስቲን ለመመለስ አይደለም ** ያለው ጀግና ዛሬ ድመት እጅ እንደገባች አይጥ በጣም አንሶና አድርባይነቱን ሊሸፍን በማይችል መልኩ ሲዘላብድ ደደቢት ላይ ሆኖ የተወራ ወሬ ወይም ድስኩር አይሰማም ብሎ አስቦ ወይንስ አንዳች ነገር ወርዶበት? ህወሃት በዓሉን የሚያከብረው በየካቲት ነው ዘንድሮ አስቀድሞ ወደ ደደቢት ሄዶ ያን ያህል ውሽከታ ሲደረግ ግርምት ጥሎብኝ ነበር።
በረከት፦ ላንተ የሚቀርብህ ሻእብያ እንጅ ህወሃት አይደለም ብአዴን ልትሆንም አትችልም ምክንያቱም አንተ የሞቱት እማ ብሬና የአባ ገብረእግዚአብሔር ልጅ ነህ እነሱ ደግሞ ጥርት ያሉ ጨዋ ኤርትራዊ ናቸው ታዲያ አንተ ብሔረ አማራ ሆነህ እንዴት ነው አማራውን የምትወክለው? ይህን ነው መመለስ የሚገባህና የምንጠይቅህ ስለህወሃት ጀግንነት ስለደርግ ጨቋኝነት አንተ አትነግረንም ይልቁንስ አንተን ጨምሮ ከጌቶችህ ጋር የምታራምዱት ሥርዓት ምን እንደሚመስል ለማሰብ ሞክር። ወጣት ሴቶችና ወንዶች በዘመናዊ ባርነት ሥር እንዲወድቁ የሚያደርግ ህጋዊ የደላላ ጽ/ቤት ከፍቶ ስደትን የሚጠራ መንግሥት፤ በተለያየ ሱስ ተለክፈው መደበኛ ተግባራቸውን እንዳይፈጽሙ የሚያደርግ መንግሥት፤ በዓረብ አገር ያሁሉ ግፍ ሲፈጸም፤ ወደ ዓረብ አገር ለመሄድ በሽዎች የሚቆጠሩ ባህር ላይ ሰምጠው የአሳ ቀለብ ሲሆኑ ከየአቅጣጫው በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ሲደርስ ያንተ መንግሥት አንድም የደረሰ ጉዳት የለም፤ የሞተ፤የታሰረ የለም ብሎ ሞግቶናል የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን ጋዜጠኞችን፤ ጦማርያንን፤ ተማሪዎች አስተማሪዎችን ነጋዴውን፤አርሶ አደሩን የሃይማኖት መሪዎችን ማሰር መግደል አስሮ ማሰቃየት የሚል መርህ የሚያራምድና የዘረጋ ጭፍን አስተሳሰብ ከሚያስቡትና በቀልተኝነትን ከሚገፉት አንዱ አንተ ነህ ምናልባት ባንተ አመለካከት እንደ ኤርትራዊነትህ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ጥቃትም ሆነ ጉዳት ላይሰማህ ይችል ይሆናል ደግሞም ትክክል ነው። እኛ ግን እንጠይቅሃለን ማተብህን ከፈታህ ወዲህ በአስፈጃቸው አማራዎች ሁሉ እንጠይቅሃለን፤የመንግሥት ሥልጣንን መከታ በማድረግ በአባቶቻችን ደምና አጥንት ተከብሮ የኖረውን ዳር ድንበራችን በማስደፈርህ እንጠይቅሃለን፤አንዱን ጐሣ ከሌላኛው ጐሣ ጋር በማጋጨት ደም በማፋሰስህ እንጠይቅሃለን፤ ምስኪን አብሮ አደጐችህን የትግል ጓዶችህን ጊዜ ጠብቀህ ስለበላሃቸው እንጠይቅሃለን። ብአዴን እንዲፈርስ አንተም ከአማራ ሕዝብ ትካሻ እንድትወርድ ሌሎችንም እንዲወርዱ እንጠይቃችኋለን ፤የአማራ ዘር እንዲመክን በማድረግህ እንጠይቅሃለን።ለዛሬው ይህ ይበቃሃል ደጋግመህ አንብበው አያ በረከት።
ነብሮ ነኝ ከሰ/አሜሪካ

No comments:

Post a Comment