Translate

Wednesday, June 19, 2013

ይድረስ ለአለምነህ ዋሴ፣ የአሜሪካ « ሰይጣን» በአገራችን?

ከኢየሩሳሌም አርአያ

ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያዬ ወጥቼ ጥቂት እንደተጓዝኩ ሁለት አሜሪካዊያን ወጣቶች ከፊት ለፊቴ ሲመጡ ተመለከትኩ። እጅ ለእጅ ተያይዘዋል…በጥንቃቄ ምስላቸውን ለማስቀረት ሞከርኩ።… ( ወንድ ከወንድ- ሴት ከሴት፣ እጅ – ለእጅ መያያዝና መተቃቀፍ ግብረ-ሰዶማዊነትን ያመለክታል በአሜሪካ)… ታዲያ ምንድነው?.. ትለኝ ይሆናል፤… ይህ «ሰይጣናዊ» የነአሜሪካ «ቁሻሻ» በአገራችን መስፋፋቱ አሳስቦኝ ነው። የ11 እና 10 አመት ታዳጊ ሕፃናት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ ት/ቤት ዳይሬክተሩን ጨምሮ 6 አስተማሪዎች እየተፈራረቁ «ሰይጣናዊ» ድርጊት ሲፈፅሙ እንደከረሙ መስማት አያስጨንቅም?… ለትምህርት የላከው ልጅህ ያውም በአስተማሪዎች እንዲህ አይነቱ ርካሽ ተግባር ሲፈፀምበት ምን ይሰማኻል?… «14ሺህ ግብረሰዶማዊያን በኢትዮጲያ አሉ» ተብሎ በአንድ ወቅት የተነገረውን ስትሰማ ምን አልክ?…ምነው ቤቲ ላይ በረታህ?… እርግጥ ነው ቤቲ የሰራችው ከአገራችን ባህል ጋር የሚጣረስ ነው!! ይህ አያከራክርም።
ግን ቤቲ አረብ አገር እንደሚሰቃዩት እህቶቻችን እጣ ቢገጥማት… ይህን ያክል ትጮህላት ነበር?… በቅርቡ አረብ አገር ቁልቁል ተዘቅዝቃ ደም እየተፋች ስትገረፍ የነበረችው (ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ ለጥፎት ነበር) እህታችን ሰቆቃ የሚሳየውን ቪዲዮ አይተኸዋል?… እንኳን ልታየው ከቁም ነገር ከተኸዋል?… ከ10 አመት በፊት ሟቹ ጠ/ሚ/ር በአዲስ አበባ ያለውን ሁኔታ ሲገልፁ «ሶስት መቶ ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች በከተማዋ አሉ» ብለው ነበር። ማን የፈጠረው ችግር ነው?… ቤቲ የዚሁ አካል አይደለችም?… ሌሎቹ አደባባይ ስላልወጡ ነው?… ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ፥ የምታገለግለው ስርአት ይህን ሁሉ ችግር እንደፈጠረ ጠፍቶህ አይደለም። በስደት ስለሚያልቁትና ስለሚሰቃዩት እህትና ወንድሞቻችን አንድም ቀን ትንፍሽ ሳትል… ቤቲ ላይ ዘመትክባት። ሃቁ ግን የኢኮኖሚ ድቀት የፈጠረው ነው!!… ስለ «ሰይጣናዊው» አደገኛ የባህል ወረርሽኝ ትንፍሽ አላልክም። ለምን?… ወገኖቼ የቱ ያስጨንቃል?…

No comments:

Post a Comment