Translate

Tuesday, July 2, 2013

ኢትዮጲያ ፍረጂ!!….(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ኢትዮጲያ ፍረጂ!!
እነዚህ ሁለት ሕፃናት በቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀን ከወላጆቻቸው ጋር « አንበሳ ግቢ፣ ህፃናትና ወጣቶች ትያትር፣ መጫወቻ ባለባቸው የመዝናኛ ስፍራዎች…» ወዘተ ለመሄድ አልታደሉም። ይልቅስ በነዚህ ቀናት ሕፃናቱ ቃሊቲና ዝዋይ እስር ቤቶች እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል። ንፁሃን በሆኑት የሁለቱ ሕፃናት አባቶች ላይ ሕገ-ወጥና ጭርሶ ተቀባይነት የሌለው የፈጠራ ክስና ፍርድ በማሳለፍ – በነዚህ ሕፃናትም ላይ በቀጥታ ፍርዱ እንዲያርፍ ተደርጓል።
ሕፃናቱ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ልጆች ናቸው። እነዚህን ሕፃናት የሚቀጡት ወይም የሚያሰቃዩት የገዢው ባለስልጣናት በአንፃሩ ልጆቻቸውን ከአገርና ህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ልጆቻቸውን፣ የስጋ ዘመዶቻቸውን ልጆች ጭምር አንቀባረው በአውሮፓና አሜሪካ ያስተምራሉ፣ ያኖራሉ። አዜብ መስፍን በተንደላቀቀ ሁኔታ በአውሮፓ ከሚያስተምሯቸው ልጆቻቸው በተጨማሪ የእህታቸው ልጅ በዋሽንግተን ዲሲ ተንቀባሮ ይኖራል፤ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በ6 ሚሊዩን ብር በ95ዓ.ም በስሙ ቪላ ተገዝቶለት ለልድቱ በስጦታ መልክ ከአዜብ ተበርክቶለታል፤ (የቪላው ቤት ቁጥር ጭምር ተጠቅሶ በኢትኦጵ ጋዜጣ በወቅቱ ይፋ ተደርጓል).. ላለፉት 10 አመታት ተከራይቶ ገንዘቡም በስሙ ባንክ ይገባለታል። የሁለት ጄነራል ልጆች በተርም 28.000 ዶላር እየተከፈለላቸው በዲሲ መማርና መኖር ከጀመሩ 8 አመት ተቆጠረ። (አንዱ ጄ/ል ከልጁ ጋር የተነሳው ፎቶ በእጄ ይገኛል) ..የሁለት ሚ/ሮች ልጆችና ቤተሰቦች በካሊፎርኒያና አካባቢዋ የተንደላቀቀ ኑሮ ይመራሉ። ብዙ…ብዙ ነው ጉዱ!!!! ኢትዮጲያ ፍረጂ!!!!

No comments:

Post a Comment