Translate

Wednesday, July 3, 2013

አውራምባ ታይምስ እንደ ወንዴ ንብ አንዴ ተኩሶ ሞተ!

አዜብ ጌታቸው

ከሁለ አስቀድሜ ሰላምና ጤና ለዲሞክራሲ ናፋቂው ወገኔ እመኛለሁ። ወድ አንባቢያን ሆይ! የዛሬው መጣጥፌ ወይም አስተያየቴ የሚያጠነጥነው፦ ጥቂት ከማይባል ወራት ጀምሮ የተወለጋገደ አካሄደና የተንሸዋረረ አመለካከቱ አነጋጋሪ ሆኖ የቆየው፤ በቅርቡ ግን የመወለጋገዱም ሆነ የመንሸዋረሩ ምክንያት ምን እንደሆነ ግልጽ በሆነው በአውራምባ ታይምሱ ባለቤት በጋዜጠኛ ዲዊት ከበደ ዙሪያ ነው።
ዳዊት ከበደ በምርጫ 97 ማግስት የወያኔ መንግስት ሽንፈቱን አልቀበል ብሎ በወሰደው የኃይል እርምጃ ወደ ዘብጥያ ከተወረወሩት የአሸናፊው ፓርቲ አመራሮች ጋር አብረው ለእስር ከተዳረጉት የነጻ ሚዲያው ባልደረቦች አንዱ እንደነበር ይታወቃል።
Journalist Dawit Kebede, Awramba Times editor
ለ20 ወራት በዘለቀው እስር ቃሊቲ ቆይቶ ከተፈታ በኋላ፦ አዲስ ፈቃድ አውጥቶ አውራምባ ታይምስን ማሳተም ጀመረ። ለዳዊት ከበደ የተሰጠው ፈቃድ በግዜው እንደሱው ከእስር ለተፈቱት ሲሳይ አጌናና ዛሬም በእስር ለሚገኘው እስክንድር ነጋ መከልከለ ጥርጣሬ ያጫረ ቢሆንም ለንባብ የበቃቺው የአውራምባ ታይምስ ይዘት ጥርጣሬውን አደበዘዘው። ዋና አዘጋጇ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በሽብርተኝነት ተከሶ ሲታሰርና እሱንም ተከትሎ ማኔጂንግ ኤዲተሩ ዲዊት ከበደ እስከተሰደደበት ግዜ ድረስ አውራምባም መንግስትን ስትፈትን ቆየች ….

በነገራችን ላይ ዳዊት ከበደ በቅርቡ ትታሰራለህ የሚል መረጃ ስለደረሰኝ ሃገር ለመልቀቅ ተገደድኩ ብሎ ከኢትዮጵያ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ከመብረሩ ጋር በተያያዘ፦ በግዜው የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘሩ እንደነበር አስታውሳለሁ። ገሚሶቹ ዲዊት ለሽልማት ወደ አሜሪካ በመጣበት ግዜ የተሰጠው የአንድ አመት ቪዛ ከመቃጠሉ በፊት አሜሪካ ለመግባት ፈልጎ እንጂ ከመንግስት አካላት ትታሰራለህ የሚል ምንም ማስፈራሪያ አልደረሰውም የሚለ ሲሆኑ፤ አንዳንዶቹም ምንም ይሁን ምን የጋዜጣውን ባልደረቦች በትኖ ራሱን ለማዳን መሮጡ ራስ ወዳድነት ነው ሲሉ ይወቅሱት ነበር። ይቀጥላል… (Read More..)

No comments:

Post a Comment