Translate

Wednesday, July 3, 2013

አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ

ከኢየሩሳሌም አርአያ

Former Prime Minister Tamrat Layneበአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ወገኖች፣ ታምራት ያንን ቢናገሩም በቃላቸው ግን እንዳልተገኙ አስረድተዋል።
« የኢየሱስ አገልጋይ ሆኜ እኖራለሁ» ያሉት ታምራት አሁን ወደ ንግድ አለም መግባታቸው እንዳስገረማቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ሌላው ቢቀር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ለሰሩት ጥፋት ህዝብን ይቅርታ ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ በይፋ አደባባይ ወጥተው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ገብሩ ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል። አቶ ታምራትና አቶ ስዬ ግን ይህን ለማድረግ ጨርሶ እንደማይፈልጉ ከያዙት አቋም በቀላሉ መረዳት ይቻላል ብለዋል።
በሌላም በኩል የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የነበሩትና ደቡብን በበላይነት ሲያሽከረክሩ ቆይተው በ1993ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተከሰው የታሰሩት አቶ ቢተው በላይ ለስድስት አመት ታስረው ከተፈቱ በኋላ በአቶ መለስ ዜናዊ የአፋር ክልል አማካሪ ተደርገው ተሹመው እንደነበረ ምንጮች አጋለጡ። ከአቶ አባተ ኪሾ ጋር ተከሰው የነበሩትና ከሕወሐት ተገንጥሎ ከወጣው <አንጃ> ቡድን አንዱ የነበሩት አቶ ቢተው ተመልሰው የመለስ አገልጋይ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአፋር ክልል አማካሪ ሆነው ለሶስት አመት የሰሩት ቢተው በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሎጅ ተዛውረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። የአቶ ቢተው ወንድም ኮ/ል ሲሳይ (በቅፅል ስሙ ሃመዴ) ጀግና ኢትዮጲያዊና አገሩን የሚወድ ታታሪ እንደነበርና በአሰብ ውጊያ ከነሂሊኮፕተሩ ጋይቶ ማለፉን ምንጮቹ አመልክተዋል። አንድም ቀን ስሙ በነመለስ ተነስቶ የማያውቀውና የጡረታ መብቱ እንኳ ሊከበርለት ያለቻለው ሟቹ ኮ/ል ሃመዴ ልጆቹ ያለአሳዳጊ ተበትነው መቅረታቸውን ምንጮቹ ሳይገልፁ አላለፉም።

No comments:

Post a Comment