Translate

Monday, June 3, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

skypeከእስረኞች ጠበቆች ጋር የተደረገው ውይይት ታፈነ
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን  በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር።

አቶ ኦባንግ ሜቶና የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ፣ ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር አራት፣ ከአዲስ አበባ ሰባት ጠበቆች በመሆን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የስካይፕ ውይይት ለመጀመር ተዘጋጅተው ነበር። የጋራ ንቅናቄው እንዳስታወቀው ውይይቱ ሲጀመር ድምጽ መስማት አልተቻለም።
በዚሁ ሳቢያ ውይይቱ መቋረጡን ያስታወቀው አኢጋን ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር ጋር በመነጋገር  ሰኞ ቀን በውል በማይገለጽ ሰዓት በሌላ መልኩ ውይይቱን ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን አመልክቷል። የአሜሪካ ህግ ባለሙያዎች ማህበር ኢህአዴግ ያለ አግባብ አስሮ የሚያሰቃያቸውን ዜጎች ጉዳይ አደባባይ ለማውጣትና አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ይቻለው ዘንድ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ጋር አብረው ለመስራት መስማማታቸውን መግለጻችን ይታወሳል። በዜናው አሁን የተጀመረው ስራ የስምምነቱ መጀመሪያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

እሁድ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ በፌስቡካችን ወቅታዊ መልዕክቶችንና ፎቶግራፎችን ስናትም ነበር፡፡ ከዚያ ላይ የሰበሰብነውን ባጭሩ ይህንን ይመስላል፡፡
በአዲስ አበባ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
አፋኝ ህጎች ይሰረዙ፣ አገራችን አትበታተንም፣ የታሰሩ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ይፈቱ የሚሉና ሌሎች ተመሳሰይ መፈክሮችን በመያዝ ጎዳና ሞልተው አልፈዋል።3
ኢትዮጵያ ሃገሬ የሚል ዜማ በማዜምና የመብት ጥያቄዎችን በማስተጋባት የተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ሰልፍ ያዘጋጀው ሰማያዊ ፓርቲ ሲሆን፣ ፓርቲው በእድሜ ከሁሉም ፓርቲዎች ታናሹና በወጣት አመራሮች የሚመራ ነው ። ሰልፉ ከቅንጅት የ1997 ሰልፍ በኋላ የተካሄደ ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት ነው።
ኢህአዴግ ፖርላማውን መሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሬያለሁ በሚልበት ሁኔታ ይህን ያህል ሰፊ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ አዳባባይ መውጣቱ ወደፊት ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ቢዘጋጅ ህዝቡ ጎዳና ሊያጣብብ እንደሚችል የሚያመለካክት ነው።
ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡
መንግስት በ3 ወር ውስጥ ጥያቄያችንን ካልመለስ በተጠናከረ መልኩ ድምፃችንን እናሰማለን! (ሰማያዊ ፓርቲ)
ያለ አግባብ የታሰሩ የፖለቲካ የሀይማኖት እና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፤ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአግባቡ እንዲመለሱ እና አፈናቃዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የኑሮ ውድነቱ አስተማማኝ እልባት እንዲሰጠው እና ሌሎችንም ጥያቄዎች አንግበው ዛሬ ኩባ አደባባይ የተገናኙት ኢትዮጵያውን ሰላማዊ ሰልፋቸውን በሰላም አጠናቀቁ!
8ሰልፉ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ የተከናወነ ሲሆን ቀበና ከሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት አንስቶ በአራት ኪሎ በፒያሳ እና በቸርቸር ጎዳና ሄዶ መድረሻውን ኩባ አደባባይ አድርጓል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በሰልፉ ላይ መንግስት በ3 ወር ጥያቄያችንን ካልመለሰ በተጠናከረ መልኩ ድምፃችንን እናሰማለን ብሏል፡፡
ሰልፉ በሰላም በመጠናቀቁ የተሰማኝን ደስታ በዚህ አአጋጣሚ እገልፃለሁ በሌላ አጋጣሚም እደግመዋለሁ. ከተለያዩ ድረ ገጾች ሰማያዊ ፓርቲን በመጥቀስ የተሰራጨ፡፡
“ሽብርተኞች እንዴት ናቹህ?” ይህ ቃል የተሠማው በዛሬው ሠላማዊ ሠልፍ ላይ ከኢ/ር ይልቃል ነው
በሠልፉ ላይ እነዚህ ድምፆች ተሠምተዋል
“ዘረኝነት ይወገድ”
“የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ይፈቱ”
“የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና ጋዜጠኞች ይፈቱ”
“የተባረሩ መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሱ”
“ወኔ የሌለው የሀገር ሸክም ነው”
“አንድ አትየጵያ”
“ዜጎችን ከቀዬአቸው ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው”
የሚሉት ብሶቶች ተሠምተዋል
በመጨረሻም ሠላማዊ ፓርቲ መንግስት የሕዝቡን ጥያቄ በሶስት ወራት ውስጥ ካልመለሠ ፓርቲው የራሡን እርምጃ ለመውሠድ እንደሚገደድ ሊቀመንበሩ ገልፀዋል:: በመልዕከት ሰልፉ ላይ ከተገኙ የጎልጉል ወዳጆች የተላከ፤ እናመሰግናለን!!
“በናይል ጠብታ ውሃ ቀልድ የለም”
ባለፈው አርብ የጁምአ ቀን በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ውስን ቁጥር ያለቸው ግብጻዊያን “የናይል ምንጩ እኛ ነን፣ የናይል ወንዝን ለመንጠቅ የሚደረግን ሙከራ እንቃወማለን” የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
የተቃውሞው ሰልፍ የተካሄደው ኢትዮጵያ እየገነባች ላለው ግድብ የአቅጣጫ ማስቀየር ስራ መስራት መጀመሯን ተከትሎ ነው። 4.7 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚያስወጣው ግድብ በ2050 እአአ 150 ሚሊዮን የሚደርሰውን የግብጽ ህዝብ አደጋ ለይ ይጥለዋል የሚል ስጋት አለ። የናይል ውሃ ዋና ምንጩ ኢትዮጵያ ሆና ሳለ አታለሙም ማለት የማይታሰብ ነው ሲሉ አቶ በረከት ለአልጀዚራ ተናግረዋል።nile egypt
ከግድቡ ጋር በተያያዘ በቅርቡ በአባይ ወንዝ ላይ የተደረገው የአቅጣጫ ለውጥ በግብጽ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የለውም በማለት የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን  ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምህረት ደበበ መናገራቸውን ፋና ኢቲቪን ጠቅሶ አስታውቋል። የወንዙ አቅጣጫ መቀየር በግብጽ ላይ ችግር ያመጣል በሚል የሚናፈሰው መረጃ ሳይንሳዊ አይደለም፣ 60 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚገመተው የአባይ ወንዝ የውሃ መጠን ላይም በአቅጣጫ መቀየሩ ምክንያት ምንም አይነት ለውጥ አይኖርም በማለት አቶ ምህረት አመልክተዋል። አያይዘውም ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰሱ አገሮች ላይም ምንም አይነት ችግር እንዳይፈጥር በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
አቶ ምህረት ይህንን ቢሉም የግብጽ የውሃ ሚኒስትር ዛቻ ሰንዝረዋል። “በናይል ጠብታ ውሃ ቀልድ የለም” በማለት “ሁኔታው ይጠና ማለት ለግንባታው ስምምነት መስጠት ማለት አይደለም” በማለት መናገራቸውን All Africa አስነብቧል። የግብጽ የተለያዩ ባለስልጣናትና ተቃዋሚዎች ዛቻ ከመሰንዘር ይልቅ ጉዳዩን በዲፕሎማሲው መንገድ ማስተናገድ እንደሚሻል የሚመክሩ የግብጽ ዜጎችም በተለያዩ ድረገጾች አስተያየታቸውን እየወረወሩ ነው።
52 ተጠርጣሪዎች ከተከሳሽነት ወደ ምስክርነት
የፌደራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ ሳያሰባስብ ክስ መስርቶ ይረታል በሚል የሚታማ ተቋም ነው። ኮሚሽኑ ከጊዜ ወደጊዜ አቅሙንና ልምዱን በማዳበር ከዚህ ችግር መውጣቱን በዳታ አስደግፎ በመግለጽ ይከራከራል። አንድም ሰው ቢሆን ለምን ያለ በቂ ማስረጃ ይታሰራል ለሚለው የሰብአዊነትና የመብት ጥያቄ ያለመረጃ አስሮ ሲረታ ካሳ ስለመክፈሉና ላጠፋው ጥፋት የሚመጥን ቅታት ስለመቀጣቱ ተሰምቶ አያውቅም። የዘወትር ቅዳሜው ጋዜጣ አዲስ አድማስ በዚህ መልኩ ይሁን በሌላ አንድ አስገራሚ ዜና ይዞ ብቅ ብሏል።
corruption vs reformከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር በተያያዘ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ካካሄደባቸው 125 ተጠርጣሪዎች መካከል በ58 ላይ ክስ ሲመሰርት 52ቱ ከክስ ነፃ ሆነው በምስክርነት እንዲቀርቡ ሊደረግ መሆኑን ምንጮች ገልጾ አዲስ አድማስ አስታውቋል። በምስክርነት ለመቅረብ ተስማምተው ከክስ ነፃ ከሆኑት ምስክሮች መካከል አምስቱ ባለሃብቶች መሆናቸውና ሌሎቹ ደግሞ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን እንዲሁም በተጠርጣሪ ባለሃብቶች ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ መሆናቸውን አዲስ አድማስ አስታውቋል። ጋዜጣው ቀንጭቦ ያሰራጨው ዜና ሰዎቹ አስቀድሞ የታሰሩበትን ምክንያት አመልክቷል።
ከክስ ነፃ የሆኑት ምስክሮች ከሙስና ተጠርጣሪዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ቢሆንም ተሳትፎአቸው በጅምር የቀረና ያልተፈፀመ መሆኑን የጠቆሙ ምንጮች፤ ለፀረሙስና ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት ለምርመራ ስራው አስተዋፅኦ ያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ምስክሮቹን በቅርበት ስለሚያቋቸው ጉዳት ሊያደርሱባቸው ይችላሉ በሚል ማንነታቸው በሚስጥር እንደሚያዝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምስክርነት ከመስጠትም በተጨማሪ ገና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችንና ማስረጃዎችን በእነዚህ ምስክሮች አማካኝነት ለማግኘት እየተሞከረ ነው ተብሏል፡፡
የኤርትራ ልዑክ ከካናዳ ውጡ ተባሉ
በቶሮንቶ የሚገኙትን የኤርትራ ጄኔራል ቆንስላ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሰመረ ገብረመድህን ሚካኤል ካናዳን ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ተሰማ። የካናዳ መንግስት ይፋ እንዳደረገው የቆንስላው ሃላፊ ካናዳን እንዲለቁ የታዘዙት ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸውና በጊዚያዊ ካናዳ እንዲኖሩ ከተፈቀደላቸው የኤርትራ ተወላጆች  ገንዘብን በመሰብሰብ ለኤርትራ መንግስት ጦር ሰራዊት የገንዘብ እርዳታSemere Ghebremariam ሲያደርጉ ስለተደረሰባቸው ነው። ጉዳዩ በምርመራ የተረጋገጠ እንደሆነም የካናዳ መንግስት አስታውቋል።
ድርጊቱ የካናዳንና የተባበሩት መንግስታትን መርህና ህግ የሚጻረር በመሆኑ የኤርትራዊ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ሃላፊ እስከ ግንቦት 27 ቀን 2005 ዓ ም ድረስ ካናዳን ለቀው እንዲወጡ ቀን ተገድቦላቸዋል። የቀነ ገደብ አስቀምጦ ትዕዛዙን ያስተላለፈው የካናዳ መንግስት ውሳኔውን ለመወሰን የተገደደው ኤርትራ ላይ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በጣለው ማዕቀብ ስለመሆኑ የተባለ ነገር የለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኤርትራው ሊቀመንበር ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ የሚደርስባቸው ተቃውሞና በተለያዩ አገራት ባላቸው ኤምባሲ የሚከናወኑት ውግዘቶች ከወትሮው በተለይ የተጠናከሩ ሆነዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት “በረሃ” ገቡ
በአዊ ዞን በጃዊ በረሃ ይንቀሳቀሳል ወደ ከተባለው አዲስ ወታደራዊ ሀይል ጋር እንደተቀላቀሉ የተነገረላቸው 19 የአማራ ክልል የዳንግላ ወታደሮች ድንጋጤ መፍጠሩን ኢሳት አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ በዘጠኝ ወር የስራ ግምገማ ሪፖርት ላይ ፖሊሶቹ መሳሪያቸውን በመያዝ መሰወራቸውን ይፋ እንዳደረገ የገለጸው ኢሳት፣ አዲስ የተቋቋመው ወታደራዊ ሃይል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንቅስቃሴያቸውን በማስፋት አንዳንድ መጠነኛ የሚባሉ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አመልክቷል።
ይህንኑ ተከትሎ በዞኑ ጠንካራ የተባለ ግምገማ እየተካሄደ ነው ያለው ኢሳት፣ “ኢህአዴግ በትጥቅ ትግል እንዲወድቅ አልመው ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብሎ የሚጠረጠሩ ባለስልጣናትን ሰበብ በመፍጠር ከስልጣን ለማውረድ ግምገማ መጀመሩን ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል” በማለት ስለሚደረገው ግምገማ ቀደም ሲል መረጃ መስጠቱን ተናግሯል። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የዞኑን ባለስልጣናት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ እንዳልተሳካለትም ጠቁሟል።
“ከኢህአዴግ ጎን ለመሰለፍ ተስፋችን ተሟጦ አልቋል”
በግንቦት ሃያ ማግስት በባህርዳር በተካሄደ የብአዴን ወጣቶች 2ኛ መደበኛ ጉባኤ “ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈን ለመታገል እምነትም ጽናትም የለንም” በማለት የሊጉ አባለት መናገራቸውን ኢሳት አስታውቋል። በክልሉ ካለው 20 ሚልዮን ህዝብ መካከል 429 ሺ 520 የሚሆኑ ወጣቶችን አባል አለኝ የሚለው ብአዴን ከአደገኛ ቦዘኔነት እስከ ልማት አርበኛ ስም የሚነግድበት ወጣት ከገዥው ፓርቲ ያተረፈው ኪሳራ መሆኑን ተሰብሳቢዎች በአስተያየት አመልከተዋል፡፡
ከመላው የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ3000 በላይ ወጣቶች በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተቋማት እንዲሳተፉ መደረጉ አስመልክቶ የዘርፉ ስኬታማነት” በሚል ርዕስ የቀረበውን ሪፖርት ካደመጡ በኋላ “የኢህአዴግ ንግድ ትርፉ ኪሳራ ነው” በማለት ለቀረበው ሪፖርት ምላሽ ሰጥተዋል። “በሃሰት እንድንኖር እየተገደድን ነው” ያሉት ወጣቶች  “ከኢህአዴግ ጎን ለመሰለፍ ተስፋችን ተሟጦ አልቋል፣ እምነትም የለንም” ብለዋል ሲል ኢሳት ዘግቧል። በጉባኤው ላይ በ1960 ዎቹ የነበሩትን የወጣቶች እንቅስቃሴ እንደነ ዋለልኝ እና ማርታ የመሳሰሉትን በማንሳት ሌላ ታሪክ ያስፈልጋል ያሉም ነበሩ ብሏል።
andmየግዳጅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ አሰልቺ የአዲስ ራዕይ ውይይት፣ መዋጮና ስራ አጥነት ተዳምረው የቤተሰቦቻቸው ሸክም እንዳደረጋቸው የተናገሩት ወጣቶች፣ ምሬታቸውን እንዳሰሙ የዘገበው ኢሳት የሊጉ ሊቀመንበር አቶ ስቡህ ገበያው “ወጣቱ ቁርጠኛ አልሆነም” ካለ በኋላ “በየደረጃው ያሉ አመራሮች የአድርባይነት እና የአቅም ክፍተት የወጣቱን ተጠቃሚነት ፈተና ውስጥ ከተውታል። ኪራይ ሰብሳቢነት፤ ብልሹአሰራርና ሙስና፣ በወረዳው ዓመራር መሃል በመስፈኑ መታገል እና ለውጥ ማምጣት ትግሉን እንደ አዲስ ለመጀመር ይታሰባል” ሲል የእንታገል ጥሪ ማቅረቡን አስነብቧል።
አቶ ስቡህ መድረኩ ፍጥጫ የበዛበት እንደነበር አምኖ፣ ወጣቶች ከኢህአዴግ ጎን አንቆምም ማለታቸውን ግን ማስተባበሉን ያመለከተው ኢሳት ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። እሳቸውም ”እናንተን ወጣቶች ይዘን የአውራ ፓርቲነታችንን እናረጋግጣለን “ ብለዋል። ጉባኤውን ለማዘጋጀት አንድ ሚሊዮን ብር መመደቡን ጨምሮ ተመልክቷል።

No comments:

Post a Comment