Translate

Wednesday, June 5, 2013

. ህወሓቶች ሙስና ላለማጋለጥ ወሰኑ …(Abraha Desta)

ባለፈው ከግብር ከፋዮች የተሰበሰበ ገንዘብ ዘርፈው ለማምለጥ ሲሞክሩ የተያዙ የገቢዎች ባለስልጣናት ምክንያት አድርገን ስለ ህወሓት/ኢህኣዴግና የሙስና መሰረቱ ተወያይተን ነበር።
ህወሓት/ኢህኣዴግ በሙስና የተገነባ ድርጅት መሆኑ፣ አሁን አሁን ሙስና ለድርጅቱ አደጋ መደቀኑ፣ ሙስና ካላስወገደ ዕድሜው አጭር እንደሚሆን፣ ኢህኣዴግ ዕድሜው ለማራዘም ሙስና መዋጋት እንዳለበት፣ ሙስና ከተዋጋ ደግሞ ከራሱ ድርጅት ጋር ግብግብ እንደሚገጥም፣ በመጨረሻም ሙስና ለማስወገድ የሙስና ምንጭ መድረቅ እንዳለበት፣ የሙስናው ምንጭ ደግሞ ህወሓት/ኢህኣዴግ መሆኑና፣ ሙስና ለማጥፋት ኢህኣዴግ ማጥፋት እንደሚያስፈልግ፣ ኢህኣዴግ ራሱ ሙስናን ለመታገል ቆርጦ ከተነሳ ግን ራስ በራስ ማጥፋት እንደሚሆን፣ ይህን ራስ የማጥፋት ስራ ደግሞ ከባድ መሆኑ ጠቅሰን ነበር።

ይሄን ‘የፀረ ሙስና ትግል’ በተመለከተ በትግራይ ክልል ስልጣን ይዘው የሚገኙ የህወሓት ባለስልጣናት በጉዳዩ ተወያይተው ሙስናን ላለማጋለጥ ተስማምተዋል። የተወሰነ ማጣራት ለማድረግ ሞክረው አብዛኞቹ ህወሓት አባላት ሙስና ሰርተዋል (በመስራት ላይ ናቸው)። አብዛኞቹ የህወሓት አባላት የመንግስት ለውጥ ከተደረገ ሀገራቸው ለቀው እንደሚወጡ ያስባሉ (ራሳቸው በደርግ ባለስልጣናት የፈፀሙት ግፍ በራሳቸው ሊደገም እንደሚችል ያስባሉ። ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር ከተደረገ በሀገራቸው በሰላም መኖር እንደሚችሉ አያውቁም።) እናም ከሀገር ለመውጣት የሚያስችላቸው ገንዘብ ለመያዝ እየተጣደፉ ነው። የመኖር ዋስትናቸው ሃብት እንደሆነ ተረድተዋል።
“ወጠጤ ለወጠጤ ሲማከሩ አንታረድ አሉ” (‘ወጠጦ ንወጠጦ እንትማኸሩ አይንታሓረድ በሉ’) ሆነና ነገሩ የህወሓት ባለስልጣናት ራሳቸው የሰሩት ሙስና “የተቃዋሚዎች መሳለቅያ አንሆንም” (‘ኣደዳ/ መሐጎሲ ተቃወምቲ ኣይንኾንን’) በሚል ሰበብ በትግራይ የተፈፀመው የሙስና ተግባር ላለማጋጥ ተስማምተው ሙስናን እየተዋጉ እንደሆነ ለማስመሰል ግን በመልካም አስተዳደር ዙርያ የሚመክር አንድ ግንባር (በግብረ ሃይል መልክ) ማቋቋማቸው ታውቋል። የግንባሩ ተጠሪዎች በሙስና የሚጠረጠሩ የህወሓት ባለስልጣናት ናቸው።
ድሮም ኮ ሙሰኛ ሙስናን መዋጋት ይከብደዋል። አንድ ሙሰኛ ማድረግ የሚችለው ነገር ቢኖር የሰራው ሙስና እንዳይጋለጥ “ፀረ ሙስና ወይ አጣሪ ወይ የሆነ ኮሚሽን ነገር” ማቋቋም ነው። ይህ መላ እየሰሩበት ነው።
ግብር መክፈል ሀገራዊ ግዴታችን ነው። የከፈልነው ግብር በኣግባቡ በመንግስት ስራ መዋሉ ማረጋገጥ ግን ይኖርብናል። ዜጎች ግብር የሚከፍሉት ገንዘብ በዝቶባቸው አይደለም። ስለዚህ ለእያንዳንዱ የምንከፍለው ገንዘብ ወደ ባለስልጣናት ኪስ አለመግባቱ ማረጋገጥ አለብን።
It is so!!! Abraha Desta

No comments:

Post a Comment