Translate

Saturday, June 1, 2013

ሰበር ዜና፣ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ ዝግጅቱ ተጧጡፏል

ዘሬ ጠዋት ላይ ሁኔታውን ለመከታተል ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያመራው በቅጽል ስሙ “ማጀስቲ” የተባለው ወጣት በተመለከተው እንቅስቃሴ እጅግ ተደስቷል።

በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ከ5 በላይ መኪናዎች ቆመዋል፣ ድንኳን ቢጤም ተጥሏል፣ በራሪ ወረቀቶችን እና ሌሎችም ለሰላማዊ ሰልፉ ግብአት የሚሆኑ ቁሳቁሶች የያዙ ወጣቶች ገባ ወጣ ይላሉ። የወጣቶች ተሳትፎ የሚያስደንቅ ነው። የጸሀዬ ዮሀንስ ቀስቃሽ ዘፈን ጎላ ብሎ ይሰማል።
ሰዎች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት እየጎረፉ ነው፣ ምን እናግዝ ምን እንስራ ይላሉ።
ይህ በዚህ እንዳለ ወጣቱ ቅሬታውንም አልሸሸገም፣
ቀደም ሲል የመኢህአድና አንድነት ፓርቲ ሰልፉን እንደሚደግፉና በቅስቀሳውም እንደሚተባበሩ አሳውቀው የነበረ ሲሆን እያደረጉ ያሉት ተሳትፎ ግን እምብዛም አልታየም ብሏል።

Addis Ababa, Ethiopia a call for demonstration

No comments:

Post a Comment