Translate

Wednesday, June 12, 2013

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው!!

(ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ)

building


ወያኔን ማስወገድ አይደለም የሚያስቸግረው፤

አስቸጋሪው ነገር አገርን መገንባት ነው !!

“We are just leaving barbarism and are still entirely at the beginning. The French, however have already gone a piece of the way and have a century`s lead in every respect.” Friedrich the Great II to Wilhelm of Prussia

መግቢያ
የወያኔን አገዛዝ ነፍስ ለመዝራት፣ ወይንም የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የሚደረገውን በአንዳንድ ምሁሮች የሚነዛውን የማያስፈልግ አጻጻፍ ትተን፣ እስከዛሬ ድረስ በተለይም ብዙዎቻችንን ያሰጨነቀንና የሚያስጨንቀን፣ የቀድሞዎቹ አገዛዝም ሆነ ወያኔ ያተራመሰውን አገር እንዴት መገንባት አለብን ? የሚለው ሳይሆን፣ እሱን አስወግዶ እንዴት ስልጣን መያዝ ይቻላል የሚለው ነው። ይህ ዐይነቱ፣ እኛን ብቻ ሳይሆን ከአርባ ዐመታት በላይ በሌሎች የተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ይካሄድ የነበረውን የትግል ዘዴና፣ ዛሬም በእኛ አገር የሚከናወነውን፣ ከብዙ የሶስተኛው ዓለም አገሮች ልምድ እንደምናየው ህዝቦችን ከድህነት አላቆ የተከበረ አገር የሚያስገነባ የትግል ዘዴ አይደለም።
fekadu bekele
(ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ)
በአንዳንዶች አስተሳሰብ ካልሆነ በስተቀር፣ ዛሬ ለአገራችን ክብር፣ ነፃነት፣ ሰላም፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ ለተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ መታገል፣ ለድህነትና ለረሃብ መወገድ፣ እንዲሁም ለጠንካራ አገር መገንባት የምንታገል ኃይሎች ግልጽ የሆነ ነገር አለ። ይኸውም የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ፣ ወይም የስልጣን ተካፋይ እስከሆነ ድረስ፣ ወይም ደግሞ ፓርላሜንት ውስጥ ተቀምጦ ችግር ፈጣሪ እስከሆነ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ስልጣኔና ሰላም በፍጹም ማግኘት እንደማይችል ነው። በታሪክ እንደታየው ያልተገለፀለት ኃይል ስልጣን እስከያዘ ድረስ፣ ወይም የስልጣን ተካፋይ እስከሆነ ድረስ በምንም ዐይነት አንድ በፀና መሰረት ላይ ሊቆም የሚችል አገር መገንባት በፍጹም እንደማይቻል ነው። አሁንም በታሪክ እንደተረጋገጠው፣ ዕውነተኛ ስልጣኔን ለማምጣት ከተፈለገ፣ በአረጀ በሬ ማረስ መጓተት ብቻ ነው ትርፉ እንደሚባለው አነጋገር፣ በአረጁ ሰዎችና በአረጀ አሰተሳሰብ በሳይንስና በቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በጥበብ ላይ የተመሰረተ አገር ገንብቶ አንድን ህዝብ ዕውነተኛ ነፃነት ማጎናፀፍ እንደማይቻል ነው። ስለዚህም በዚህም ተባለ በዚያ አጉል አርቆ-አሳቢ ነኝ ለማለት ካልሆነ በስተቀር የዛሬው አገዛዝ በአገር ግንባታ ውስጥ ሊሳተፍ የሚችል ኃይል አይደለም፤ ብቃትም እንደሌለው በአለፉት 21 ዐመታት አረጋግጧል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

No comments:

Post a Comment