Translate

Tuesday, August 15, 2017

ሙስና… ሙስና… ሙስና! (በኤልያስ ገብሩ)

ከጭቁን ህዝብ ጉሮሮ ተንገብግቦ መዝረፍ ይብቃችሁ!

በኤልያስ ገብሩ (ጋዜጠኛ)
Flood in Addis Ababa
ይህ ትናንት በአዲስ አበባ በዘነበው ዝናብ የተነሳ የተፈጠረ የጎርፍ ትዕይንት ነበር። ዝናቡ ባልከፋ፣ ነገር ግን ኢብኮ “ሚሊየንና ቢሊየን ብር ወጥቶባቸው ተመረቁ” እያለ በ’ልማታዊ’ ዜና የሚደሰኩርልን የተሽከርካሪና እግረኛ መንገዶች ተሽከርካሪዎችንና እግረኞችን እንዲህ በነጻ ሲያስዋኙት ታይተዋል።

ክስተቱ ጥቁርና ነጭ የሌለው የዘቀጠ የሙስና ውጤት ነው።
“መንገዶች ተሰሩ፣ በልማት ላይ ነን!” እንባላለን፤ ግን ጥራት እና የተራዘመ የአገልግሎት ዘመን የለም!
እስኪ እውነት እንነጋገርና …በጥራት ተሰርቶ የአገልግሎት ዕድሜው የረዘመልን የመንገድ ሥራ በዘመነ ኢህአዴግ ይኖር ይሆን?!
በልማት ሥራ ስም፣ ከላይ እስከታች ባለ መዋቅር፤ ስር በሰደደ አስቀያሚ፣ መረን በወጣ፣ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት በራቀ፣ ህዝብን በናቀና ከስግብግብነት ሰብዕና በመነጨ ሙስና ተጨማልቆ ጥራት ያለውና የአገልግሎት ዘመኑ የረዘመ የመንገድ ሥራን መጠበቅ የዋህነት ነው።
ቢሆንም …ሙስና የሀገር፣ የህዝብ፣ ቤተሰብና የግለሰብ ጠንቅ ነውና መወገዝ አለበት!
እኚህ ትናንት ይነሳኋቸው ጥቂት ፎቶግራፎች የሙስና ውጤቶች በመሆናቸው አይቼ ማዘኔ አልቀረም።
ከጃፓን የተኮረጀው የውሃ ማቆር የልማት ስትራቴጂ [በዋነኝነት አቶ መለስ ዜናዊን ይመለከታል]፣ ለመስኖ ስራ እንጂ ለመንገዶቻችን ልማት አልመሰለንም ነበር።
እንደዚህ አይነት ጥራት አልባ መንገዶችን ሞስነው ለህዝብ ግልጋሎት የሚያቀርቡ የመንገድ ስራ ባለሞያዎችም በድርጊታቸው ማፈር ይገባቸዋል – ህሊና ካላቸው!
በሀገራዊ ችግሮቻችን ላይ ለውጥ ለማምጣት፤ አሁንም ደፍሮ መነጋገር እና መወያየት ያሻናል! አንድም የተሸፋፈነ ማኅበራዊ አኗናራችን ነው መረን ለለቀቀው ሙስና በር የከፈተው። ሀገራዊ ሙስናን በግልጽ በመነጋገር እንጂ በጓዳ ሀሜት ልንቀንሰው ከቶ አንችልም!
Flood in Addis Ababa
Flood in Addis Ababa

No comments:

Post a Comment