Translate

Thursday, August 17, 2017

ከያኒ አብዲ ኪያር እግዚአብሄር ይይልህ (ዳዊት ዳባ)

ዳዊት ዳባ
አንድ ሰው ምንድን ነህ? (ብሄረሰብህ ምንድን ነው) ተብሎ ለምን ይጠየቃል። ለምንስ ይናገራል የሚለው ትልቅ ጉዳይ የሆነው አሁን ላይ ፋሽን ተደርጎ እየተቀነቀነ ያለ ፖለቲካዊ አቋም ስለሆነ ብቻ ነው። “ምንድን ነህ የሚለው የሚከብድ ነገር አለው” በሚል ለመጀመርያ ጊዜ   ሲናገር የሰማሁት የምወደው የኪነ ጥበቡ ሰው አብዲ ኪያር ነው። ሀሳቡን ያነሳበት ሆነ ያስረዳበት መንገድ ጠቅላላ መንፈሱ ምንም ስህተት ያለውም አልነበረም።
ያነሳበትም በቂ ምክንያትም ነበረው። ከዛ በሗላ ግን በብዙ ፀሀፍት፤ ፖለቲከኞች ፤ታላላቅ አገራዊ መድርኮች ላይ ሁሉ በተሳሳተና መስመር በለቀቀ መንገድ አስጨብጫቢ አሳብ አድርገውት ብዙ ጊዜ አይቻለው። ከቃሉ አጠቃቀም አኳያ ዘርህ(ብሄረሰብህ) ምንድን ነው? ከማለት “ምንድን ነህ”? ማለቱ ችግር አለው ከሆነ ተቀባይ ሊሆን ይችላል። ይህም ቢሆን ግን የቋንቋ ጉዳይ ነው። ጠያቂውም ተጠያቂውም ከተግባቡበት ታቡ ሊደረግ የሚገባ ችግር አይደለም። ለምሳሌ  አበሻ ነህ? ተብዬ እጠየቃለው። የጠያቂው ፍላጎት የሴም የካም ዘር የሚለው የተራዘመ ትንታኔ እንዳልሆነ ስለምረዳ መልሴ ባጭሩ አዎ ነው። ስሜን ወይ እምነቴን ሌላም ማንነቴን ስጠየቅ በቀጥታ እንደምመልሰው።  ምንድን ነህም? ተብሎ ሆነ በሌላ አገላለፅ ዘሬን ስጠየቅም በቀጥታ መልስ እሰጣለው። እራሴንም ሆነ ጠያቂዬን ዘረኛም ሆነ ስህተተኛ አድርጎ የሚያስወስደኝ ምክንያት የለም። በኔ እይታ ስህተተኛነቱም ዘረኝነቱም ያለው ለምን ይጠየቃል። ለምንስ ይመለሳል የሚለው ላይ ነው። ብዙውን ጊዜ ምንድን ነህ ብሎ አንድ ሰው ዘርህን የሚጠይቀው በጭራሽ ለመጥፎ አይደለም። የበዛውን ጊዜ ዝም ብሎ ለማወቅና ለውይይት አካል አድርጎ ስለሚወሰደው ብቻ ነው። እንዲህ ነኝ ብሎ የሚመልሰውም ግለሰብ እውነቱን መናገር ስላለበትና የሆነወን ወይ ነኝ ብሎ የሚያምነውን ነው።
ኢትዮጵያዊ በሆነ ወገን ተጠይቄ አላውቅም ማለት አልችልም።ስለማላካብደውም ይሆናል። ትልቅ ፖለቲካዊ አጀንዳና የንግግር መክፈቻ የሆነውን ያህል በቀጥታ ዘሬን የተጠየኩበትን ጊዜና የጠየቁኝን ግለሰቦች ለማስታወስ ሞክሬ  አንድ ገጠመኝን ለማስታወስ ግን  አልቻልኩም። እኔ ዘሩን የጠየኩትንም ኢትዬጵያዊም በተመሳሳይ። ይህ ስላስገረመኝ የቻልኩትን ያህል እስቲ ሰፋ ላድርገው ብዬ አካባቢዬ ላሉ ከአስር ለሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን እነዚሁኑ መጠይቆች አቀረብኩላቸው። ሶስቱ አንድና ሁለት አጋጣሚ ከብዙ ጥረት በሗላ ቢያስታውሱም ጠቅላል ባለ መልሳቸው እንደማያስታወሱና ተጠይቀውም ሆነ ጠይቀው ቢያውቁ ለመጥፎ እንዳልነበረና አካብደው የሚያዩት ጉዳይ እንዳልሆነ ነው። የዚህ አይነት ጥያቄዎች የሚጠየቁበት መንፈስ ዝም ብሎ ለማወቅና ከግንኙነት በዘለለ ለመጥፎ እንዳልሆነ ተጨማሪ አስረጅ የሆነኝ እኔም ሆንኩ እነዚህ ወገኖች የሌሎች አገር ዜጎችን እንደሚጠይቁና እነሱም በሌላ አገር ዜጎች  በዙ ጊዜ ተጠይቀው የሚያውቁ መሆናቸው ነው። እነዚህ የሌላ አገር ዜጎች ትንሽ ስለኛ የሚያውቁ ከሆነ አማራ፤ ትግሬ፤  ኦሮሞ ተብሎ መጠየቅም ያጋጥማል። ዲነካ ነህ ኑዌር ሱዳኖችን። መጀርተን- ሀዊያ ብዬ ሱማሌዎችን፤ ኩኩዬ- ሊዬ ኬንያዊያንን ጠይቄያለው። ኢትዬጵያዊ ኢትዬጵያዊን በቀጥታ የሚጠይቀው  እንግዳ የሆነ ቦታ ሲያገኘው ለዛውም እርግጠኛ ለመሆን ሲል ኢትዬጵያዊ ነህ? አንዳንዴም አበሻ ነህ? ብሎ ብቻ  ነው። ሲጀመር ያንድን ሰው ዜግነት፤ እምነቱን፤ ሰፈሩን፤ ብሄረሰቡንና ቤተሰቡን……መጠየቅ ታምራዊ በሆነ ዛሬ የተጀመረ አይደለም።  ወያኔ ያመጣም አይደለም። በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ በየትኛውም አለም ላይም የሚጠየቁ ጥያቄዎች ናቸው። የዘር ግንዳቸው ከጀርመን ከፖርቹጋል እያሉ ቅድመ አያቶቻቸውን አንስተው የሚነግሩህ አሜሪካኖች ብዙ ጊዜ ያጋጥማሉ።
በመጀመሪያ ሰው ነበርንና፡ መጀመርያ ከሚለው ከተነሳን እንቁላል ነበርን  ብልስ። እንቁላል ከመሆናችን በፊትስ ብሎ ጠይቆ ደግሞ ጎመን ወይ ቁርጥ ስጋ ብሎ መመለስ እና እየቀጠሉ መሄድ ይቻላል እኮ። አልያም እንደ እምነታችን አፈር፤ ውሀ፤ እስትንፋስ እያልን መድከም ነው።  በአለም ላይ ሰው አይደለሁም የሚል ክርክር የገጠመ ኖሮ የሚያውቅ አይመስለኝም። ስለዚህም አይ ሰው ነህ የሚል ማሳመኛም እንዲሁ ቀርቦ አያውቅም።    ክርክሩ በሌለበት የፈለገ በመጀመርያም ይበለው በመጨረሻ  ሰው ነኝ ብሎ ማሳመኛ ማቅረብ ከፈለገ መብቱ ነው። ሊባል የሚቻለው ትክክል ነህ። ግጥም አድረገህ ሰው ነህ ብቻ ነው። ነገር ግን ስምህ ማነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እከሌ ከማለት ሰው ነኝ ቢል ለተጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛና ቀጥተኛ መልስ አልሰጠም። በተመሳሳይ ዜግነትህ፤ ሰፈርህ፤ ዘርህ፤ ስራህ፤ እምነትህ ለመሳሰሉት ብዙ ተመሳሳይነት ላላቸው ጥያቄዎች  “ሰው ነኝ” መልስ አይሆንም።  ከነዚህ አይነት የተለያየ ማንነቶች ተፅኖ ውጪ እየኖርኩ ነው። ወይ መኖር ይቻላል ከሆነ አላማው?። የማይቻል መሆኑንን ለማሳየት ትናንት ከተነገረና  ከተፃፉ እንዲሁም ከተኖረ ሂወት በዙ ማሳጫ ማቅረብ የሚቻል ቢሆንም አስፈላጊ አይደለም። እስቲ ነገን ፍፁም በሚሰኝ ሳይሆን- ስልጡን በሆነው እንኳ ኑሩትና አሳዩን ብሎ ማለፉ ይሻላል። ስልጡን ለመሆን በመጀመርያ ከኛ የተለየ ዜግነት፤ እምነት፤ ቀለም፤ ዘር፤ ቋንቋ፤ አኗኗር፤ ባህል፤ አመጋገብ፤… ያለቸው መኖራቸውን መቀበል። በመኖራቸውም መደሰት። የተቻለውን ያህል ማፍቀር። ማክበርና አለመፍራት። አልፎም የተለየ ፍላጎትና ሊኖራቸው እንደሚችል ማወቅ። አለመጥላትን በዋናናነት ይፈልጋል።
“የሰውን ልጅ እንጂ ያሉ ልዩነቶችን አምላክ አልፈጠራቸውም”። ምን ያህል እርግጠኛ መሆን ይቻላል?። ልዩነቶች መኖራቸውን እንደሚያውቅ የልተቃወመውና እንደውም— አልለውም የነበረ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይቻላላ። ልዩነቶችን የሰው ልጅ ነው የፈጠራቸው ብለን ድርቅ ብንል እንኳ። የሰው ልጅ ልፍጠር ብሎ አስቦ ያልፈጠራቸው ወይ እንዳይፈጠሩ ለማድረግ ቢፈልግም ይቻለው ያልነበሩ ነገሮች ደግሞ አሉ። “ተፈጥሯዊ” ወይም naturale የሆኑ ማለት ነው። በተጨማሪም ልዩነቶችን የሰው ልጅ ስለሰራቸው ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች ናቸው የሚለው። ሰው የሰራው ሁሉ መጥፎ ነው የሚል የተሳሳተና አሳዛኝም መከራካሪያ ነው። እዚህ እርቀት ድረስ የምንሄደውና ስህተት ውስጥ የምንገባው ከኛ በምንም አይነት መንገድ የተለዩ ለምን ኖሩ?  በሚመስል አንድና አንድ መኖራቸውን ለመውደድ አቅም ስለምናጣ ብቻ ነው።
ሲጀመር ያንድን ኢትዬጵያዊ ዜጋ ብሄረሰቡ ሆነ እምነቱን ለማወቅ መጠየቁ አስፈላጊ መቼ ሆኖ ነው። ከሰላምታ በሗላ ለትንሽ ደቂቃ ማውራት ብቻ ነው የሚያስፈልገው። የበዛውን ጊዜ እምነቱን ሀ ብሎ ሲጀምር ሰላማታው ውስጥ ታገኘዋለህ። ሌላውን መነስነስ፤ ኢ ሚዛናዊነት፤  ማንቋሸሽ፤ ጠላትነት፤ እሮሮ፤ መሰበክ፤ በነገሮች ላይ ያለው ምለክታ የወገነ በመሆኑ ማንነቱን ማወቅ ቀላል ነው። የበዛነው በዚህ ደረጃ በቀላሉ ለመታወቅ እጅግ ቀላሎች ነን።  ልንታገለውና ልንለውጠው የሚገባ ይህ ነው። ብዙ ሊባልበት የሚገባም ይሄ ነው። እኛ ስናወራ በጥሞና ለዳመጠና ጥሩ ዜጋ ለሆነ። እውን ይህ ሰው ስለ አገሩ ሰው! ስለወገኑ ነው የሚያወራው ብሎ መጠየቅ ድረስ ያደርሳል። አስፈሪ የሚያደርገው እየተሻለን ሳይሆን ከድጡ ወደ ማጡ እየሄድንበት ያለ ችግር መሆኑም ነው። እንደ አንድ አገር ህዝብ በዚህ መንገድ ለመቀረፃችን ምክንያት ታሪካችንም አተራራኩም። መንግስቶቻችንም አስተዳደራቸውም። ድርጅቶቻችንም ፖለቲካቸውም። እምነቶቻችንም አስተምሯቸውም። በእኩል መጠበባችንም ጥበበኞቻችንም። ልዩነቶቻች መኖራቸውን የሚጠሉና የሚዋጉ አልፈውም የሚክድ አይነት የሚመስሉ በመሆናቸው ምክንያት ነው። ያሉንን ልዩነቶች አምላክም ፈጠሯቸው አልፈጠሯቸው። የሰው ልጅም ይፍጠረው ተፈጥሯዊ ይሁኑ። ልዩነቶች አሉን። ይኖራሉም። በማውገዝም ሆነ በማበሻቀጥ አናጠፋውም። መኖራቸውን ተቀብሎ፤ ፍላጎትን አቻችሎና አስተፋቅረን መኖርን ልናውቅበት ግድ ይላል። ሌላኛው መንገድ የተሞከረና አንደርድሮ አንደርድሮ ገደል አፋፍ ላይ አቁሞናል።
ከተመክሮዬ አሜሪካኖች ያንተ እምነት ትክክል አይደለምና የኔን እመንት ተከተል ብለውኝ አያውቁም። ጠቅለል ባለ ማመን ጥሩ  ይሉሀል።  እምነትህን ጠይቀውህ ያለህበትን እምነት አጥብቆ መያዙ ጥሩ እንደሆነ በወሬ ደረጃ ሊያወሩህ ይችላሉ። ስላንተ እምነት የሚያውቁትን መልካም ነገሮች ይነግሩሀል አለቀ። አሁን ባለው አለማቀፋዊ ሁኔታና የዜና ሽፋን ውስጥም የእስልምና እምነት ተከታይ ነኝ ብዬም ሞክሬዎለው። በተመሳሳይ ከየት ነህ? አገርህን ትነግራቸዋለህ። አገርን ያህል ነገር ለቆ በሌላ አገር መኖርና መላመድ ከባድ እንደሆነ፤ አሁን እዚህ ደስተኛ መሆንህን? ይጠይቁሀል። ስለአገርህ የሚያውቁትን ያህል ያወሩሀል። በኛ አገር ሁኔታ ስለረሀብተኛነታችን፤ ስለ ሀይለ ስላሴ፤ ስለ አበበ በቂላ፤ ስለ ሙሴ ታቦት፤ ስለጦርነት ታሪካችን፤ ጣሊያንን ስለማሸነፋችን  የመሳሰለውን። ለኛ ቅንጦት ቢሆንም እነሱ ደግሞ ስለአገራቸው ችግርና ትክክል አይደለም የሚሉትን ይነግሩሀል። መነስነስ የለባቸውም። ስልጥቁር ታሪካቸው ማውራትም አይገዳቸውም። እንደኔ ታክሲ ነጂ ለሆኑ ተደጋጋሚ መሆኑ ይሰለች ይሆን እንጂ በዚህ አይነት ጉዳይ ላይ ጠብ ውስጥ የሚሳገባ አይደለም ቅር  የሚያሰኝ ነገር ከመናገር ቁጥብ ናቸው። የተጋነነ የሚባል ዘረኝነትና ጥላቻም ገጠመኝም ያለ ሰመቼ አላውቅም።
አንዴ ግን ሳቄን ላቆም ያልቻልኩበትና የተማርኩበትን አንድ ገጠመኜን ላካፍላችሁና ልጨርስ። የናጠጡ ሀብታሞች ከሚኖሩበት ሀይ ላንድ ፓርክ ከሚባል ቦታ አንድ ተንኮለኛ ነጭ ሽማግሌ አነሳው። እርቆ አይሄድም። የሚሄድበት ቦታ አምስት ወይ ስድስት ማይል ቢሆን ነው። ሰላምታ ከተለዋወጥን በሗላ የተለመደውን ወሬ ማስጀመሪያ ሰለ እለቱ የአየር ሁኔታ አወራርቶኝ ከየት እንደሆንኩ ጠየቀኝ። ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነገርኩት። ሰለ ኢትዬጵያ ብዙ መልካም ነገሮችን ያወጋኝ ጀመረ። በእለቱ የማውራት ፍላጎቱ ስላልነበረኝም ይሁን ብዙ ጊዜ እራሴን በምወቅስበት ሁኔታ ከሌላ ዜጎች ጋር ስለኢትዬጵያ ስወያይ ጨለምተኛ ነኝ። ሙገሳው ስላልተመቸኝም ይሆናል እየሰማው እንደሆነ እንዲያውቅ ብቻ አንገቴን እየነቀነኩና አንዳንዴም እሀ- ያ እያልኩ ዝም ብዬ መንዳቴን ቀጠልኩ። ስለ ጅግንነታችን ስለታቦቱ አውርቶኛል። ጨመረ ስለ እንግዳ ተቀባይነታችን፤ ስለደግነታችን። አሁንም አንገቴን እየወዘወዝኩ መንዳቴን ቀጠልኩ። ቀጠለ ገነት ስለሆነው አየር ንብረታችን፤ ስለድሮ ስልጣኔያችን፤ ተቻችለን ስለመኖራችን፤ የራሳችን ፍደልና ቀን መቁጠርያ እንዳለን። ብቻ አንድም መልካም የሆነ ታሪካችንን አልቀረውም። እንዲሁ እንደተረከልኝ የሚሄድበት ቦታ ደረስንና አቆምኩለት። ሊወርድ በሩን እየከፈተ አስገራሚ ጥያቄ ጠየቀኝ። ይህንን ያህል ታሪክ ስለአገርህ ስነግርህ እንዴት አወቅክ ብለህ እኮ አልጠየከኝም? የሚል። ጥያቄው አስገርሞኛል። እየወረደም ስለነበረና ስረው እሩጫ አለበት። አጭሩ ደህና ሁን ማያ መንገድ አድርጌ ስለወሰድኩት። እውነትክን ነው። ይህን ሁሉ ስለ አገሬ እንዴት ልታውቅ ቻልክ? ብዬ ጠየኩት። ምን ብሎኝ ቢወርድ ጥሩ ነው። ለለፉት አምስት አመታት መንዳት አቁሚያለው። በሳምንት አንዴ ቤተከርስቲያን ለመሄድ ታክሲ እጠቀማለው። የናንተን አላውቅም እኔ ግን የማውቀውን ስለማውቅና ያንጀቴን ስለነገረኝ ወደኩ ነው።

No comments:

Post a Comment