Translate

Friday, August 25, 2017

ህወሀት በአዲስ አበባ ህዝባዊ ተዋውሞ ይነሳል በሚል ስጋት ውስጥ ገብቷል

ህወሀት መራሹ መንግስት በኦሮሚያ የተጀመረው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በአዲስ አበባም ይደገማል በሚል ትልቅ ስጋት ውስጥ መውደቁን ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዛሬው ዕለት በአሜሪካን ግቢ ከፍተኛ ፍተሻ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡ በተለይም ከሱማሌ ተራ ወደ አሜሪካ ግቢ በሚያስገባው እና ከአንዋር መስጂድ ወደ አሜሪካ ግቢ በሚያስገባው መንገድ ላይ ብዛት ያላቸው የፖሊስ ኃይሎች ቆመው መታወቂያ በመጠየቅ ፍተሻ ሲያካሂዱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ባለፈው ወር በነጋዴው ላይ የአላግባብ የግብር እዳ እንዲከፍል በመተመኑ የተነሳ በአምቦ ህዝባዊ ተቃውሞ ተነስቶ በነበረበት ወቅት ከቀናቶች በኃላ የመርካቶ ነጋዴዎችም ተቃውሞውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡
በመሆኑም በአሁን ወቅት የህወሀት መራሹ ባለስልጣናት በኦሮሚያ የተጀመረውን ህዝባዊ አምቢተኝነት በአዲስ አበባም ይጀመራል በሚል ትልቅ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ብዛት ያላቸው የፖሊስ ኃይሎችን በተለያዩ ቦታዎች አሰማርቶ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment