Translate

Sunday, August 13, 2017

የውስጥ አርበኞች በባህርዳር ህወሃትን እና የብአዴን ተላላኪዎቹን ጭንቅ ውስጥ ከተዋቸዋል

በተፈራ አሳምነው
Bahir Dar City
ነሀሴ 1/2008 ዓ.ም ህወሃት ያሰማራቸው ነብስ ገዳዮች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት አደባባይ በወጡ የባህርዳር ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፍተው ከመቶ በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ጨፍጭፈዋል።

በአመቱ ነሀሴ 1/2009 ሰማእታቱን አስቦ ለመዋል ነጋዴዎች የንግድ ቤቶቻቸውን ዘግተው፣ እንዲሁም ማንኛውም ሰው በቤቱ በመቀመጥ ሰማእታቱን እንዲያስብ ጥሪ ተላለፈ፣ ጥሪውን ሳይቀበሉ በሚቀሩትና ከህወሃት/ብአዴን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በሚታወቁ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ተነገረ።
በሚያስገርም መልኩ የባህርዳር ህዝብ ለጥሪው ምላሽ ሰጥቶ በቤት ውስጥ በመቀመጥ ሰማእታቱን ለማሰብ የተጠራውን አድማ ተግባራዊ አደረገ። ይሁንና አንዳንድ ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸውና በአቋራጭ የከበሩ ባለጊዜዎች ጥሪውን ቸል በማለት ንግድ ቤቶቻቸውን ከፍተው ዋሉ።
ህወሃት እና የብአዴን ተላላኪዎቹ በበኩላቸው ህዝቡ የውስጥ አርበኞቹን (አስተባባሪዎቹን) መስማቱ እጅግ አስደንግጧቸዋል። ስለሆነም ሃይላቸውን ለማሳየት የእውር ድንብራቸውን ተንቀሳቀሱ።
በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይት በመተኮስ ሲገድሉ የነበሩትን የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላትን ወደ ባህርዳር በብዛት አስገቡ፣ ወዲያውም የባህርዳርን መውጫ መግቢያ ዘግተው ተደራራቢ የፍተሻ ኬላዎች አቁመው ህዝቡን በፍተሻ ያስጨንቁት ገቡ፣ በመቀጠልም በአድማው የተዘጉ የንግድ ቤቶችን እየዞሩ አሸጉ፣ ይህም አልበቃ ብሏቸው ህዝቡን ለማሸበር እና ፍርሃት ውስጥ ለመክተት ታዋቂ ነጋዴዎችን እና ግለሰቦችን እያፈሱ ማሰር ጀመሩ (ከታሰሩት ነጋዴዎች መካከል የታዋቂዋ ዘፋኝ እጅጋየሁ ሽባባው/ጂጂ አባት ይገኙበታል)።
ህወሃት እና ተላላኪዎቹ በዚህ መልኩ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር አውለነዋል ብለው ባሰቡበት ሰዓት ነው ትላት ቅዳሜ ምሽት በካሪቡ ካፌ እና ዋዜማ ጃንቦ ሀውስ አቅራቢያ የቦንብ ጥቃት የተፈጸመው። ካሪቡ ካፌ ሰማእታቱን ለማሰብ የተጠራውን አድማ ምላሽ እንዳልሰጠ የታወቀ ሲሆን የዋዜማ ጃንቦ ሀውስ ባለቤት እንግዳወርቅ ፅጌ ደግሞ የህወሃት የደህንነት አባል ነው ተብሎ ይታመናል። የተጠቀሱት የንግድ ቤቶች ባለቤቶች ለደህንነታቸው በመስጋት ባህርዳርን ለቀው መውጣታቸውም እየተነገረ ነው።
የውስጥ አርበኞቹ እያሰራጩ ባሉት መልእክቶቻቸው የባህርዳር ህዝብ ሰማእታቱን ለማሰብ በተጠራው አድማ ላይ ያልተሳተፉ የንግድ ቤቶችንና ባለቤቶቻቸው ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸውን የንግድ ቤቶችን እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር አስተላልፈዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ነሀሴ 7/2009 ዓ.ም በክልሉ መስተዳድር ተጠራ የተባለው አስቸኳይ ስብሰባ ከፍተኛ መተራመስ የነበረበት እና ያልውጤት መበተኑም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment