Translate

Saturday, August 5, 2017

ኃይሌ ገብረሥላሴ ምን እያለ ነው? (ደረጀ ሀብተወልድ)

ደረጀ ሀብተወልድ
ይህ ኃይሌ ገብረሥላሴ ዛሬ ጧት የሰጠው አስተያዬት ነው፣
“ሞ ፋራህን ወደ ኋላ ሄጄ ቪዲዮውን ብመለከት እንዲህ የሚባል ሰው የለም:: እኔም ስሮጥ አልነበረም ቀነኒሳም ሲሮጥ የለም:: ለማሸነፍ ሲሮጥ እንጂ ሰአት ሲያሻሽልም አታየውም:: ይሄን ስታይ ትጠራጠራለህ ከየት መጣ? የምጠረጥረው ነገር አለ ግን በአደባባይ መናገሩ ክስም ሊያመጣ ይችላል”
Mo Farah is the UK's finest ever distance runner
ሞ ፋራህ በአዲስ አበባ፣ ከቴዲ አፍሮ ጋር
ይህ አስተያዬት ከሌላ ሰው ቢሰነዘር ምንም አልነበረም። ሆኖም በሱ ዘመን ሲያሸንፍ አድናቆት ሲጎርፍለት የነበረ አትሌት ዛሬ ባለስልጣን ሆኖ ተሹሞ በቡድኑ ላይ ሽንፈት ሲደርስበት ተራው የሌላ አትሌት መሆኑን አምኖ ከመቀበል ይልቅ ወደ ስም ማጥፋት መሮጡ ያሳዝናል።

ደግሞ እሱ ሲሮጥበት ከነበረበት ጊዜ ይልቅ ሞ በሚሮጥበት በአሁኑ ወቅት የተሻለ የዶፒንግ ምርመራ አለ።
እንደ አንድ በዘርፉ በአሸናፊነት እንዳለፈ አትሌትም ሆነ እንደ አንድ ባለሥልጣን ፣እዚያው አጠገቡ መጥቶ ዐይኑ እያዬ በሡሉልታ ሜዳ ላቡ ጠብ እስኪል ድረስ ሠርቶ ያሸነፈን ጀግና “የድካምህን ዋጋ በማግኘትህ እንኳን ደስ ያለህ!” ማለት ነበር የሚገባው፣ የሚያምርበትም። እሱ ግን እንደ ወይዘሮ ጥንፌ የቡና ላይ ወሬ ሃሜትን መረጠ።
ሞ ያሸነፈው በዶፒንግ ሊሆን ይችላል ለሚል ስፔኩሌሽን በር የሚከፍትን ሃሜት የምፀየፈው ልክ “ኃይሌና ቀነኒሳ ሲያሸንፉ የነበሩት በዶፒንግ ነበር” የሚልን ሃሜት በምፀየፈው ልክ ነው::
እንዴ! ተው እንጂ ኃይሌ! ሞ ፋራህምኮ በውድድሩ ባይኖር ተሸንፈናል! የተሻለው ውጤትኮ 5 ተኛ ነው። ፋራህ ባይኖርም 4 ተኛ እንሆን ካልሆነ በስተቀር በሜዳሊያ በኩል የሚመጣ ለውጥ የለም። አረንጓዴው ጎርፍ ምንጭም ሆኖ አልታዬም። ዕድሜያቸውን ቀንሰው በህፃናት ውድድር ያሸነፉ አትሌቶች እነ ሞ ጋር ሲገጥሙ ፓራሊምፒክስ የሚሮጡ ነው የመሰሉት። ለምን ይዋሻል?
ወደ ኋላ ሄደህ ሞ ፋራህ የሚባል አትሌት ማግኘት ካልቻልክ ወርቅ በወርቅ ሲደራርብ የሚያሳዩ ከደርዘን በላይ ሊንኮችን እኔ እክክልሃለሁ።
የከበቡትን የምሥራቅ አፍሪቃ አትሌቶች ብቻውን ተቋቁሞ በሚያስደንቅ ብቃት ያሸነፈው ሞ ፋራህ የጀግና ጀግና ነው።
አሁን የምንመኘው ቴዶ ለኃይሌና ለቀነኒሳ እንዳዜመላቸው ሁሉ ለወዳጁ፣ ከጎረቤታችን ሶማሊያ ለተወለደውና በደሙ አፍሪቃዊ ወንድማችን ለሆነው ለሞ አንድ ዜማ እንዲለቅለት ነው።

No comments:

Post a Comment