Translate

Thursday, August 17, 2017

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ሆስፒታል በነበሩበት ወቅት በተነሳ የእስር ቤት ቃጠሎ ምስክር ተሰማባቸው

ጌታቸው ሽፈራው
Dr. Fikru Maru
ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ሊፈቱ በተቃረቡበት ወቅት የእሳት ቃጠሎው ተከሰተ። በወቅቱ ታመው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገብተው ነበር። ሳንባቸው ተጎድቶ በመሳርያ ተደግፈው ነበር የሚተነፍሱት። ባልነበሩበት ከተከሰሱ በሁዋላ ምስክሮች ቀርበውባቸዋል። ምስክሮቹ በሀሰት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ለእስረኛ አከፋፍሏል ብለው መሰከሩባቸው። ይህ የሚባለው ከ200 ብር በላይ በማይፈቀድበት ቂሊንጦ እስር ቤት ነው። ዶ/ር ፍቅሩ ላይ ዛሬ አንድ ምስክር ቀርቧል። ምስክሩ ሀዱሽ ሀይለስላሴ የፌደራለደ ፖሊስ ነበርኩ ያለ ግለሰብ ነው። አሁን እሰረኛ ነው።

ከሁለት መቶ ብር በላይ በማይገባበት ቂሊንጦ እስር ቤት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር አስገብተዋል ተብሎ አሳዛኝ የሀሰት ምስክር ሲሰማባቸው የከረሙት ዶ/ር ፍቅሩ ዛሬም ሌላ አሳዛኝ ምስክር ተሰምቶባቸዋል። ቂሊንጦ ላይ ተደራጅቶ ስፖርት መስራት አይፈቀድም። ዶ/ር ፍቅሩ ላይ ግን ቴኳንዶ ይሰሩ የነበሩ ወጣቶችን አይዧችሁ እያሉ ያበረታቱ ነበር ተብሎ ተመስክሮባቸዋል። ይታያችሁ ቂሊንጦ ውስጥ ቴኳንዶ? 20 እና 30 ሆነው? ደግሞ እስር ቤቱ ውስጥ ይፈቅዳል ወይ ሲባል አላውቅም ይላል፣ በድብቅ ነው የሚሰሩት ሲባል በግላጭ ነው አለ ሀዱሽ!
ከ20 እስከ 30 ሆነው ቴኳንዶ ይሰሩ ነበር የተባሉት የኦነግ አባላት ናቸው ብሏል ምስክሩ። የህወሃት አባል ሆኖ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባትና የአልሻባብ አባል ነን እያሉ ይነግሩኝ ነበር አለ። እነዚህን የኦነግ፣ ግንቦት ሰባትና አልሸባብ አባል ነን አሉኝ ያላቸውን ደግሞ የሚያበረታቱት ዶክተር ፍቅሩ ናቸው።
ይህ ምስክር ፍፁም ቸርነት በሚባል ተከሳሽ ላይም መስክሯል። “የተከበሩ የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ በትግርኛ ቲቪ ስለ ወልቃይት መግለጫ ሲሰጡ እየተከታተልኩ እያለሁ ስብሰባ ስላለ ቴሌቪዥኑን ዝጋ ብለውኛል” ብሎ ህወሃታዊ ምስክር መስክሯል። ይህ ለሽብር ክስ የቀረበ የጥላቻ ምስክር ነው። አይ ህወሃት ይህን ሁሉ እዳ መቼ ትከፍለዋለህ?

No comments:

Post a Comment