Translate

Saturday, August 12, 2017

በርካታ ፖሊሶች የሥራ መልቀቂያ እያስገቡ ነው

(ትንሳኤ ራድዮ እንደዘገበው) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መልቀቂያ እንዳያስገቡ ላለፉት አሥራ አንድ ወራት ተከልክለው የነበሩ የመከላኪያና ፖሊስ አባላት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቶአል ከተባለበት ማግሥት ጀምሮ አገዛዙን እጅግ በሚያስደነግጥ ሁኔታ መልቀቂያ እያስገቡ መሆናቸውን ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየገለጹ ነው።
FilePhoto
በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች መልቀቂያ በማስገባት ላይ ካሉ የሠራዊቱና የፖሊስ አባላት መካከል በአዲስ አበባ የሚገኙ ፖሊሶች ከፍተኛውን ቁጥር እንደያዙ ተገልጾአል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት የዛሬው ቀን ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ መልቀቂያ ካስገቡ አባላት
መካከል ከ20 በላይ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖችና ኤክስፔርቶች እንደሚገኙ ታውቋል።
ብዛት ያላቸው የመከላኪያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት በጥቂት ቀናት ውስጥ ባቀረቡት መልቀቂያ የተደናገጠውና ግራ የተጋባው የህወሃት አገዛዝ በደመወዝ ጭማሪና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እንዴት አድርጎ መልቀቂያ ያቀረቡትን አባላት ማስቀረት እንደሚቻልና ወደፊትም ሊቀርቡ የሚችሉ የመልቀቂያ ጠያቄዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ ማስጠናት እንደጀመረ ከውስጥ ምንጮች ለትንሳኤ ሬዲዮ ዝግጅት ከደረሰው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። አገዛዙ እያስጠና ካለው ጥቅማ ጥቅም በተጨማሪም አንድ የሠራዊት አባል መልቀቂያ
ለማቅረብ ማበርከት ያለበት የ7 አመት አገልግሎት ጊዜን ወደ አሥር ወይም አሥራ ሁለት ከፍ ለማድረግ እየታሰበ እንደሆነም ተገልጿል።

ህወሃት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከወረዳ እስከ አገር አቀፍ ያቋቋመው የአፈና መዋቅር እና መዋቅሩን ለመምራት ያቋቋመውን ኮማንድ ፖስት ሳያፈርስ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አጥቶ የተጣሰውን አዋጅ አንስቻለሁ በማለት የገጽታ ግንባታ ሥራ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በዚህ የገጽታ ግንባታ ሥራ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተግባር ላይ በነበረባቸው አሥራ አንድ ወራት ውስጥ አገሪቱ ላይ በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካና በማህበራዊ ዘርፎች ደርሶ የነበረው ጉዳት መጠን ሳይገለጽ እንዲቆይ ከተደረገ ቦኋላ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሚዲያዎች ሰሞኑን መግለጽ መጀመራቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
ሃይለማሪያም ደሳለኝንና በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆኖ የተሾመውን ወርቅነህ ገበየሁ ጨምሮ የአገዛዙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወደ አገራችን የሚገቡ የውጪ አገር ኢንቨስተሮችንም ሆነ አገር ውስጥ ባሉት ባለሃብቶች ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ የለም በማለት በየአደባባዩ መግለጫ ሲሰጡ እንደነበር ይታወሳል። የመንግሥት ሚዲያ ላይ ሰሞኑን እየተሰጠ ያለው የህዝብ እና የፖለቲካ አዋቂዎች አስተያየት ግን በባለሥልጣኖች ሲሰጥ የነበረውን ቃል የሚቃረን ብቻ ሳይሆን ባለሥልጣናቱና የመንግሥት ጋዜጤኞች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ወደ አገር የሚመጡ የውጪ ባለሃብቶች ቁጥር እየጨመረ ነው በማለት ሲሰጡት የነበረውን መግለጫዎች ባዶነት በሙሉ እርቃኑን ያስቀረ እንደሆነ በሰፊው እየተወራ ነው ።

No comments:

Post a Comment