Translate

Saturday, April 9, 2016

የወያኔ ስርሃት ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ዘገበ

12376295_1018502434888475_6231050438946837590_n
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነቶችንና አመለካከቶችን በተገቢው ሁኔታ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው በሃገሪቱ ተቃውሞ ኣየተባበሱ መምጣቱን የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ አርብ ዘገበ። በተለያዩ ክልሎች መጠኑን እያሰፋ የመጣው ይኸው ተቃዎሞ በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበርና በዴሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄዎች ላይ ጥያቄ አስነስቶ እንደሚገኝም ጋዜጣው አስነብቧል።

በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ በትንሹ 266 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ያወሳው ጋዜጣው አስተዳደራዊ ጥያቄን ባነሱ የኮንሶ ማህበረሰብ ዘንድም የሃይል እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል። የሃገሪቱን የብሄር ብሄረሰቦች መብት በመጠቀም በደቡብ ክልል የተነሳውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎ የኮንሶ ማህበረሰብ መሪ የሆኑን ካላ ገዛኸኝ በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበረም ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ በዘገባው አውስቷል።
በአማራ ክልል ከቅማት ማህበረሰብ የአስተዳደር ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለአመታት የቆየ ተቃውሞ ሲሰማ መቆየቱን የዘገበው ጋዜጣው በሃገሪቱ የፖለቲካ አመለካከቶችና ልዩነቶች በአግባቡ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው በመንግስት ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎች እየተባባሱ መምጣታቸውን አስነብቧል። በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘውንና ብሄርን ማዕከል ያደረገው የፌዴራሊዝም ስርዓትም የተጠበቀውን ያህል መረጋጋትና ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችልም በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ገልጸዋል።
የፌዴራል መንግስት በክልሎች ሊያካሄድ ባሰበው የኢኮኖሚና ተዛማች ጉዳዮች ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር ምክክሮችን ማካሄድ ቢጠበቀበትም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌዴራሊም ባለሙያ የሆኑት አቶ አሰፋ ፍሰሃ ለዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ አስረድተዋል።
የፌዴራል መንግስት ክልሎችን ሳያማክር ሰፋፊ የስኳር ፋብሪካዎችንና ሌሎች ፕሮጄክቶችንም በራሱ ስልጣን እያከናወነ እንደሚገኝ ጋዜጣው የተለያዩ መረጃዎች በምሳሌነት በማቅረብ ዘግቧል።
ገዢው የኢህአዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉን ያወሳው ጋዜጣው ውጤቱን ተከትሎ መቀስቀስ የጀመረው ተቃውሞ በፓርቲው የበላይነት ላይ ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ ማሳያ ነው ሲል ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል። በሃገሪቱ ያለው የፌዴራል ስርዓትም ከተለያዩ አካላት ዘንድ ጥያቄ እየቀረበበት እንደሚገኝም ጋዜጣው አክሎ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment