Translate

Monday, April 11, 2016

የአቶ አባይ ፀሃየና የስኳር ኮርፖሬሽኑ ድራማ


ሟቹ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ, አባይ ፀሃይና ,መሰል ጓደኛሞቹ ተሰባስበው በስኳር ፋብሪካዎቹ ጀርባ ወያኔ በትግራይ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን ትምህርት ጨርሶ ቁጭ ያለው ስራ አጥ ስራ ስለማስያዝና በተያያዥም በርከት ያለ የትግራይን ሰው ወደ አዲስ አበባ በስራ ምክንያት ማዘዋወር ስለሚቻልበት ለመምከር ነበር ጓደኛሞቹ ለስብሰባ የተቀመጡት ከብዙ የሃሳብ ፍጭት በኃላ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከተሰብሳቢ ጓደኛቻቸው የተሰነዘሩትን ሃሳቦችና አስተያየቶች ጨምቀው ጠቅለል ያለ መሆን አለበት ያሉትን የራሳቸውን ጨምረው በፅሁፍ መልክ አቀረቡ ::

ይህውም የሚቋቋመውን የስኳር ፋብሪካዎች በቁጥር በርከት እንዲሉ ማድረግ ፋብሪካዎቹ የሚቋቋሙበትም ሆነ የሸንኮራ አገዳ የሚተከሉባቸውን. አካባቢዎች ከረጅሙ የወያኔ ትግራይ የመስፋፋት ፕላን ጋር ተያያዥነት እንዲኖረው ማድረግ እናም ከፋብሪካዎቹ ብዛት ተነስተን በኮርፖሬሽን እንዲዋቀርና ኮርፖሬሽኑን አባይ ፀሃየ እንዲመራው ማድረግ ወደዝርዝር ስንገባ የስኳር ኮርፖሬሽኑ ከመንግስታዊ አደረጃጀት ውጭ በተለየ የራሱ የሆነ አሰራር እንዲኖረው ማድረግና በተዋረድ የሚሾሙ የየፋብሪካዎቹ ሹሞች ተጠሪነታቸው ለአባይ ብቻ ይሆናል ሰራተኛ ቅጥርን በሚመለከት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፋል ቅጥሩ ግን የሚፈፀመው መቀሌ ላይ ይሆናል በትግራይ ክልል ከኮለጅ ምሩቃን እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃን ያጠናቀቁ በስራ አጥነት የተቀመጡ የትግራይ ዜጎችን በተዋረድ ይመዘገባል በአንድ ጊዜ በቁጥር ከአንድ ሽህ ያላነሱ ቅጥረኞች ማሰልጠኛ ይገባሉ በየስድስት ወሩ እንደ አመዘጋገቡ ከስድስት መቶ ያላነሱ ተመዝጋቢዎች ተጓጉዘው ከመቀሌ ወደ ማሰልጠኛ አዋሽ አርባ ይገባሉ:: እነዚህ ሰልጣኞች ሰልጥነው ሲወጡና ወደተመደቡበት ፋብሪካ ሲላኩ አነስተኛው ደሞዝ ተከፋይ ማለትም ለምሳሌ ሾፌር መነሻ ደሞዙ 5,000(አምስት ሽህ) ብር ነው አንድ ጀማሪ የቢሮ ፀሃፊ 5,000 ብር መነሻ ከፍሎ ነው የሚያስጀምረው:: ስራ ያልጀመረው ስኳር ፋብሪካ በዚህ መልክ ሲከፍል ይቆይና ሰራተኛው ስድስት ወር ሲሞላው ወደሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ከነደመወዙ ይቀየራል የነበረበት የስኳር ፋብሪካ ቦታው ባዶ በመሆኑ ማሰልጠኛ ያሉትን ወደየፋብሪካዎቹ በምደባ ካሸጋሸጉ በኃላ መቀሌ ሌላ ስድስት መቶ እንዲልክ ይጠየቃል መቀሌም እንደቅደም ተከተላቸው ይልካል ወደማሰልጠኛም ያስገባል በዚህ መልክ ከ12ዙር ያላነሱ ቅጥርና ማሰልጠኛ ከዚያም ወደ ተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች በዝውውር መልክ ከነደሞወዛቸው በመቀየር የአብዛኛው የመንግስት መስሪያ ቤት ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋዮች እነሱ እንዲሆኑ ትግራይ ውስጥ የነበረውን የተማረ ስራ አጥ በአጭር ጊዜ አብዛኛውን የመንግስት ሰራተኛ በማድረግ አዲስ አበባ ውስጥ ማስገባት እና መስሪያ ቤቶችን በከፊል መቆጣጠር:: የአምስት አመቱ ፕላን ሲዘጋጅ እነዚህን በታሰበላቸው ጊዜ መተግበራቸውን እንጅ ስኳር ፋብሪካው በታሰበለት ጊዜ ተጠናቆ ስራ ስለመጀመሩ የተጨነቁለት ነገር አልነበረም ለዚህም ሁሉም በታሰበለት መንገድ ያለምንም መንገጫገጭ ሲጓዝ ባልታሰበ ሁኔታ የሟቹ ጠ/ሚር መሞት መርዶ ድንገት ድንጋጤን ፈጥሮ ለተወሰነ ጊዜ አቁሞ የነበረ ሲሆን የሁኔታወችን አካሄድ ከተመለከተና የመረጋጋት ነገር ማየቱን እንደተረዳ አዳዲስ ቅጥረኞችን ማሰልጠኛ ማስገባቱን በአቶ አባይ ትእዛዝ እንዲቀጥል ሆነ በዚሁ መሰረት የቀድሞው ጠ/ላይ ከሞቱ በኃላ ለሁለት አመት ያህል እየቆመም እየተገዳገደም ማስቀጠል ተሞክሮ ነበር ሆኖም በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይሸፈን የነበረው የተዛባ የበጀት አመዳደብ እየፈጠጠ የተዝረከረከው አሰራር መታየት መጀመሩንና መሸፈን የማይቻበት ደረጃ ላይ መደረሱን የተረዳው ወያኔ የአባይ ፀሃየን ቦታ በደቡብ ብሄር ሰው በመተካት የደረሰውን ኪሳራ ለመሸፋፈን ተሞክሯል ሆኖም በአዲስ ተሹሞ የመጣው ሰው ቀደም ብሎ ይሰራ የነበረው ስራ በፍፁም ታይቶ ለማለፍ የማይቻል በመሆኑና ድርጊቱም አይን ያወጣ ሆኖ ስላገኘው የስኳር ድርጅቱ ስራ ሳይጀምር ተኮላሽቷል (ሞቷል) መቀጠል አይችልም የሚል ሪፖርት በማቅረቡ አጣሪ ቡድን እንዲላክ ምክንያት ሆነ በአጣሪ ቡድኑ ሂሳቡ ከተመረመረ በኃላ ከ800,000,000ሚሊየን ብር (ከስምንት መቶ ሚሊዮን ብር ) በላይ የገባበት አልታወቀም በሚል ምላሽ ሰጥቷል አጣሪ ቡድኑ አጣራሁት ያለው ሂሳቡን ብቻ ሲሆን በድጋሚ አሰራሩን እንዲመረምር የተጠየቀውን ጥያቄ በወያኔ ሃላፊዎች ርብርብ የቅጥርና የዝውውር አሰራሩን ሳይመረመር በእንጥልጥል ትቶታል የሃይለማርያም አስተዳደር ከአንዴም ሁለት ጊዜ በጥያቄ መልክ አንስቶት ዳግም ለሶስተኛ ጊዜ እንዳያነሳው ለማድረግ የመጀመሪያው ትራንስፎርሜሽን ላይ ፌል ያደረጉ ሳይጠኑ የተካተቱ እቅዶች በሚል ከተዘረዘሩት መሃል ላይ በማካተት ፋይሉ ለጊዜው እንዲዘጋ ተደርጓል::

No comments:

Post a Comment