Translate

Thursday, April 7, 2016

ሰበር ዜና — ወያኔ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ በዳንሻ ከተማ የጦርነት አዋጅ መርዙን ሲረጭ አምሽቷል

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር ኢትዮጵያ
መጋቢት 29 /2008 አ/ም
በዛሬው  ቀን ወያኔ የዳንሻን ወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በነገው ቀን ስብሰባ ካልወጡ ከባድ እርምጃ  እንደሚወስድ  አስጠነቀቀ። ነገ  መጋቢት 30  ሱቆች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣብያና ክሊኒኮችና ሁሉም  የሲቪል  ሰርቪስ  ቢሮዎች  ካላንደር  ሳይዘጋቸው በእነርሱ  ፈቃድ ብቻ  ነገ  እንዲዘጉ  ትእዛዝ  ካስተላለፉ  ብሗላ  በያንዳንድዋ  የዳንሻ  ከተማ ጥግ ልዩ  ልዩ የስድብና  ማስፈራሪያ  የተሞሉበት ትምክህታዊና ውዳቂ  መፈክሮች  የተጻፈባቸው  ጨርቆችና  አርቴፊሻል ላይቶች ዲኮር  አድርጎ “አንድም  የዳንሻ  ሰው  በነገው  ቀን በተዘጋጀው ስብሰባእንዳይቀር!”  በማለት  በተለየ  ሁኔታ ደግሞ  አንድም  በዳንሻ  የሚገኙትን   የወልቃይት  ጠገዴ ወጣቶች ሞባይሎቻችሁ ከቤቶቻችሁ  ጥላችሁ በስብሰባው  ባትገኙ ውርድ ከራሴ!!!”  በማለት በሶስት  መኪኖች  ሞንታርቦዎቹ  እስኪቀደዱ  ድረስ  እያስጠነቀቀ  እስከዚህችው  እስከ ምሽቱ 4:45 ከተማዋን እያመሳት ይገኛል። ውድ ወገኖቻችን እየደረሰብን ያለውን መከራና ስቃይ እባካችሁ ተረዱልን።
በሶስት  ሞንታርቦዎች  ጀሮአችንን  የሚያደነቁሩን  አንሷቸው  ፖሊሶችና ካድሬዎች  በአካል መስጊድ ድረስ ሄደው ሙስሊሞች እየሰገዱ ሳለ ምንም ኣይነት ስቅታ ሳይሰማቸው አጨብጭበው ካስቆሟቸው ብሗላ ነገ ከበሯቸውናየበአል ልብሳቸው ለብሰው እንዲወጡ እያስፈራሩ ሲናገሩዋቸው የመስጊዱን  በር  ከሚዘጋ  ከአንዱ ሙስሊም  ወገናችን ውጭ ሁሉም  በመስጊድ ሲሰግዱ የነበሩት  ሙስሊም  ወገኖቻችን  በንዴት ስግደታቸውን ሳይጨርሱ ፖሊሶቹንና ካድሬዎቹን ሳያናግሩዋቸው እዛው የመስጊዱ  ግቢ  ውስጥ ጥለዋቸው ሄደዋል።

ለህዝበ-ክርስቲያኑ ደግሞ  በከተማ  በሚዞሩት ሞንታርቦ  ሀፍረት ሳይሰማቸው የቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ  አቡነአረጋዊ የቤተ ክርስቲያን ሁሉም አገልጋዮች ደግሞ የቤተ- ክህነት ልብሳቸውን  ለብሰውና  ታቦቱን  ተሸክመው የዝማሬ  መሳሪውያዎች  ሁሉ  ይዘው  እንዲወጡ  በእብሪት  ከከባድ  ማስጠንቀቂያ  ጭምር ጥሪ  አቅርበዋል።  ይህ  በእንዲህ  እንዳለ ተማሪዎቹ  ዩንፎርማቸውን  ለብሰውና  ደብተሮቻቸውን  ይዘው  በአንድ  በኩል፣ ህዝቡ ደግሞ በሌላ በኩል ሆነው በአራት ቡድን  ሆነው  ለሰላማዊ ሰልፍ መውጣት እንዳለባቸው በማሳወቅ በሞንታርቦ  እየተናገሩት እናለ ከሆነ በባለፈው በዳንሻ  ከተማ  የተፈጠረው  ረብሻ  የጸረሰላም  ሃይሎች  በመሀላችንተገኝተው የሰሩት ተንኮል ነው እንጂ  እኛን  የዳንሻን  ህዝብ  አይወክልም!  የእኛ  ድምጽ  አይደለም!!  የጸረሰላምሃይሎች ለፍርድ ይቅረቡልን!  መንግስት  ከኣማራ  ክልል የተላኩ ትምክህተኞችን  ልክ ያስገባልን! መንግስትትዕግስቱ  በዝቶ  በትምክህተኛ  ሃይሎች  ትግሬነታችን ተነጥቆ  ያልጠየቅነውን  አማራነት በግድ  ሲጫንብን  ለምን ዝም ይላል? እያላችሁ ቀሳውስት በአንድ በኩል፣ ሼኮች በሌላ በኩል፣ ተማሪዎችና መላው ህዝብም እንዲሁነገ ጧት ይፋ በሚሆንላችሁ  ቡድን ሆናቹህ በየራሳችሁ ቡድን መናገር አለባችሁ” ብለዋል። ይህ ሳያደርግ የሚቀር ጥሪየተደረገለት አካል ቢኖር ግን የጸረሰላም ሃይሎች ተባባሪ እንደመሆኑ መጠን ከነገ ጀምሮ ለሚደርስበትበህልውናው ያነጣጠረ ጥቃት ሃላፊነቱ በራሱ ይወስዳል ብለዋል። “ይህን  የማያደርግ  ሰው የትግራይ  ህዝብ  ጠላት ብቻ ሳይሆን  እንዲሁም  የኢትዮጵያ  የመለስ  ራእይ የሚያደናቅፍ  የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት እንደመሆኑ መጠን ለዚህም መንግስት ሃላፊነት አይወስድም” በማለት ስጋታችንን ከፍ እንዲል በማድረግ ከባድ ጫና በህዝባችን ላይ ሲፈጥሩ ውለው ኣሁንም ይሔን ጽሑፍ እያዘጋጀን እስካለንበት ድረስ ጫናውን በመፍጠር ላይ ናቸው።
የትግራይ መንግስት ከአሁን በፊት ያደረሰብንን ሰቆቃ እንዳይበቃው ጭራሽ በዚህ መልክ እኛን እያፈነና እያሸማቀቀ  ልዩ ልዩ የውሸት ቀረጻ በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝብ በውሸት በቀረጻው በማደናገር እውነተኛ የአማራ ማንነታችንን በሃይልና  በአፈና  ነጥቆ በግድ ያልሆነውን  የትግሬ ማንነት  ለመጫን ሲል እንዲህ  በአስጨናቂና  አጣብቂኝ ሁኔታ እንድንገኝ አድርጎናል።
“ውሽትና  ስንቅ  እያደር ይቀላል”  እንዲሉ በግዜ ሂደት እውነታው እንደሚወጣና እኛም የአማራነት ማንነታችን እንደሚከበር በልበ ሙሉነት ብናምንም ይሄን ያወቀ የትግራይ መንግስትና ካድሬዎቹ  ግን  ‘በውሸት  ህጋዊነት’  ከባድ የሞት ድግስ እየደገሰልን ስለሆነ የተወደድከውና  የተከበርከው  መላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  ሆይ በእኛ በወገኖችህ ላይ እየደረሰ ያለውን  መጠነ-ሰፊ ጭፍጨፋ በማውገዝ ከጎናችን እንድትቆም አደራ እንላለን።
የግዜ  ጉዳይ ሆኖብን ነው እንጂ እኛ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ  እንኳን አሸባሪ ልንሆን ጣልያንና  ድርቡሽ  እንዲሁም  በየግዜው የተነሱ በሱዳን በኩል የመጡብንን ጠላቶች እንኳን የመከትን  ለኢትዮጵያ  ሰላምና  አንድነት የምንተጋ ሰላማዊ  የአማራ ህዝብ  መሆናችን ታሪክ የሚመሰክረው ሃቅ ነው። እኛ የጎንደር አማራ ህዝብ አሸባሪዎች የሚል ስም በፍጹም አይመለከትንም  የሰማነውም  በወያኔና  ካድሬዎቹ  ነው፤ ማንነት መጠየቅ  አሸባሪነት ከሆነ ግን  ከዛሬ  ጀምሮ  አሸባሪዎቹ  እኛ  የወልቃይት  ጠገዴ አማራ ህዝብ ሳንሆን ኣሸባሪዎቹ   ወያኔና ካድሬዎ  እንደሆኑና  ይልቁንስ  በማህበረሰባችን  ህጋዊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማድረግ  ሲል የለጠፈብን የውሸት ማንነት መሆኑን መላው የኢትዮጵያ  ህዝብና መላው አለም ኣውቆልን ከዚህ የጥፋት ዘመቻ እንዲጠብቀን በጥብቅ እናሳስባለን ።
አዎ አሸባሪነትማ ምንም ወንጀል ያልሰራነውን እኛን የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ማፈን፤በመኪና  እየገጩ  መግደል፤ ያለ በዳላችን በሃሰት ፍርድ  ማሰቃየትና ደብዛችንን ማጥፋት፣ የእኛን የአማራ ማነንት  ከህግ በላይ ሆኖ መጨፍለቅና ህልውናችንን በመካድ በግድ ያልሆነውን የትግሬ ማንነት ማከናነብ ነው!!! እነዚህና ሌሎች ያልጠቀስናቸው በደሎች የሚያደርስ  ህግ የማይገዛው የትግራይ መንግስትና ካደሬዎቹ  ናቸው አሸባሪ  ተብለው መኮነን ያለባቸው። እንደዚህ ኣይነት የኣምባገነን  ውዳቂ ኣስተሳሰብ በ21ኛው መ.ክ.ዘ  ልእልና ኣግኝቶ የኣንድ ማህበረሰብ ማጥፊያ መንገድ ሊሆኑ ኣይገባቸውም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቢደረግ ግን ለተከበረችው ኣገራችን በእውነቱ በጣም ኣሳፋሪ ታሪኳ ይሆናል ማለት ነው።
ስለዚህ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በወልቃይት ጠገዴ ወገኖችህ  በወያኔ እየደረሰብን ያለውን ፍጹም የሆነ አፈና፣ የዘር መጥፋት፣ የኣማራ ማንነት መጨፍለቅና የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም ድጋፋችሁን በሰላማዊ ሰልፍ እንድትገልጹልን በሞት አፋፍ ላይ ሆነን ይህንን ጥሪ አቅርበናል።
መላው የአማራ ህዝብም በፍትነት  ሊደርስልን  ይገባል።  እኛ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶችና ህዝብ  ግን  እኛም  በግድ  ካስወጡን  ውርድ  ከራሳችን”  ብለን ተማምለናል። ውድ የአማራ ህዝብ ሆይ ጉዳዩን ራሳህን ለማንኛውም ኣይነት ኣስፈላጊ ዝግጅት እያደረክ  ጉዳያችንን  በአንክሮ እንድትከታተል  እኛ  የመከራው ተካፋይ የሆንን  የዳንሻ  ህዝብ ጥሪ  አቅርበንልሃል። እባካችሁ ድረሱልን በላያችን ላይ በያንዳንድዋ ደቂቃ ወያኔ ብዙ ግፍ እየፈጸመብን ነው፤ ብአዴን ባይደርስልን እንኳ የምንወደው ወገናችን ሊደርስልን ይገባል!!! እኛ ይህ ሁሉ ሰቆቃ  የምንቀበለው ስለ አማራነታችን ብለን ነውና እባካችሁ ድረሱልን።
ተጻፈ በወልቃይት ጠገዴ
ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ
መጋቢት 29 /2008 አ/ም

No comments:

Post a Comment