
የቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚደንት አቶ ኦኬሎ አኳይ የጋምቤላ ጭፍጨፋን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ማብራሪያ ሰጡ። የጭፍጨፋውን ሂደት በማዛባት፣ የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ እንዲያቀርቡ በመገደዳቸውና ጭፍጨፋው የህሊና ሰላም ሰለነሳቸው ፕሬዚደንትነታቸውን ጥለው ድንበር አቋርጠው መሸሻቸውን በጽሁፍ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።

ከሳምንት በፊት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር በሚገኙ የኑኢር ማህበረሰብ ላይ ከጎረቤት ደ/ሱዳን አንደመጡ የሚነገረላቸው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የደ/ሱዳን የመከላከያ ሰራዊቱን የድምብ ልብስ ያጠለቁ መሆናቸው የተነገረላቸው የሞራሌ ጎሳ ተወላጆች በ 10 የኑዊር መንደሮች ላይ በከፈቱት የጅምላ የተኩስ እሩምታ ከ 200 በላይ ሰዎች ህይወትን በመቅጠፍ ከ100 በላይ ጨቅላ ህጻናትን ደግሞ አፍነው በመወሰድ ፣ከ 2ሺህ በላይ የቀንድ ከበቶቻቸውን በመዝረፋቸው ሳቢያ በበርካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊናኦች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ሃዘን እና ቁጭት መቀሰቀሱ አይዘነጋም።




የተከበሩት የቀድሞ የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ለወያኔ በግፍ ተላለፈዉ ሲሰጡ የእንግሊዝ የደህንነት አካላት ያዉቁ እነደነበር እና የየመን የጸጥታ ሐይሎች እንዲሁም የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን በመተባበር እገታዉን እንዳካሄዱት ዛሬ ከብሔራዊ መረጃ ምንጭ ተገኝቷል።




ኢትዮጵያ በበብዛትም ይሁን በጥራት በውጭው አለምም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ምሁራን ያፈራች ሀገር ነች። በጅጉ የሚያሳዝነው ግን በሀገሪቱና በሕዝቧ ችግር ላይ ሀሳብ ሲሰጡ ፣ ባደባባይ ሲከራከሩና ሲታገሉ የሚታዩት በጅጉ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ ነው ተከታታይ መንግስታት በምሁራን ላይ ያደረሱት ጥቃትና ማግለል ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ብዙዎች መከራን ከህዝብ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ አጎንብሶ ማሳለፈን የመረጡበት ሁኔታ አለ። ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑም ለግል ጥቅማቸው ቅድሚያ በመስጠት ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር በመተባበር የሚሰሩ መኖራቸውም አይካደም። አብዛኛው ምሁራን በተለይም በብዙ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸው ጭምር ሀገሪቱን ከገባችበት ማጥ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ እየተሳተፉ አይደለም። ይህ ዛሬ ባለው ችግርም ይሁን በታሪክ ፊት አሳዛኝ ነው።
ኢሳት ባለፉት ስድስት ዓመታት (ከሚያዚያ 2003 እ/ኤ/አ April 2010) ጀምሮ በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እያገለገል ይገኛል።ኢሳት በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ ከሳተላይት ለማውረድ ስድስት ዓመታት ሙሉ በተደረገው የመንግስት ርብርብ 20 ያህል ሳተላይት ለመቀየር እና ተጨማሪ ወጪ ለማውጣት ተገደናል።ለሳተላይት አቅራቢ ኩባንያዎች የተማጽኖ ደብዳቤ በመጻፍ እና መደለያ በማቅረብ እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስትን የመሳሰሉ ታዋቂ የምዕራብ ሚዲያዎች ጭምር እንደዘገቡት ኢሳት ላይ የሳይበር ጥቃት ቢሞከርም ሁሉንም ተቋቁመን ለ 6ኛው ዓመት ደርሰናል፥ ግባችን ዓመታት መቁጠር ሳይሆን ነጻነት በመሆኑ የኢትዮጵያውያን የዋይታ ድምጾች በደስታና ድል ሲመነዘሩ ለማየትና ለመስማት ተስፋም ሰንቀናል።