Translate

Friday, March 21, 2014

በመኢአድ በኩል የቀረበው ቅድመ ውህደት ያለመፈረም ሰበብ አሳዛኝና የህዝቡን ጥያቄ ያኮሰሰ ነው!!

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሰጠው መግለጫ

Andenat Party UDJየአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ለረዥም ዓመታት የህዝብ ፍላጎትና አንገብጋቢ የሆነው ተቃዋሚዎች ” ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ ” ጥያቄ ለመመለስ በስትራቴጂ አምስት ዓመት እቅድ ውስጥ በማካተት መንቀሳቀስ ከጀመረ ዓመታት አስቆጥረዋል:: የውህደቱ ጉዳይ ለአንድነት ፓርቲ የአንድ ሳምንት ጥያቄ ሳይሆን ስትራቴጂ ግብ ነው:: የዚሁ አካል የሆነው እንቅስቃሴ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች መሐከል መካሄድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል:: ሂደቱን ለመቋጨት በርካታ ድርድሮችና የደብዳቤ ልውውጦችም ቢከናወንም እነሆ አሁንም ተጨባጭ ውጤት በተግባር አለመታየቱ የሁለቱም ፓርቲ አባለት በጅጉን እያሳዘነ ነው::
በተለይ በቅርቡ እየተካሄደ ከነበረው ተግባር መካከል ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈልንን ደብዳቤ መሰረት በማድረግ የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲገናኙ የተጠየቀው ጥያቄ በደስታና በላቀ መንፈስ ተቀብለነዋል::
በዚሁ መሰረት መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም ለፊት ውይይት የምንፈልገውና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት በተጠራውና የሁለቱ ፓርቲዎች የብ/ም/ቤት አባላትና የላዕላይ ም/ቤት አባላት በተገኙበት ለታሪክ በተቀረፀ ወሳኝ ስብስባ ስፊ የሃሳብ ልውውጦች ተካሂደው የፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የሚከተሉትን አስገዳጅ የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ነበር ::
በዚሁም መስረት:-
1. የሁለቱም ፓርቲዋች አባላት አላስፈላጊ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት ውህደቱን አታጓቱ ውህደት የማትፈፅሙ ከሆነ እኛ አባላት በራሳችን ውህደት እንፈጽማለን የሚል ጥብቅ ተማፅኖና ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል::
2. በአጠቃላይ የሁለቱ ፓርቲዎች ፕሬዝደንቶችና አደራዳሪ ሽማግሌዎች በገቡት ቃል መስረት ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም ቅድመ ውህደት የመግቢያ ሰነድ እንዲፈረም ከስምምነት ተደርሶ ነበር ::
3. የሁለቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች የውህደት አስፈፃሚውን ጠቅላይ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑትን የስም ዝርዝር የፊርማው ሰነ ስርዓት በሚከናወንበት እለት እንዲያመጡ ተስማምተን ነበር ::
በከፍተኛ አመራሮች በሁለቱ ስራ አስፈፃሚዋች ውሳኔ መሰረት የሁለቱ ፓርቲ ፕሬዝደንት ተሰማምተው የቅድመ ውህደት መግቢያ ሰነድ በሁለቱ ፓርቲዎች የድርድር ኮሚቴ አባለት መካከል ተፈራርመን ሆቴል ተከራይተንና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝባዊ ሰብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ ክፍል የዕውቅና ሰነድ አግኝተን የመጨረሻ የሰነ ሰርዓቱን መርሃ ግብር በመጠባበቅ ላይ እያለን በድንገት በመኢአድ ፕሬዝደንት በኩል በቁጥር መ /ኢ/አ/ድ 278/06 መጋቢት 9 ቀን 2006 ዓ.ም በዕለቱ የቅድመ ውህደት ፊርማውን መፈረም እንደማይችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ለፓርቲያችን መድረሱ በእጅጉ አሳዝኖናል::
ከደብዳቤው እንደተረዳነው መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከበርካታ የሃሳብ ልውውጥ በኋላ የደረሱበትን ውሳኔ የሚቀለብስ የሁለቱ ፓርቲዎች ተደራዳሪዎች እየተሰማሙ በቃለ ጉባኤ ያፀደቁትንና ከሁሉም በላይ የሁለቱ ፓርቲ ተደራዳሪዎች ለቅድመ ውህደት ባዘጋጁትና ባፀደቁት የመግቢያ ሰነዶች ላይ የሰፈሩ ነጥቦችን እንደ አዲስ በማንሳት በጥቃቅን ጉዳዮች በመጠመድ የቅድመ የቅድመ ውህደቱ እንዳይፈረም ተደርጓል ::
ለዚህ ታሪካዊና የሕዝብ ጥያቄ መደናቀፍ ምክንያት የመኢአድ ፕሬዝደንት ሲሆኑ ይህን ሆኔታ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ለሁለቱ ፓርቲዎች አባላት ደጋፊዎች በግል ተነሳሽነትና በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ሂለቱን ፓርቲዎች ለማደራደር ሲደክሙ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ለህዝቡ ጥሩ ዜና ባይሆንም ላለመፈረሙ ሃላፊነቱን የሚወሰዱት የመኢአድ አመራሮች በተለይ ፕሬዝደንቱ መሆናቸውን ማሳወቅ እንወዳለን ::
በዚህ አጋጣሚ ለውህደቱ መሳካት የመኢአድ አባላትና ከፊል አመራሩ እያሳዩ ለሚገኘው ፍላጎትና ጥረት ፓእሪያችን መልካም አክብሮቱን መግለፅ ይወዳል ::
መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Andenar (UDJ)
andenat

No comments:

Post a Comment