Translate

Friday, September 20, 2013

በኢትዮጵያ የመብት ጥሰት በከፍተኛ ሁናቴ ተባብሷል፤

በኢትዮጵያ የመብት ጥሰት በከፍተኛ ሁናቴ ተባብሷል፤ በሃገራችን በሚገኙ ‹ማረሚያ› ቤቶች እየደረሱ ያሉ ሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በፖለቲካ እና የህሊና ‹ታራሚዎች› ላይ እየደረሰ ያለው ጥሰትን የመጨረሻ ደረጃ ማሳያ አይደለም፡፡ ምናልባትም ይህ ግፍ በህውሃት ዝቅተኛው ሊሆን ይችላል፡፡
በህውሃት እስር ቤት የሚደርስባቸው በደል፣ግፍ፣ስቃይ እና የመብት ጥሰት ሊሰማላቸው ያልቻለ ብዙዎች እንዳሉ ለመረዳት ነብይ መሆን አይጠይቅም ነገሩ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
እንደ አጋጣሚ ሆኖ ታዋቂ ወይም ስራው/ዋ ከሚዲያ ጋር የተያያዘ ከሆነ፤ የሱ/ሷ ጉዳይ ለሚዲያ የመቅረቡ እድልም ሰፊ ነው፡፡ታዋቂና ለሚዲያ ቅርብ የሆነ ሰው የሚደርስባት ማንኛውም ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት ለሚዲያ እንደሚደርስ እየታወቀ መብቶቿ በአደባባይ የተጣሱ፤ የሌሎች የፖለቲካ እና የህሊና ‹ታራሚዎች› አያያዝ ሁኔታ ከነሱ የባሰ እንደሚሆን ማስብ ተገቢ ነው።

በማንኛውም ሰው ላይ የደረሰ/እየደረሰ ያለ ማንኛውም አይነት የመብት ጥሰት ሁኔታውን መቀየር ባንችል፤ ቢያንስ መበደላቸውን እና መብታቸው እየተጣሰ እንደሆነ ካየን/ከሰማን በማንኛውም መልኩ ላልሰማ በማሰማት የበኩላችንን እንወጣ፡፡
ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎቿ ምቹ፣ ሁሉም ዜጎቿ ካለምንም የጥላቻ ስሜት እርስ በርስ ተደጋግፈው ሰብኣዊና ቁሳዊ የሀገር ግንባታ ላይ ብቻ የሚያተኩርበት እና የበለጠ የምታኮራ ሀገር ሆና ማየት የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በዚህ አይነት የመብት ጥሰት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ሕልማችሁን እንድታጋሩ እና የሌሎችን ሕልም እንድትጋሩ መጣር ያስፈልጋል፡፡
ለዛም
ስለሚያገባን እንጦምራለን!!!
 Zekarias Asaye

No comments:

Post a Comment