Translate

Thursday, September 26, 2013

እነ ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ፕሬስ ካውንሰል መመስረት አልቻሉም

qwe

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ወይንም ፕሬስ ካውንሰል ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበው ጊዜያዊ ኮምቴ የካውንስሉን መስራች ጉባዔ መጥራት እንዳልቻለ ተጠቆመ፡፡
በኢህአዴግ ደጋፊነት በሚታወቁት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስበርስ ባለመግባባቱና ከብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል፡፡
ይህ ኮምቴ በወ/ሮ ሚሚ ሊቀመንበርነት፣ በአቶ አማረ አረጋዊ ምክትል ሊቀመንበርነት መመራት ከጀመረ ሶስት ዓመታት የቆጠረ ሲሆን በተለይ በሁለቱ ሰዎች መካከል ባለ
ግልጽ የስልጣን ሽኩቻና መናናቅ ምክንያት ምስረታውን ማካሄድ እንዳልተቻለ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

አሁን በስራ ላይ የሚገኘው የመገናኛ ብዙሃንና በሚረቀቅበት ወቅት መንግስት የፕሬስ ካውንስል እንደሚያቋቁም ተደንግጎ የነበረ ቢሆንም በተለይ በግሉ ፕሬስ ያልተቆጠበ ተቃውሞ ረቂቅ ህጉ ተሻሽሎ እንዲወጣና በተሻሻለውም ሕግ መሰረት ፕሬስ ካውንስሉን የማቋቋሙ ኃላፊነት የሚዲያ ባለሙያዎች
እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል፡፡
የፕሬስ ካውንስሉ ቢቋቋም በተለይ ጋዜጠኞች በትንሽ በትልቁ ጉዳይ ፍ/ቤትና ፖሊስ ጣቢያዎች የሚመላለሱበትን በማስቀረት የሚቀርቡ ክሶችና ቅሬታዎች በአስተዳደራዊ መንገድ መፍትሔ ለማስገኘት ይረዳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ ከምርጫ 1997 በፊት 385 በላይ ጋዜጦችና መጽሔቶች የነበሩት በአሁኑ ወቅት እጅግ አሽቆልቁለው 16 ጋዜጦችና 17 መጽሔቶች ብቻ በህትመት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአንጻሩ በመንግስት የተያዙ የራዲዮና የቴሌቪዝን ጣቢያዎች ቁጥር አድጎ በጠቅላላው 23 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 15 ያህሉ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎች፣ ራዲዮ ፋናን ጨምሮ 5 የግል ራዲዮ ጣቢያዎች ፣10 የመንግስት ጣቢያዎች ፣1 የቴሌቪዝንና፣ 3 የክልል ጣቢዎች ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment