Translate

Saturday, September 21, 2013

የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ – አንድነት የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ አንድነት

1238242_721208644562266_1225807894_n
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራትከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡
ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡



ለመጨረሻው ዙር ሳያልፉ የቀሩት አቶ ትግስቱ አወሉ እና አቶ ሽመልስ ሀብቴ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረው አንድነትን ለመምራት ከሚመረጠው ቀጣይ ሊቀመንበር ጋር ትግሉን ለማፋጠን እንደሚተጉ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡
በተያያዘም ዜና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በቅርቡ በሚመረጠው አዲሱ ስራ አስፈፃሚ የሚቀጥሉ ተከታታይ ህዝባዊ ንቅናቄዎች እንደሚኖሩና በቀጣይነት ከሚነሱት የንቅናቄ አጀንዳዎች መካከል ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች እንደሚገኙበት ታውቀዋል፡፡ ከፓርቲው ህዝብ ግንኙነት የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው አንድነት የትግል የተፅእኖውን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ በማድረግ ወደ ለውጥ የሚደረገውን ትግል ከዳር የሚያደርሱ ስትራቴጂዎችን ነድፎ ከዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር እንደሚታገል አስገንዝቧል፡፡

No comments:

Post a Comment